2013-03-07 08:56:20

ፓኪስታን፦ የእምነት ዓመት


RealAudioMP3 የእምነት ዓመት ካቶሊካዊው እምነት ዳግም ለይቶ ለማወቅ ለመገንዘብ እምነትን በጥልቅ ዳግም ለማደስ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በጥልቀት ለማወቅ በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል በርትቶ ለመንቀሳቀስ ከሚሰጠው አቢይ ድጋፍ ባሻገር አሸባሪነትና አመጽ ለመቅረፍ ለሚደረገው ጥረት መሠረት መሆኑ በዚህ በተገባው የእምነት ዓመት ምክንያት በፓኪስታን ላሆር ከተማ በተካሄደው ዓውደ ጥናት የላሆር ከተማ ሐዋርያዊ መስተናብር ብፁዕ አቡነ ሰባስቲያን ፍራንሲስ ሻው ባሰሙት ንግግር ማብራራታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በዚህ የተለያዩ የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ካህናት ደናግል ዓለማውያን ምእመናን በተሳተፉበት ዓውደ ጥናት የቤተ ክርስቲያን መሠረታዊው የእምነት ትምህርት ለሰላምና ተከባርቦ ለመኖር ለሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ መርህ መሆኑም ንግግር ያሰሙት የላሆር ሰበካ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ አባ በርናርድ ኢናያት ገልጠው፣ ቅዱስነታችው ልኂቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ የእምነት ዓመት ሲያውጁ እንዳሳሰቡትም ለዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጭምር መሠረት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፣ እምነት የሚኖር የሚመሰክር መሆን አለበት እንጂ በግል ሕይወት ብቻ የሚታጠር መሆን የለበትም ካሉ በኋላ፣ በሰዎች መካከል ተከባሮ ለመኖር እንዲቻል ለሚያደርገው ጥረት የሃይማኖት ነጻነት ማክበር ወሳኝ ነው። አለ ሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ ማኅበራዊ ሰላም ለማረጋገጥ አይቻልም እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.