2013-03-22 14:05:49

የተኃድሶ አቢያተ ክርስቲያን፦ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ኃሴት ተስፋን ይሰጣል


RealAudioMP3 ዓለም አቀፍ የተኃድሶ አቢያተ ክርስትያን ውህደት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ መጋቤ ሰአትሪ ንዮሚ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ጅማሬ በተመለከተ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የተኃድሶ አቢያተ ክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እየኖረቸው ያለው ኃሴት ተካፋዮች ናቸው ካሉ በኋላ በእውነቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገዛ እራሳቸውን ሲገለጡ እርሱም የእግዚአብሔር ጸጋ አቃቢ ቢሉም፣ ነገር ግን ይኽ አቢይ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ ሥልጣን በትህትና በማገልገል የሚፈጸም መሆኑ ገልጠዋል። ሥልጣን አገልግሎት ነው ብለዋል። ዓለም በተለያዩ ችግር ውስጥ ተነክሮ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት እንደ እሳቸው ያለ መሪ ማግኘት መታደል ነው። ስለዚህ ስለ እሳቸው ከመጸለይ ማንም መቦዘን የለበትም ብለዋል።
የተናቁትን የተጨቆኑትን ድኾችን በጠቅላላ በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ተገለው ለሞኖር ለተገደዱት ሁሉ ድምጽ መሆናቸው ከወዲሁ ካስደመጡት ንግግር ለመገንዘብ ተችለዋል፣ ይኽ ደግሞ ለሁሉም ለአቢያተ ክርስቲያን ለምእመናን ጭምር አቢይ አስተንፍሶ ነው ካሉ በኋላ ትኅትናቸው የሚያስደንቅ ብቻ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ የሚያስተላልፈው መልእክትም ነው በማለት የሰጡትን ቃል ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.