2013-03-07 08:51:33

የመላ አፍሪቃና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ


RealAudioMP3 በአክራ የመላ አፍሪቃና የማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ፖሊቲካ ማአክል ያደረገ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት ንግግር ያስደመጡት የአክራ ሊቅ ጳጳሳትና የዚህ የመላ አፍሪቃና የማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ የገንዘብ ሃብት ተቆጣጣሪ ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ካብሬል ፓልመር ቡክለ አፍሪቃ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ ለሚደቅነው ተጋርጦ በተገባና በተዘጋጀ እንዲሁም በነቃ ብቃት ተጋፍጣ በመወጣቱ ረገድ የተዋጣለት ቆራጥ ሚና የመጫወቱ ኃይል ታጎለብት ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ ይኽ እ.ኤ.አ. መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. የተከፈተው ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. እስከ መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚዘልቅ መሆኑም ሲታወቅ፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለማረጋገጥ፣ አመጽ ድኽነት የተፈጥሮ የአየር ንብረት ብከላ የመሳሰሉት ኅብረትሰብ የሚያጎሳቁሉ ከሙሉ ብልጽግና የሚያገለው ተጋርጦ ለመቅረፍ የሚያስችል የተዋጣለት ተገቢ ብቃት ያለው መሥተዳድር ማረጋገጥ አስፈላጊነቱ ማብራራታቸው ተገልጠዋል።
ከመላ ዓለም ድኽነት ለመቅረፍ ታልሞ የተወጠነው ሚለኒዩም የልማት እቅድ ለማረጋገጥ የተደረገው የልማት ጉዞ ሲጤን እንደታለመው በሙላት ይረጋገጣል ለማለት እንደማይቻል ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ ፓልመር ቡክለ ቤተ ክርስቲያን ለተሟላ እድገት እርሱም ሰብአዊና ቁሳዊ እድገት ለማረጋገጥ የምትሰጠው ሕንጸት ለአዲሲቷ አፍሪቃ መረጋገጥ ያለመ መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ እድገት በተመለከተ ዓላማ ቅድሚያ መሰጠት የሚገባው እቅድ ለይቶ በዓለማዊነት ትሥሥር ሥር የሚነበብ መሆን አለበት ብለዋል። የልማት እቅድ ኵላዊ የሰብአዊ መብትና ክብር ላይ የተመሠረተ የሁሉም ተሳትፎ የሚጠይቅና የሚኖርበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መረጋገጥ ላይ ያለመ፣ የግላዊና ማኅበራዊ ነጻነት ብሎም የሁሉም ብሄሮችና የሰዎች የባህሎች የሃይማኖቶች እኩልነት ማመንና ማክበር ተቀባይነት ላለው የልማት እቅድ መረጋገጥ መሠረት መሆኑ ካብራሩ ካሉ በኋላ በዚህ ረገድ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳት ትምህርት የሚሰጠው ድጋፍ ብሎም ያለው አስፈላጊነት እንዲሁም ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቤተ ክርስትያን በአፍሪቃ በተሰየመው ቀጥለውም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የአፍሪቃ ቃለ ማሕላ በሚል ርእስ ሥር የደረሱዋቸው ሐዋርያዊ ምዕዳኖች አማካኝነት የሕይወት ባህል ጥበቃ ይኽ ደግሞ ለድኽነት የሚዳርግ ሳይሆን ድኽነት ለመቅረፍ መሠረታዊ መፍትሔ ከመሆኑም ባሻገር የሁሉም ጥቅም ለማረጋገጡ ባህል ድጋፍ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.