2013-03-13 17:57:03

ጌታ መልካም እረኛ እንዲሰጠን ዘንድ እንጸልይ፣


ይህንን ያሉት የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ ትናንትና አዲስ ር.ሊ.ጳ ለመምረጥ በመንበረ ጴጥሮስ ባሳረጉት ቅዳሴ ባደረጉት ስብከት ነው፣
እውነትም ባለነው የመሸጋገር ጊዜ ጌታ ለቤተ ክርስትያኑ መልካም እረኛ እንዲሰጠን መጸለይ የክርስትያኖች ሁሉ ተግባር መሆን ያለበት ነው፣
በመንበረታቦቱ ከብፁዕነታቸው ጋር ር.ሊ.ጳ ሊመርጡና ሊመረጡ የሚችሉ ከመላው ዓለም የተሰበሰቡ 115 ካርዲናሎች እና ሌሎች ካርዲናሎች ተሳትፈዋል፣ ብዙ ቤተ ክህነትና ም እመናንም በቅዳሴው ተሳትፈዋል፣
ብፁዕነታቸው በስብከታቸው መግቢያ ላይ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛን ሲያመሰግኑ በቤተ ክርስትያን የነበሩ ረዘም ላለ ግዜ በብርቱ ስሜት አጨብጭበዋል፣
የቅዳሴው መክፈቻ መዝሙር “እግዚአብሔር የሕዝቡ ኃይልና በኢየሱስ ክርስቶስ የድኅነቱ ዋስትና ነው” የሚል ስለነበር ብፁዕነታቸው በስብከታቸው የእግዚአብሔር ምሕረት ለዘለዓለም እዘምራለሁ የሚለውን መዝሙረ ዳዊት በዕለቱ በቅዱስ ጴጥሮስ መቃብር ላይ እንደገና በመዘመር እንደ ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔር ለቤተክርስትያኑ ስላደረገው እንዘምርለታለን፣
በዛሬው ዕለት እኛም በሰማያት ያለው ለእግዚአብሔር አባታችን ቤተ ክርስትያኑን በፍቅሩ ሁሌ ስለረዳት በተለይ ደግሞ በር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ስለሰጠን መታደስና መሪነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በዘማሪው ላይ በነበረው መንፈስና ስሜት “የእግዚአብሔር ምሕረት ለዘለዓለም እዘምራለሁ” እያልን ምስጋና እናቅርብ፣ ካሉ በኋላ የዕለቱን ቃለ እግዚአብሔር በመመርኰዝ መልካም እረኛ በፍቅር ተገፍቶ ስለ በጎቹ ሕይወቱን የሚሰጥ ነው፣ ጌታ እንዳለውም ሕይወትህን ለጓደኞች አሳልፎ ከመስጠት የላቀ ፍቅር የለም፣
እንደ እውነቱም ከሆነ የቤተ ክርስትያን እረኞችን ለሰውል ልጆችን ለማገልገል ከግዝያዊ ሥጋዊ የምሕረትና የፍቅር ሥራ እስከ ከፍተኛው ለሰው ልጆች የእምነት ብርሃንና የክርስቶስ ጸጋ ኃይል የማደል አገልግሎት ለመስጠት የሚገፋፋቸው ይህ ፍቅር ነው፣ ሲሉ የእረኝነት የእግዚአብሔር ምሕረትና ፍቅር መተሳሰር ከገለጡ በኋላ ስለ ቤተ ክርስትያን አንድነት አስፈላጊነት አብራርተው ይህ ግን አንድ የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስትያንን ለማገልገል እንደ የሰውነት አካላት የተለያዩ ስጦታዎችና ጸጋዎች እንዳሉም ባለ መዘንጋት ብዙነት ያቀፈ በፍቅር የተሳሰረ አንድነት እንደሚያስፈልግ ገልጠዋል፣
በመጨርሻም እግዚብሔር መልካም እረኛ እንዲሰጠን በኃይል መጸለይ እንዳለብን በመማጠን ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.