2013-03-29 16:36:31

ሲመተ ሊቀ ጳጳስ ቦነስ አየረስ፤


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በትረ ሥልጣነ ጴጥሮስ ተቅብለው ሥራቸው ከጀመሩ ለመጀምርያ ግዜ ትናንትና መንበራቸው ለነበረው ለቦነስ አየርስ የሚያገለግሉ አዲስ ሊቀ ጳጳሳት ሾመዋል፣ ቅዱስነታቸው የሾሙዋቸው ብፁዕ አቡነ ማርዮ አውረልዮ ፖሊ ሆነው እስካኡን የሳንታ ሮዛ ሰበካ ጳጳስ የነበሩ ናቸው፣ 65 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ብፁዕ አቡነ ማርዮ አውረልዮ ፖሊ የቀለም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በ22 ዓመት ዕድሜአቸው በቦነስ አየርስ ዓቢይ ዘር አ ክህነት ገብተው አስፈላጊውን ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ በ25 ኅዳር 1978 ዓም ክህነት ተቀብለዋል፣ ወዲያውኑ የቅዱስ ካይታኖ ቍምስና ቪካር በመሆን ለሁለት ዓመት የዓቢይ ዘር አ ክህነት አለቃ ሆነውም ለ7 ዓመት የመንፈስ ቅዱስ አገልጋዮ አበነፍስ ሆነው ለ3 ዓመት አገልግለዋል፣ ለ4 ዓመታት ደግሞ በቦታው ለሚገኝ የቤተ ክርስትያን ተቅዋም የቅዱስ ቶማስ ዘአኵኖ የወንድማሞችና የቡድኖች ማኅበር ረዳት ሆነው ሰርተዋል፣ በዘር አ ክህነት እንደአስተማሪና እንደአበነፍስ እንዲሁም እንደ አለቃ በየጊዜው አገልግለዋል፣
በየካቲት 8 ቀን 2002 ረዳት ጳጳስ እንዲሆኑ ተጠርተው በሚያዝያ 20 ቀን 2002 በአሁኑ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ያኔ ካርዲናል በርጎልዮ እጅ ቅብአ ጵጵስና ተቀብለዋል፤ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓም ደግሞ የሳንታ ሮዛ ሃገረ ስብከት ጳጳስ ሆነዋል፣
በአርጀንቲና ረኪበ ጳጳሳት በተለያዩ ን ኡሳን ክፍሎችና ኮሚቴዎች እንደ አላፊና መሪ ሆነው አገልግለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.