2013-03-13 22:21:14

የጵጵስና ታሪክ በቅዱስ መጽሓፍ


የቤተ ክርስትያን አስተዳደር በጉባኤ መልክ ሊንቀሳቀስ የጀመረው በመጀመርያው ክፍለ ዘመን በግብረ ሐዋርያ ም ዕራፍ 15፤14-17 ተመልክቶ እንደምናገኘው ሐዋርያ ያዕቆብ “እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል። ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ። ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።”
እንዲሁም ወንጌላዊው ሉቃስ ጌታ ኢየሱስ “እኔ እንደ አገልጋይ በመሃከላችሁ እገኛለሁ” (22፡24) በማለት የገባውን ቃል በር.ሊ.ጳ እና በአበው አማካኝነት ሁሌ መካከላችን እንደሚገኝ ያረጋግጥልናል፣ ቤተ ክርስትያን አለ ጴጥሮስ የኢየሱስ መሆን አትችልም፤ ምክንያቱም ጌታ ራሱ አንተ አለት ነህ በዚሁ አለትም ቤተ ክርስትያኔን አቆማለሁ ባለው መሠረት ነው፣ ጴጥሮስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር በመሆን የተቀሩትን አሥራ አንድ ይመራል፣ እርሱ የውህንደትና አንድነት መገናኛ ነው፣ የሕዝበ እግዚአብሔር እረኞች ሁሉ ሰበሳቢ እና መሪ ነው፣ በዚሁ ዋናው እረኛ በመሆን የሚታይ ምልክትና ምሥጢር በመሆን በመላው የቤተ ክርስትያን ታሪክ አንዱ ሌላውን ሲተካ እስከ ዘመናችን ደርሰዋል፣ ስለዚህ ቅ.ጴጥሮስ ሁሌ ከሌሎቹ ጋር በኅብረት ሌሎችም በእርሱ ዙርያ ሆነው ቤተ ክርስትያንን ይመራል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.