2013-03-29 13:33:09

ሰሙነ ኅማማት: ጸሎተ ሐሙስ


RealAudioMP3 በላቲን ሥርዓት በዚህ ወደ በዓለ ፋሲካ በሚያሸጋግረው የዓቢይ ጾም ወቅት መሠረት ትላንትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዋሜ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባንና ምስጢረ ክህነት የፈጸመበት ዕለተ ጸሎተ ሓሙስ ተክብሮ መዋሉ ሲገለጥ፣ በጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርድእቱ የፍቅር ትእዛዝ “እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” (ወንጌል ዮሐንስ ምዕ. 13 ቍ.34) ሲል የሰጠው አዲስ ትእዛዝ የሚከበርበት እለት ከመሆኑም ባሻገር “…ከማእድ ተነሣና ልብሱን አስቀመጠ ፎጣም እንስሥቶ በወገቡ ታጠቀ ከዚህ በኋላ በመታጠቢያ ሳሕን ውሃ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብ ጀመረ በታጠቀው ፎጣ እግራቸውን አበሰ…እናንተ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣጠብ ይገባችኋል እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁት እናንተም እንድታደርጉ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁ…(ዮሐ. 13.1-15 ተመ.) በማለት የፈጸመው የሕጽበተ እግር ሊጡርጊያ የሚፈጸምበት ዕለትም ሲሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትላትና በሮማ ሰዓት አቆጣጠር አምስት ሰዓት ተኩል ሮማ ካሳል ደል ማርሞ ወደ ሚገኘው የወጣቶች የጸባይ ማረሚያ ወኅኒ ቤት በመሄድ ሕጽበተ እግር እንደሚፈጽሙ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በወህኒ ቤቱ ከሚገኙት የተለያዩ አገር ዜጋና የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ ታዳጊ ወጣቶች መካከል ለተወጣጡት 12 ወጣቶች ሕጽበተ እግር በመፈጸም የእያንዳንዱን እግር በፎጣ አብሰው በመሳም የመፈጸሙበት የሊጡርጊያ ሥነ ሥርዓት ሁኔታ በወህኒ ቤቱ የሚያገለግሉት የበጎ ፈቃድ ማኅበር አባላት እንደመሩትም ሥነ ሥርዓቱን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ ካጠናቀረቡት ዘጋ ለመረዳት ሲቻል፣ በወህኒ ቤት የግብረ ሠናይ አገልግሎት የሚሰጠው የበጎ ፈቃድ ማኅበር አባል አናሊዛ ማራ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በወህኒ ቤቱ አገልግሎት የሚሰጠው የበጎ ፈቃድ ማኅበር በወህኒ ቤቱ ለሚገኙት ታዳጊ ወጣቶች ቅርብ በመሆን በተለይ ደግሞ እሁድ ጧት በበዓላት ቀን ማለትም በበዓለ ልደት በበዓለ ፋሲካና እንዲሁም በአዲስ ዓመት እዚያ በወህኒ ቤቱ በመገኘት ለወጣቶቹ ቅርብ በመሆን የቤተሰብ መንፈስ እንዲኖሩ የሚያደርግና እንዲሁም የሕንጸት መርሃ ግብር ያቀርባል ካሉ በኋላ አያይዘውም በወህኒ ቤቱ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መገኘት የፈጸሙት ሕጽበተ እግር ያስደመጡት ሥልጣናዊ ስብከት በወህኒ ቤቱ የሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ ወጣቶች የማረከ አለ ዜግነት የሃይማኖት ልዩነት ለሁሉም ወጣት ያሳዩት ቅርበት ያላቸው የላቀ ሰብአዊነት ትህት ያጎላ ሲሆን ትህትናቸውና ሰብአዊነታቸው ሁላችን ልንከተለውና ልንኖረው የሚገባን አብነት ነው ብለዋል።
የቅዱስነታቸው በወህኒ ቤቱ መገኙት ሁሉንም ማስደሰቱና ልብን በኃሴት የሞላ በተለይ ደግሞ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ላልሆኑት ወጣት እስረኞችን አስደንቀዋል፣ ይህ በወህኒ ቤቱ የሚያገለግለው የበጎ ፈቃድ ማኅበር በነጻ የሚያገለግል በመሆኑ ወጣት እስረኞች ይኸንን በመገንዘብ አድናቆታቸውን በመግለጥ ከበጎ ፈቃድ አባላት ጋር ቅርበት ለማጽናትና ክፍት በሆነ ልብ በመወያየት ምክር ለመጠየቅ ይገፋፋቸዋል ካሉ በኋላ፣ በወህኒ ቤቱ የሚገኙት ታዳጊ ወጣቶች በስርቆት አደንዛዥ እጸዋት ማሰራጨት የመሳሰሉ ወንጀል የፈጸሙ በሌሎች የወንጀል ቡድኖች ለዚህ ወንጀል የተዳረጉ ናቸው። ወጣቶቹ ለመለወጥና ታርመው በሰላም ከኅብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው ለመኖር ያለው እድል ፈጽሞ የፈጸሙት ወንጀል እይሰርዘውም በመሆኑ ለዚህ የሚያበቃቸው ሕንጸት በተለያየ ዘርፍ በማግኘት የወህኒ ቤቱ ቆይታቸው የሕንጸትና ጸባይ የማረሚያ ወቅት እንዲሆንላቸው በሁሉም መስክ ድጋፍ ያገኛሉ በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.