2013-03-25 13:35:12

በዓለ ሆሣዕና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ


RealAudioMP3 በላቲን ሥርዓት ትላትና በዓለ ሆሳዕና መከበሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለበዓሉ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መርተው የሰጡት ሥልጣናዊ ጥልቅ ስብከትና አስተምህሮ የሁሉም ልብ የማረከ እንደነበር ሥነ ሥርዓቱን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል። ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት አለ ምንም ቀቢጸ ተስፋነትና ጨለምተኝነት የመስቀል ማአክልነት በማብራራት ከዚህ በዓል ጋር በተያያዘ መልኩም በኢጣሊያ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤት ክርስትያን ብሔራው የወጣቶች ቀን መሆንም ቅዱስነታቸው በማስታወስ ወጣት ለተስፋ ክፍት የሆነ ልብ ያለው መሆኑ በጥልቀት በማስረዳት ሁሉም ወጣት እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. በሪዮ ደ ጃነይሮ ለሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን እንዲሰናዱ በተለይ ደግሞ ዝግጅቱ ጥልቅ መንፈሳዊ ላይ የጸና ይሆን ዘንድ በማሳሰብ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ ማቅረባቸው ታማሮ ገልጠዋል።
በዚህ በሰሙነ ኅማማት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅማማትን በጥልቅ መንፈሳዊነትና በሕይወት እንድንኖረው በማሳሰብ፣ ለክርስቶስ ስቃይ ዕለት በዕለት በስቃይ በሚኖሩት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስቃይ ቅርብ በመሆን እነርሱን በመደገፍና በማጽናናት የሚኖሩትን የስቃይ ህይወት ተካፋዮች በመሆን እንድንኖረው ጥሪ አቅርበውልናል። የክርስቶስ ስቃይ ከወንድሞችና እህቶች ስቃይ ነጥሎ ማየቱ የኃሰት መንፈሳዊነት ምልከት መሆኑ ማስገንዘባችውም እዛው በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተሳተፉት ምእመናን ከሰጡት ምስክርነት ለመረዳት መቻሉንም ልእክት ጋዜጠኛ ታማሮ አስታውቀዋል።
እምነት አለ ቅዱሳት ምሥጢራት መኖር የማይቻል ነውና ሁሉም በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ዘወትር በመሳተፍ በሚሥጢረ ንስኃ በመሳተፍ ሊኖረው እንደሚገባው ቅዱስ አባታችን አስረድተው፣ እምነት ከቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ከማኅበረ ክርስቲያንና ከቤተ ሰብ ጋር የሚኖር ነው እንዳሉም ታማሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.