2013-03-22 14:01:55

ኦርቶዶክሳውያን፦ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የእግዚአብሔር ጸጋ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከትላንትና በስትያ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን እንዲሁ የተለያዩ ሃይማኖቶች መንፈሳውያን መሪዎችን ተቀብለው ያሰሙት ንግግር በመንፈሳውያን መሪዎችና በአድማጭ ህዝብ ዘንድ የቀሰቀሰው አወንታዊ ስሜት አሁንም እተስተጋባ መሆኑ ይነገራል።
ቅዱስነታቸው በእነዚህ የተለያዩ ሃይማኖቶችና እንዲሁም በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል በአንዱ ስለ ሌላው በሚሰማው ኃላፊነት፣ በጋራ ለሰላምና ለእርቅ የመሥራቱ ፍላጎት መርህ በማድረግ የሚከናወነው የጋራው ውይይት ፈጽሞ እንዳይደበዝዝ አደራ ሲሉ፣ ቀደም በማድረግ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛን ተቀበለው ባሰሙት ንግግር፣ በተመሳሳይ መልኩ በጋራ መጓዝ ያለው አስፈላጊነትና እንዲሁ በጋራ ለመጓዝ ዝግጁ መሆናቸው እንዳረጋገጡ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ለቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ በኢጣሊያና በማልታ ሜትሮጶሊታ ሊቀ ጳጳሳት ዘርቮዝ ገናዲዮስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በተካሄደው ግኑኝነት የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛ ውኅደት መረጋገጥ የሚገባው ክርስቶሳዊ ፍላጎት ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት አንገብጋቢ መሆኑና ሁሉም አቢያተ ክርስቲያን በጋራ ያንን አንድ ይሆኑ ዘንድ የሚለው የጌታ ፍላጎት ለመከወን የሚያበቃ ትብብር መሠረት አብረው መጓዝ ይገባቸዋል በማለት ያሰመሩበት ሃሳብ በማስታወስ፣ ለውህደት የሚደረገው ጥረት ለድሆች ልዩ ትኩረት በሚሰጠው አገልግሎት በተለይ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ተከስቶ ባለው የኤክኖሚ ቀውስ ለተለያየ ችግር ተጋልጦ ለሚገኘው በድኽነት ለተጠቃው የኅበረሰብ ክፍል በማገልገል መገለጥ እንዳለበትም በተካሄደው ግኑኝነት ተገልጠዋል። ለተናንሽ ለተጨቆኑት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚሰቃዩት ቅርብ በመሆን መንፈሳዊ ግብረ ገባዊ ቁሳዊ ድጋፍ ማቅረብ የሁሉም ኃላፊነት ነው። በተለይ ደግሞ የአቢያተ ክርስቲያን ኃላፊነት መሆኑ መዘንጋት የለበትም ካሉ በኋላ፣ የቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው መመረጣቸው በእውነቱ የጌታ አሳቢነት የሚያጎላ ተግባር ሲሆን የእግዚአብሔር ፍላጎት ናቸው። በገጻቸው በሚያስደምጡት ቃል የሚታየው የሚሰማው ደስታ፣ ትህትና እና ዝግጁነት በእውነቱ በእሳቸው ዘንድ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ጉልበት ለሁሉም አስገርመዋል። የእግዚአብሔር ድጋፍና የሁሉም ጸሎት እንደማይለያቸውና ለአንድነት የሚደረገው ጉዞ እርቅ ወድማማችነት ሰላም መርህ በማድረግ እንደሚቀጥሉበተ የተረጋገጠ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው የእግዚአብሔር ጸጋ ናቸው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.