2013-03-22 14:11:18

ብፁዕ አቡነ ሮኬታ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዋኅነት ደንዳናውን ልብ ይለወጥ የሚል መልእክት አዘል ነው


RealAudioMP3 ዶስቶቭስኪይ “የዋኅነት የትሁት ፍቅር ጉልበት ወይንም ኃይል ነው” በማለት ይገልጠዋል። ስለዚህ የዋህነት በተናቁት ወይንም በትሁታን የሚገለጥና የሚኖር እሴት አይደለም። ይኸንን መሪ ቃል ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ የተልእኮ ሥልጣናቸውን በይፋ ለማስጀመር በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባስደመጡት ስብከት ገልጠውታል። ቸርነት የዋህነት የሚለው ቃል በቅርቡ “የየዋህነት ወይንም የቸርነት ቲዮሎግያ፣ ገና መታወቅ የሚገባው የብሥራት ቃል” በሚል ርእስ ሥር ለንባብ የበቃው ጥልቅ መጽሓፍ ደራሲ የፐሩጃ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ካርሎ ሮከታ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው።
ይኽ ቸርነት የዋኅነት የፍቅር ጉልበት መሆኑ በመታመን በዚሁ ርእስ ሥር በማስተንተን በመጸለይ ብዙ ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ምርምር ማድረግ ከጀምሩ ብዙ አመታት የሆናቸው ብፁዕ አቡነ ሮከታ ይላሉ፦ በውነቱ ቅዱስ አብታችን በዚህ ቃል ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ጥሪያቸውን ሲያጀምሩ በማየቴ ልቤ በኃሴት ሞልቶታል። እግዚአብሔር የዋህነት ሲሆን ይኽ የዋህነት ወደ መስቅል በመሄድ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ኢየሱስ ሁሉንም የሰውን ዘር በማቀፍ የገለጠው ክቡር እሴት ነው ብለዋል።
እግዚአብሔር ትህትና ነው። እኛ በእርሱ አምሳያና አርአያ የተፈጠርን ነን። ስለዚህ ከእርሱ በየዋህነት በትህትና ሌላውን ለማፍቀር መማር ይገባናል። ይኽ ማለት ደግሞ ገዛ እራሳችንን ሌላውን በመንከባከብ ማንም ካለ ማግለል ትንሹንም ትልቁንም ክፍለ ተፈጥሮ የሆነውን ሁሉ በማፍቀር መግለጥ መኖር እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው ብለዋል።
ተፈጥሮን አቅቦ መንከባከብ የሁሉም ጥሪ ነው። ስለዚህ በየዋህነት በቸርነት ማቀብና መንከባከብ ማለትን ያሰማል። ሁሉም የእግዚአብሔር ጸጋ በመሆኑ በቸርነት በትህትና በየዋህነት ተፈቅሮ መታቀብ አለበት። የሚወለድ ሕፃን በእናት ማሕጸን፣ በመጽሓፍ ቅዱስ ቸርነት የዋህነት የሚለው ቃል ሥርወ ቃሉ የአረማይስጥ ቋንቋ ሲሆን፣ አንስት ጾታ ያለው ትርጉሙም ማሕጸን ማለት ነው። ስለዚህ ትህትና ቸርነት የሚለው ቃል ከሕፃን ጋር የሚገናኝ ቃል ነው። በማሕጸንዋ ሕፃን ልጅዋ ያቀበችው እናት በእናት የዋህነትና ቸርነት የታቀበው ሕፃን መካከል ያለው ፍቅር እግዚአብሔር ነው። መጽሓፍ ቅዱስ አለ ምክንያት አይደለም እግዚአብሔር በእናት መልክ የሚገልጠው። ልክ ልጇን እንደ ምትወድ እናት እግዚአብሔርም ሕዝቡን ያፈቅራል።
ቅዱስ አባታችን የዋህነት የድካምነት ምልክት ሳይሆን የመንፈስ ጽናት መሆኑ በጥልቅ ገልጠውልናል። ጽኑ ቆራጥ የተረጋጋ መንፈስ ያለው ብቻ ነው የዋህና ቸር የመሆን በቃቱ የሚኖረው።። ካልሆነ ግን አስመሳይነት ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚለው ድንጋያማውን ልብ ወደ ሥጋዊ ልብ እንዲለወጥ የሚጠራ ቃል ነው ካሉ በኋላ የዋህነት ቸርነት ከምህረት ጋር የተቆራኘ ነው። ይኸንን ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዲሁም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሰውና ኃጢአት ለይተን መመለከት እንዳለብን በማስገንዘብ ኃጢአትና ኃጢአተኛን ለይቶ መመልከት የሚቻለው ከየዋህነትና ከቸርነት ከሚወለደው ምህረት ነው። ኃጢአተኛው ማፍቀር ኃጢአት ደግሞ መወገዝ አለበት።
ትሁታን የዋሆች ለመሆን አትፍሩ። በማለት ቅዱስ አባታችን ሲያሳስቡ፣ አለ ምክንያት አይደለም። የዋህና ቸር እግዚአብሔርን ያውቃል ምክንያቱም ቸርነትና የዋህነት እግዚአብሔር ነውና፣ የዋህነት ቸርነት የመላ ሰው ዘር መጻኢ ቁልፍ እንደሚሆን ይኸው ቅዱስ አባታችን በዚሁ ቃል መሠረት ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተልእኮአቸውን ሲጀምሩ በይፋ ገልጠውልናል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.