2013-03-20 17:49:57

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእህትማሞች አብያተ ክርስትያንና የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ተቀብለው ሲያነጋግሩ ያቀረቡት ቃል፤


ውድ ወንድሞችና እህቶች ፣ በመጀመሪያ ከልብ የመነጨ ምስጋናና ሰላምታዬን ወንድሜ አንድሬያ ያላችሁን በመድገም በድጋሜ በጣም አመሰግናለሁኝ ።
በዛሬው እለት ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ጋር መገናኘቴ በጣም ለየት ያለ ደስታን ሲሰማኝ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተጠሪዎች የኦርቶዶክስ፣ የምስራቅ ኦርቶዶክስና የምዕራብ አውሮፓ የቤተክርስቲያን ጳጳሳትን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ሳቀርብ፣ እናንተም ከኔ ጋር ለመካፈል በዛሬው እለት የምጀምረውን የሮማ ሊቀ ጵጵስና የሐዋሪያው ጴጥሮስ ተከታይና እረኝነትን ለማገልገል ከኛ ጎን በመሆናችሁ ነው፡፡
ትላንት ጠዋት በተካሄደው ስርዓተ ቅዳኤ ላይ በእናንተ ልዑካኖች አማካኝነት ሕብረተሰቦቻችሁ በመንፈሳዊነት ሕብረት መሳተፋቸውን ሲገልፅ፣ በተካሄደውም የዕምነት መግለጫ ከምን ግዜም የበለጠ በጸሎት አማኞች በሙሉ በሕብረት በክርስቶስ አንድነት በመሰባሰብ እግዚብሔር አባት ላለው እቅድ የኛም እውነተኛ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው።
ዘንድሮ የሐዋሪያዊ እረኛ ስራዬን የምጀምረው ከኔ በፊት በነበሩት የተከበሩት አባታችን ቢኔዲክቶስ 16ኛ፣ ዘንድሮ ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዓመቱን ለመንፈስ ቅስቀሳ የዕምነት አመት ብለው በሰየሙት መሠረት እኔም ምኞቴ ከዚሁ በመነሳት የዕምነት ዓመት ጉዞውን በማበረታታት መቀስቀስ ነው። አባታችን ቤኔዲክቶስ 16ኛ ባለፈው በተካሄደው 50ኛው የ2ኛው ቫቲካን ጉባኤ እያንዳንዱ ክርስቲያን የግል ጉዞውን የሚገልጽበት በግሉ ከክርስቶስ እየሱስ ጋር ያለውን ግንኙነት የእግዚብሔር ልጅ እኛን ለማዳን ሞቶ በትንሣኤ መነሳቱን ነው። ይህ ዘላለማዊ ሃብት የሆነውን ትንሣኤውን መግለፅ ለዘመናችን ሰዎች አስፈላጊ ሲሆን የቫቲካን ጉባኤም ዋና ነጥብ ይህ መልዕክት ነው።
ሌላው አብሬያችሁ መርሳት የማልፈልገው 2ኛው የቫቲካን ጉባኤ ለሃይማኖቶች አንድነት የተጫወተውን ሚና ነው። ማስታወስ የምፈልገው ነፍስ ሔር ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ በቅርቡ በሞት ሲለዩ 50ኛ ዓመት ሲከበር ለ2ኛው የቫቲካን ጉባኤ ምርቃት ላይ ያሉትን “ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሃላፊነቷ ክርስቶስ በመጨረሻው እራት ላይ የጸለየውን ጸሎት “አንድነት” እንዲሆን ዘንድ ማስተማርን ነው።
አዎን ውድ ወንድሞችና እህቶች ሁላችንም በውስጣችን በአንድነት እንደተሳሰርን የመጨረሻውን የክርስቶስ እራት ለአባቱ ለለመነው ጸሎት ይሰማን። ለሰማያዊው አባታችን በሚስጥረ ጥምቀት የተቀበልነውን የእምነት ጸጋ ስጦታ በነፃነት፣ በደስታና፣ ድፍረት እንመስክር። ይህ ነው በተለይም ለኛ ክርስቲያኖች ለአንድነታችን እንድናገለግል ከተፈለገ ተስፋችን ሳንከፋፈል፣ ሳንፈካከር ስንሰራ ነው። ለሰማያዊው አባታችን በሐሳቡ፣ ቃሉና ተግባሩ ታማኞች ከሆንን ወደ አንድነት ጉዞ እንደርሳለን።
ለአይሁዳዊያን ተጠሪዎችም በመንፈስ አንድነት የተሳሰርን ሲሆን ይህም በ2ኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው የሚስጥረ ድህነት በጥንት አባቶች አባቶች ሙሴና ነቢያቶች እንደሚገኝ ነው። እዚህ በመገኘታችሁ በጣም ሳመሰግን ለወደፊትም በወንድማማችነት ምክር በመወያየት እንደ ቀድሞው ብዙ ፍሬዎችን እናፈራለን።
በመጨረሻም እዚህ የተሰበሰባችሁን የተለያዩ ሃይማኖትና ባሕል ተጠሪዎችን በሙሉ ሳመሰግን በተለይም ሙስሊሞችን እነሱ ለአንድ አምላክና ይቅር ባይ መሃሪ ብቻ በጸሎት ስለሚያምኑ ነው። ሁላችሁም ስለተገኛችሁ በጣም ሳመሰግን በእናንተ መገኘት ሁላችንም በፈቃደኝነትና በሕብረት ለሕብረተሰቡ አንድነትና ለመስራትና ለማደግ እንደምንፈልግ በተጨባጭ አየዋለሁኝ።









All the contents on this site are copyrighted ©.