2013-03-25 13:31:37

ታሪካዊው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ግኑኝነት
“ወንድማማቾች ነን”


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከአገረ ቫቲካን ከሚገኘው ከሄሊኮፕተር ማረፊያ ተነስተው ሮማ አቅራቢያ ካስተል ጋንዶልፎ ወደ ሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንፃ በመሄድ እዛው ከሚገኙት ከቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ጋር መገናኘታቸው ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ የተካሄደው ታሪካዊ ተብሎ የሚነገርለት ግኑኝነት ጥልቅ አንዳዊ መንፈሳዊና ሰብአዊ መንፈስ የጎላበት ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ካስተል ጋንዶልፎ እንደደረሱ በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አቀባበል ተደርጎላቸው አብረው ጸልየው ምሳ ተቋድሰው ለ 45 ደቂቂ የግል ውይይት ካካሄዱ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከቅትር በኋላ ሁለት ሰዓት ከ 40 ደቂቃ ወደ አገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ መንበራቸው ተመልሰዋል።
በቅዱስ አባታችንና በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መካከል የታየው መተቃቀፍ በሁለቱ መካከል የቆየው ጽኑ ወዳጅነት ወንድማማችነት የሚያስተጋባ ከመሆኑም ባሸገር ታሪካዊነቱም በሁለት ማለትም በቅዱስ አባታችንና በልኂቅ ር.ሊ.ጳ. መካከል የተካሄደ ግኑኝንት በመሆኑም የተካሄደው ግኑኝነት በመላ ዓለም የመገናኛ ብዙኃን አቢይ ትኵረት የተሰጠው ሆኖ፣ ሁሉንም አስደንቀዋል።
በቅድሚያ ሁለቱ ካስተል ጋንደልፎ በሚገኘው ጳጳሳዊ ቤተ ጸሎት ለመጸለይ ሲገቡ በሁለቱ መካከል የታየው የትህትና መንፈስ እጅግ የሚያስደንቅ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ የቅድስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚገባቸው ልዩ የመጸለያ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቢጋብዙዋቸውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አይ ወንድምማቾች እኮ ነን በማለት ያለ ምንም ልዩነት በአንድ ላይ ጎን ለጎን በመሆን ተንበርክከው ለመጸለይ መርጠው ጸልየዋል። የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ግኑኝነቱ “እጅግ የላቀ ጥልቅ ውህደት” የታየበት እንደነበርም ገልጠዋል።
ቀጥሎ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መካከል በጳጳሳዊ የካስተል ጋንደልፎ ሕንፃ በሚገኘው ጳጳሳዊ ቤተ መዝገብ ውስጥ የተካሄደው 45 ደቂቃ ከፈጀው ግላዊ ግኑኝነት ቀደም ብሎ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅድስት ድንግል ማርያም የትህትና እናት ቅዱስ ምስል ገጸ በረከት በማቅረብ የትህትና እናት የተሰየመ የማርያም ቅዱስ ምስል ያለ አይመስለኝም ነበር ለእኔ አዲስ ነው። ይኽ ቅዱስ ምስል እንዳየሁ እርስዎን የጥልቅ እምነት ምሰሶ የበሳል ጥበብ መምህር የእምነት ምስክርነትዎትን ነው እንዳስታውስ ያደረገስኝ በማለት ሲናገሩ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. ክልብ ሲያመሰግኑ ታይተዋል።
የተካሄደው ግኑኝነት ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለመላ ዓለም እምነት ፍቅርና ተስፋ በቃልና በሕይወት የመሰከረ የውኅደት የአንድነት መንፈስ ምስክርነት መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.