2013-03-25 13:39:41

አባ ካንታላሜሳ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቤተ ክርስቲያንን በበለጠ ለዓለም ክፍት የሚያደርጉ ናቸው


RealAudioMP3 የሐዋርያዊ ቤተ ጳጳስ ሰባኬ የካፑቺን ማኅበረ አባል አባ ራኒየሮ ካንታላመሳ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መጠሪያቸው እንዲሆን የመረጡት ፍራንቸስኮስ የሚል ስም ቤት ክርስቲያን በበለጠ ወደ ዓለም ክፍት መሆንዋ ይኽም የሁሉም ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ የሚያጎላ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ አብነት የሚኖር ነው ካሉ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን በይፋ ከጀመሩበት ዕለት ጀምረው ደጋግመው የተጠቀሙበት እቃቤ የሚል ቃል እርሱም ተፈጥሮን ማስተዳዳር ብቻ ሳይሆን ማቀብንም ጭምር ያለው አስፈላጊነት የሚተነትን እንዲሁም ፍቅር የዋህነት የተሰኙት ግሦችም ሲያዘወትሩ ይታያል። ቅዱስ አባታችን ይላሉ አባ ካንታላሜሳ ካላቸው ጥልቅ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ታሪክና እንዲሁ የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ታሪክ እውቀት ከዚያ ከነበረው ዘመን ይልቅ ዛሬ ተፈጥሮን ማቀብ ያለው አንገብጋቢነት ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸው ያረጋግጥልናል። የእግዚአብሔር ክብር መግለጫ የሆነውን በውስጡ ክብር ለእግዚአብሔር የሚለው የውዳሴ መዝሙር የሚያዜመው ተፈጥሮ ማቀብ የእግዚአብሔር ክብር ማወጅ ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲያወድስ የሚያነቃቃ ጥሪ ነው እያስተጋቡ ያሉት ብለዋል።
ቅዱስ ዮሲየፍ ቅድስት ድንግል ማርያምን እንደተንከባከበ ሁሉ ባሎች ሚስቶቻቸውን ሚስቶችም ባሎቻቸውን እንዲሁም ወላጆች ልጆቻቸውን መንከባከብ ይኽም ማቀብ ገዛ እራስን ማቀብ መንከባከብ ከክፋት መንፈስ ገዛ እራስን ማግለል ማለት ነው። በብዙ ሚሊያርድ የሚቆጠረው የቆሻሻ ውኃ እንጥብጣብ ንጹሕ ውቅያኖስ አይሆንም፣ ስለዚህ በብዙ ሚሊያርድ የሚገመተው እንክን ያለው ልብ ሰብአዊነትና ንጹሕ ተፈጥሮ እያጸናም፣ ማቀብና መንከባከብ የሚለው ቅዱስ አባታችን የሚጠቀሙበተ ቃል ተፈጥሮን የምንጠቀምበት ነገር ሁሉ ማቀብንም ጭምር ያሰማል፣ ስለዚህ ተጠቅሞ መጣል ልማድ ያደረገው የበለጸገው ዓለም በሁሉም ዘርፉ ማቀብ የተሰኘው ቃል የዘነጋ ከማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ መዝገበ ቃላት ቃሉን ጭምር የሰረዘ ነው የሚመስለው ብለዋል።
አባ ካንታላሜሳ ባለፈው ጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም. ለካህናት ሱባኤ ስብከት ባቀረቡበት ወቅት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው የተመረጡት ከመመረጣቸው በፊት ብፁዕ ካርዲናል ቦርጎሊዮ እንደተሳተፉና እዛው በቅርብ እንዳወቁዋቸውም ገልጠው፣ ትህትና ጥልቅ እምነትና መንፈሳዊነት የሚኖር ብቻ ነው በቃልና በሕይወት ሊመሰክረው የሚችለው፣ ይኽ ደግሞ ቀድመው በእኚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሕይወት ያነበቡት ተግባር መሆኑ አባ ካንታላሜሳ ገልጠዋል። እውነተኛ ሰው ብቻ ነው ትህትናና የዋህነት ለመኖር የሚችለው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የትህትናና የየዋህነት ወንጌል ሰባኬ ናቸው ይኸንን መንፈስ እርግጠኛ ነኝ በቤተ ክርስቲያን በዓለምም እንዲኖር በቃልና በሕይወት ይመራሉ። ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ኵላዊ ቅዱስ ነው። ለተፈጥሮ ክፍት በመሆኑም ለሁሉም ሰው ዘር ለተናቁት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚኖሩት ሁሉ ቅርብ ብቻ ሳይሆን እነርሱ የሆኑትን ሆኖ የሚኖር ትሁትና የዋህ ቅዱስ ነው የእርሱ ስም የመረጡት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኸንን መንፈሳዊነት የሚኖሩ ቤተ ክርስቲያንን ምእመናን ውሉደ ክህነት ወደዚህ መንፈሳዊነት የሚመሩ ናቸው። ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ ኢየሱሳዊ ምልከት ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.