2013-03-21 09:30:23

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ በይፋ ተረከቡ ፡


እነሆ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና መጋቢት 19 ቀን እንደ ኤውሮጳ አቆጣጠር የርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ጅማሬ እና የሮም ጳጳስ በመሆን የመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ በይፋ ተረከብዋል ።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባለፈው ወርሀ የካቲት 11 ቀን እንደ ጎርጎርዮስ ዘመን አቆጣጠር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት በገዛ ፈቃዳቸው መንበሩ መልቀቃቸው የሚታወስ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እሳቸውን ለመተካት በብጹዓን ካርዲኖሎች መሰየማቸው አይዘነጋም ።
ይሁን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሁለት መቶ ሺ ህዝብ በተገኘበት በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ የርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ጅማሬ በብዙ ካርዲናሎች ጳጳሳት እና ካህነት ተሸኝተው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።
የ130 ሀገራት ርእሳነ ብሔራት መራህያነ መንግስታት የመንግስታት ወኪሎች በዚሁ በቅዱስ ጰጥሮስ የተካሄደው ሥርዓተ ቅዳሴ ተሳታፊ ሁነዋል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቅዱስ ጰጥሮስ ጨምሮ 266ኛ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንደሆኑ ይታወቃል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፡ እውነተኛ የቤተ ክርስትያን ብሎም የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስልጣን ደካሞችን ማገለገል እና ፍጥረትን መንከባከብ ነው። ቅድስነታቸው ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንድተሰየሙ ድሃ እና ለድሆች የቆመች ቤተ ክርስትያን እንደሚፈልጉ ማመልከታቸው አየዘነጋም።
የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዋነኛ ስራ የእግዚአብሔር ህዝቦች መንከባከብ ደካሞችን ማገልገል እንደሆነ ርእሰ ሊቃነ ጳጳት ፍራንሲስ በስብከታቸው ላይ ተናግረዋል።
በዚሁ ምቹ የአየር ጸባይ በተካሄደው መሥዋዕተ ቅዳሴ ከብጹዓን ካርዲናሎች ከብጹዕ ካርዲናል ቱራን እና ከብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ አንገታቸው ላይ የሚያደርጉት ሞጣህደ ክሳድ የዓሳ አስጋሪ ቀሌቤት እና በትረ ኖልዎ ተቀብለዋል።ትናትና የቅዱስ ዮሴፍ ዓመት በዓል በመኖሩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቅዱስ የሴፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት አስታውሰዋል።
ቅዱስ ዮሴፍ ጠባቂ እናየእግዚአብሔርን ቃል ያዳመጠ ቅዱስ መሆኑ አስገንዝበዋል።የእግዚአብሔርን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ከቅዱስ ዮሴፍ መማር ግድ ይላል ያሉት ቅድስነታቸው የክርስትና የጥሪ ማእከል ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ነግረዋል።በማያያዝ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወታችን አካል ነው ከክርስቶስ በክርስቶስ ለክርስቶስ መጓዝ አለብን ብለዋል ።
ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ አሲሲ ጠቅሰው ፍጥረትን ሁሉ መንከባከብ የፍጥረት ቁንጅና ማድነቅ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ሁሉ መከበር ማክበር እንደሚገባ የምንኖርበት አከባቢ መጠበቅ እንደሚገባም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አመልክተዋል።
በማያያዝ ሕጻናት አረጋውያን ደካሞች መንከባከብ እና መውደድ ክርስትያናዊ ባህል እንደሆነም ነው ቅድስነታቸው ያስገነዘቡት ።በዚሁ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ጅማሬ የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት እና ክርስትያን ያልሆኑ ሃይማኖቶች መሪዎች ከ130 የሚበልጡ ሀገራት ርእሳነ ብሔራት መራኅያነ መንግስታት እና የመንግስታት መሪዎች የተገኙ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የመንግስታት መሪዎች በማስመልከት ፡ ክቡራት እና ክቡራን የኤኮኖሚ የፖሊቲካ እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ተጠሪዎች የእግዚአብሔር የሥነ ፍጥረት እቅድ እንዲጠበቅ እና እንዲከበር ተማጽነዋል።
በመጨረሻም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚች ጨለማ የሚታይባት ዓለማችን ብርሃን እና ተስፋ መስጠት የሁሉም ግዴታ መሆኑ አሳስበዋል።በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍርንሲስ እውነተኛ ሥልጣን አገልግልት መስጠት መሆኑ በዕለቱ ያሰሙት ስብከት በትዊተር @pontifex ተሰራጭተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ከቀትር በኃላ የቅዱስ ዮሴፍ ዓመተ በዓል በመሆኑ እና የቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት የጥምቀት ስማቸው የሴፍ በመሆኑ ደውለው ማነጋገራቸው እና ላበርከቱት ሐዋርያዊ ኖልዎ በስማቸው እና በቤተ ክርስትያን ስም ማመስገናቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አመልክተዋል።የቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክትም አዲስ ለተሰየሙት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መልካም ርእሰ ሊቃነ ጳጳስና ተመኝተው በጸሎት አተጠጋባቸው መሆናቸው እንድገለጡላቸው መግለጫው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.