2013-03-08 15:07:38

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፦ “በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ በምድር በሚኖረው በአንድ በአዲስ ሰብአዊነት ማመን ማለት ነው”


RealAudioMP3 በዚህ ቤተ ክርስቲያ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣን ክፍት የመሆን ሁኔታ እየኖረች ባለችበት የሽግግር ወቅት በአቢይ የመጠባበቅ መንፈስና እንዲሁም ብዙዎች የሚያቀርቡት ስለ ጉዳዩ የሚመለከቱ አበይት ጥያቄዎች የተስፋ አንገብጋቢነትና ክቡር ዋጋ የሚያበክር ነው። ተስፋ እግዚአብሔር እቅዶቹን በዚህ በተከፈተው አዲስ ወቅት እንደሚከውን ወይንም ገቢራዊ እንደሚያደርግ ለእርግጠኛነቱ እማኔ ማለት ነው። ስለ ተስፋ በተመለከተ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ “Spe salvi-በተስፋ ድነናል(የዳነው በተስፋ ነው)” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክትና እንዲሁም ባለፉት በስምንቱ ዓመታት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናዊ አስተምህሮአቸውን መልስ ብለን ስንዳስስ፦ እ.ኤ.አ. የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ባቀረቡት ረቡአዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ “ኢየሱስ በመጨረሻ በሞት አፋፍ ላይ እያለ ሁለ መናውን በእግዚአብሔር እጅ አሳልፎ በእነሆኝ ሲያኖር፣ በዚህ ተግባር ለእኛ ያስተላለፈው መልእክት ይኽም በማንኛው ከባድና አቢይ ፈተና ዘንድ ብንገኝም ስቃይ አቢይና እጅግ ጥልቅ ቢሆንም ቅሉ ከነዚያ ከፈጠሩን ከደገፉን በመላ ህልውናችን ከሚሸኙን ከእግዚአብሔር እጆች ውጭ አንወድቅም ምክንያቱም እጆቹ ማለቂያና ወደር በሌለው በታማኝ ፍቅሩ የሚመሩ መሆናቸው በጽናት በማረጋገጥ ይኽንን እማኔ ነው ያካፈለን” ያሉትን ሃሳብ እናገኛለን።
ለእግዚአብሔር የተሟላ ሥፍራ መስጠት ለክርስትያን ጭምር ከባድ ነው። ይኽ ደግሞ ከእምነት ጋር የተቆራኘ ጉዳይ ሲሆን ስለዚህ፦ “በእግዚአብሔር ላይ የጸናው ተስፋችን በአንድ ተራ ሃይማኖተኛነት በሚሰጠው የተስፋ ትርጉም አዘል ወይንም በአንድ ጭፍን በሆነ ነሲባዊ መንፈስ በዕድል የተወሰነ ዕጣ ወይንም ፍራጃ ላይ የጸና እምነት መግለጫ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያዳግም ሁኔታ በሙላትና በተረጋገጠ ሁኔታ በገለጠው እኛን የፍቅርና የሕይወት ወደ ሆነው መንግሥቱ ሊመራን ፍቃዱ ከሰው ጋር መሆንን የሚሻ የሰውን ገጠመኝ በሚካፈል እግዚአብሔር ላይ እንታመናለን። ይኽ አቢይ ተስፋ በዕለታዊ ሕይወታችን የሚያነቃቃና እንዲሁም ሰብአዊ ተስፋችንን የሚያርም ነው” ሲሉ እ.ኤ.አ. ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባስደመጡት አስተምህሮ እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ያ ሰብአዊ ተስፋዎችን የሚያርመው አቢይ ተስፋ መሠረት በማድረግ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ባስደመጡት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ፦ “…ክርስትያናዊ ተስፋ ከተገባውና ትክክለኛ ከሆነው የሰው ልጅ ከሚጠባበቀው ማኅበራዊ ፖሊቲካዊ ነጻነት ልቆ የሚሄድ ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ከእግዚአብሔር የሚመጣው ሆኖም በዚህ በምንኖርበት ምድር በጌታ መንፈስ ፍሬያማ እንድትሆን ገዛ እራሷን ፈቅዳ ስታቀርብ በእርስዋ ላይ ተዘርቶ የሚያፈራ አዲስ ሰብአዊነትን አስጀምረዋል” እንዳሉም ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ በሌላው ረገድ አንድ ክርስቲያን ለገዛ እራሱ ብቻ ተስፋ የሚያደርግ ሳይሆን ተስፋ ሲያደርግ ለሌልች ጭምርም መሆኑ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ባስደመጡት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ፦ ተስፋ ማድረግ ማለት ሙሉ በሙሉ በእምነት አመክንዮ ዘንድ በመግባት በእግዚአብሔር ማመን በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ማመን፣ በተመሳሳይ መልኩም ለእግዚአብሔር መንግሥት ግንባታ ተግቶ መሥራት ማለት ነው። ሰላምና ፍትህ በእርግጥ ከእግዚአብሔር የሚሰጡ ጸጋዎች ቢሆንም ቅሉ ሰው እነዚያን ጸጋዎች ለመቀበል ዝግጁና መልካም ዘር የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል ለማስተናገድ የሚችል መልካም መሬት ሆኖ እንዲገኝ የሚል ቅድመ ሁኔታ የሚጠይቅ ነው” እንዳሉ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.