2013-03-28 13:14:33

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝግብ


RealAudioMP3 የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገበ ሃይማኖት ዝክረ 20ኛው ዓመት ምክንያት የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስትያን ጉባኤና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳርዩስ ኮዋልዝይክ አማካኝነት ሳምንታዊ ዕለተ ማክሰኞ የሚያቀረብው አስተምህሮ በመቀጠል ትላትና አባ ኮዋልዝይክ 19ኛን ክፍለ ትምህርት፦ ኅልወተ መላእክት ከሰብአዊ ኅላዌ ጎን ኅያውነታቸው አንዱ የእምነት ሐቅ ነው” በሚል ርእስ ሥር በማቅረብ፣ ካቶልካዊት ቤተ ክርስቲያን መላእክት የእግዚአብሔር መልእክተኞች መሆናቸው እውቅና ትሰጣለች።
እግዚአብአብሔር ፈፍጣሬ ኵሉ “ሰማይንና ምድርን” ፈጥረዋል። ይኽ ማለት ደግሞ ሁሉም ኅያው የሆነ እርሱ ፈጥሮታል ማለት ነው። ምድር ሲል በጠቅላላ ግኡዝ ተጨባጭ ነገር ሰማይ ሲል ደግሞ መንፈሳውያን የማይጨበጥ የማይዳሰሰውን ነገር ሁሉ ያመልክታል።
የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቁጥር 328፦ “የመንፈሳውያን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙውን ጊዜ ‘መላእክት’ ሲል የሚጠራቸው ረቂቃን ፍጡራን ሕላዌ የእምነት ሐቅ ነው። የመጽሓፍ ቅዱስ ምስክርነት እንደማያሻማው የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ግልጽ ነው።” በማለት ኅልወተ መላእክት ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክረዋል። ቅዱስ አጎስጢኖስ መላአክት፦ መልአክ በሚል ነጠላ ስም ተግባሩና ተልእኮው ኃላፊነቱ የሚያጠቃልል መሆኑ በማብራራት፣ መልአክ የእግዚአብሔር መልክተኛ የተልእኮ ኃላፊነት ለበስ መሆኑ ባህርዪውም መንፈስ መሆኑ በጥንቃቄ በቲዮሎጊያና በቅዱስ መጽሐፍ ሥር እንደተነተው አባ ኮዋልዝይክ ባቀረቡት አስተምህሮ ጠቅሰው፣ ከነዚህ መላእክት ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት “ጠባቂ መላእክት በማለት የሚሰይማቸው እንዳሉና ማንኛውም ምእመን ጠባቂ መልአክ እንዳለው በመዝሙረ ዳዊት ቁ. 92፦ በመንገድህ የሚጠብቁህ እግዚአብሔር ለመላእክቱ ትእዛዝ ሰጠ” ሲል ወደ እምብራውያን ምዕ. 1 ቁ. 14 “መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎች አገልግሎት ይላኩ የለምን” የሚለውን ቃል ከጠቀሱ በኋላ ኢየሱስ በተልእኮው በመላእክት እንደታጀበና እንደተሸኝም ወንጌል ያረጋግጥልናል ብለዋል።
ቅዱስ ባዚሊዮስ ዘቀሳሪያ፦ “እያንዳንዱ አማኝ ወደ ሕይወት የሚመራው ከጎኖ ሆኖ የሚጠብቀው እረኛ አለው” (ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 336) ይላል። ስለዚህ እያንዳንዳችን ከጠባቂው መልአካችን ጋር ልክ እንደ አንድ ጥብቅ ጓደኛ ልንወያይ ልንነጋገር ይገባናል ካሉ በኋላ የዚህ ምስክርነትም ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ በአንድ ወቅት “ከአበይት አካላት ጋር ስገናኝ ቀድሜ ጠባቂ መልእኬ ከምገናኘው አካል ጠባቂ መልእክ ጋር እንዲወያይ እልከዋለሁ በማለት የገለጡት ሓሳብ ጠቅሰው፣ መልእክት አምላካውያን-መለኮታውያን ሳይሆኑ የአንድነትና ሦስትነት እግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸው በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.