2013-03-18 13:38:15

ደስታና ልብን የሚማርክ የሞቀ አቀባበል ከምእመናን ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ


RealAudioMP3 ትላትና እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ሃና ቁምስና ትንሿ ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው እንዳበቁ በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተሳተፉን ሁሉ አንድ በአንድ ከውጭ በር ቆመው ሰላምታን ሲያቀርቡም ሆነ በዚያ ወደ አገረ ቫቲካን ወደ ሚያስገባው የቅድስት ሃና በር መግቢያ በመሄድም እዛው ከነበሩት ሁሉም ጋር በመገናኘት ያሳዩት ቅርበት በእውነቱ የሚያስደንቅ ሲሆን፣ ምእመናን ለቅዱስነታቸው ደስታቸውን በመግለጥ ልብን የሚማርክ የሞቀ አቀባበል በማቅረብ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያላቸውን ፍቅር መግለጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሳልቫቶረ ሳባቲኖ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ቅዱስነታች በመቀጠልም እኩለ ቀን ከሐዋርያዊ መንበራቸው ካለው መስኮት ሆነው ብለው ባሳረጉት ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔርና ባሰሙት የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ከውስጥና ከውጭ በመጡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን ጭምር የተከታተለው ምእመናንና ሕዝብ ስፍር ቁጥር እንዳልነበረውም ይንገራል።
በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተገኙት ምእመናን እግዚአብሔር አብ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ አማካኝነት ወደር የማይገኝለት ጸጋውና ፍቅሩን ገልጦልናል፣ ሁሉም የእሳቸው አስተምህሮና የሚያቀርቡት ሥልጣናዊ ትምህርት በጸሎት በመተርጎም እግብር ላይ ያውለውም ዘንድ የሁሉም ምኞት መሆኑ ብዙዎቹ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሲያበክሩ፣ ምህረትን ለመጠየቅ አትፍሩ እግዚአሔር እኛን ይቅር በማለትም ሆኖ የምህረቱ ጸጋ በመለገስ ፈጽሞ የማይደክምና የማይሰለች አምላክ ነው፣ ምህረትን የመጠየቁ ድካም ከእኛ ነው በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያሉትን ሃሳብ የሁሉን ልብ እንደማረከም በጸሎቱ የተሳተፉት ምእመናን በስጡት ቃለ መጠይቅ አረጋግጠዋል።
በቅድስት ሃና ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገውም እንዳበቁ ለምእመናንን አንድ በአንድ ሰላምታ በማቅረብ፦ “የእናንተ ጸሎት ያስፈልገኛልና ስለ እኔ ጸልዩ” በማለት አንዱ ለሌላው የመጸለዩ ክርስቲያናዊ ተግባር የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ አስገንዝበዋል። የሕዝብ የመእመናን የሁሉም እረኛና አባት መሆናቸው ካሳዩት አባታዊ ፍቅር ለመገንዘብ መቻሉንም ምእመናን ሲመሰክሩ፣ ትሁት ነጻ የመንፈስ ቅዱስ ብርታት የተሞሉ መሆናቸም ምእመናን ይናገራሉ። ስብከታቸው አስተምህሯቸው መልእክታቸው ልብን የሚነካ ቀልብን የሚስብ ሁሉም ሊረዳው የሚችል ብቻ ሳይሆን በሚያሰሙትም መልእክት የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሚሰማም በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተሳተፉት ምእመናን ይናገራሉ።







All the contents on this site are copyrighted ©.