2013-03-20 17:54:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለቦነስ አየረስ ያስተላለፉት የተለፎን መልእክት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በአርጀንቲና በቦነስ አየረስ ለተሰበሰቡና ምእመናን በተለፎን መልእክት አስተላልፈዋል፣ ምንም እንኳ ብዙ ውሉደ ክህነትና ምእመናን እስከ ሮም ለመምጣትና በዚሁ ልዩ ቀን ከእርሳቸው አብረው ሊጸልዩ ልዩ ፍላጎት ቢኖራቸው ቅዱስነታቸው ግን አስቀድሞ በቦነስ አየረስ በሚገኘው የር.ሊ.ጳ ሐዋርያዊ እንደራሴ ኑንስዮ አማካኝነት ማንም ጳጳስ ወይም ም እመን እስከ ሮም ለመምጣት አይሞክር ብቻ እዛ ላይ ሁናችሁ በጸሎት እርዱኝ፣ የመንገዱ ርዝመት የጉዞው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ እስከ ሮም ለመምጣት ያቀዱ ሁሉ ለድሆችና መስኪኖች መባ እንዲሆን የተቻለውን ያበርክት በማለት ስለከለከልዋቸው፤ ከቦነስ አየርስና ከመላው አርጀንቲና በመንፈስ ከቅዱስነታቸው ጋር ለመተባበር በማዮ አደባባይ ተሰብስበው ሲጸልዩ ር.ሊ.ጳ በስልክ ይህንን መልእክት አስተላልፈዋል፣
በአደባባይ እንደምትገኙ አውቃለሁ፤ ስለ ጸሎታችሁ አመሰግናለሁ” ሲሉ መላውን ሌሊት ሲጠባበቁና ሲጸልዩ የነበሩ ም እመናን በአርጀንቲና ሰዓት አቆጣጠር የሌሊቱ 3፡30 ነበር፣ በአደባባዩ የንበሩ በብዙ የሚቆጠሩ አዛውንቶች ወጣቶች ቤተ ሰቦች ከሕጻኖቻቸው ጋር የሊቀ ጳጳሳቸውን ድምጽ ባልጠበቁበት ጊዜ ሲሰሙ የተሰማቸው ደስታ እጅግ ታላቅ ነበር፣ በቦታው የተገኙ ጋዜጠኞች እንደገለጡት ከሆነ በካተድራሉ እና በአደባባዩ የተለያዩ ታላላቅ የቢድዮ ሰሌዳዎች ተዘጋጅተው በመንበረ ጴጥሮስ የሚካሄደውን ቅዳሴ በቀጥታ እንደተከታተሉትና በታላቅ መንፈሳዊነት ብሥር ዓቱ እንደተሳተፉ ገልጠዋል፣
ቅዱስነታቸው በስልክ መናገር ሲጀምሩ ሊገለጥ የማይቻል ዝምታ እንደሰፈነና ቅዱስነታቸውም “አንድ እርዳታ የምጠይቃችሁ አለ፤ እባካችሁ ሁላችን አብረን እንጓዝ” ካሉ በኋላ፤
“አንዱ ለሌላው እንሰብ፣ መጥፎ ነገር በማድረግ ለሌችን እንዳትጐዱ ይሁን፤ ቤተ ሰቦቻችሁን ጠብቁ፤ ተፈጥሮን ጠብቁ፤ ሕጻናትን ተንከባከቡ፤ አዛውንቶችን እርዱ፣ ጥላቻ አይኑር፤ ቅናትን አወግዳችሁ አንድን እንዳታሳዝኑ አደራ፣ እርስ በእርሳችሁ አንዱ ሌላውን ለመከላከል ብዙ ውይይት ይኑራችሁ፤ ሁሌ መሓሪ በሆነውና ምሕረት እየሰጠ ችግራችሁን ወደሚረዳ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም አብዝታ ትባርካችሁ፣ እጅግ ርቆ ያለው ሆኖም ግን እጅግ ለሚወዳችሁ ይህንን ጳጳስ አትርሱ፤ በጸሎት አስታውሱኝ” በማለት የስልክ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.