2013-03-07 11:50:33

የሐዋርያት ውህደትና አንድነት የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ቅድመ ሁኔታ ነው፣


አስቀድሞ እንደተገለጸው ብፁዓን አበው ፓርትያርኮችና ካርዲናሎች አዲሱን ር.ሊ.ጳ ለመምረጥ መንፈስ ቅዱስ እንዲያበራላቸው ተሰብስበው እየጸለዩና እያስተነተኑ ሲሆን ይህንን በተመለከተ የቀድሞው ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ባለፉት 8 ዓመታት በመንበረ ጴጥሮስ በሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርታቸውን ያሉትን የቫቲካን ረድዮ ባልደረባ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አቅርበውታል፣
ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በበዓለ ጰራቅሊጦስ እ.አ.አ 2009 ዓም ባቀረቡት ስብከት “የሐዋርያት ውህደትና አንድነት የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ቅድመ ሁኔታ ነው፣ የውህደቱ ቅድመ ሁኔታ ደግሞ ጸሎት ነው” ሲሉ ያስተማሩት ቅድስት ቤተ ክርስትያን በዚሁ ሳምንት የምታካሄደው ይህንን ይመስላል፣ የብፁ ዓን አበው ፓትርያኮችና ካርዲናሎች በዚሁ ሳምንት በመንበረ ጴጥሮስ ተሰብስቦ አብሮ መጸለይና ማስተንተን ልክ ሓዋርያት በጽርሐ ጽዮን ከቅድስት ድንግል ማርያም አብረው ያደርጉት የነበረውን የሱባኤ ሁኔታ ያመለክታል፣ ያኔ ለተመሠረተችው ቤተ ክርስትያን ዋነኛ ተዋናይና ረዳት ሆኖ በልሳነ እሳት መልክ በሐዋርያት ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ቅዱስነታቸው ይህንን ፍጻሜ አስመልክተው ሲያብራሩ ሁለት የሰው ልጅ ሳንባዎች ካለ ኦክስጀን ምንም መሥራት እንደማችሉ ክርስትያኖም አለመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምንም ለማድረግ እንደማችሉ እንዲህ ሲሉ ገልጠው ነበር፣
“ነፋሱ ለስጋዊ ሕይወት ኑሮ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ ነገር ደግሞ ለመንፈሳዊ ሕይወት ነው፣ የነዋሪዎች ሕይወትን የሚመርዝ የአከባቢ የአየር ብከላ እንደሚያጋጥም ሁሉ የምልብና የመንፈስ ብከላም ይገኛል፤ ይህም መንፈሳዊ ኑሮን ይገድላል እንዲሁም ይመርዛል፣” ብለው ነበር፣
መርዙ የት እንደሚገኝ ሲገልጡ በነዲክቶስ 16ኛ ከእግዚአብሔርም ሳይቀር ለመሸሽ በሚደረግ የግል ነጻነት የመፈለግ ዝንባሌ በሰው ልጅ ታሪክ ብዙ እንዳስከፈለ በማምለከትም እንዲህ ብለው ነበር፣
“መንፈሳዊው እሳት ከሰው ልጆች የውግ ያና የቦምቦች እሳት እንደሚለይ ሁሉ በቤተ ክርስትያን የተነሣው እና በእርሷ የሚያስተጋባው የኢየሱስ ክርስቶስ እሳትም ልዩ ነው፤ ልዩነቶም ከዛሬ በፊት በተለያዩ አምባገነኖች ከተለኰሱ እሳቶች በተለይ ደግሞ ባለፈው ክፍለ ዘመን ከነበሩና የተቃጠለ ምድርን ከበስተኋላቸው ትተው ከሄዱ ይለያል፣ የእግዚአብሔር እሳት ማለትም የመንፈስ ቅዱስ እሳት ሙሴ በዕጸ ጳጦስ እንዳየው እሳት ሆኖ የማያቃጥል እሳት ነው፣ የሚያሞቅ እንጂ የማያቃጥል እሳት ነው፤ እንዲሁም የሰው ልጅ ልብን እያሞቀ የወው ሁኔታ ውሳጣዊና ለእውነትና ለፍቅር ያለው ጥሪ የበለጠውንና የተሻለውን ነገር የሚያመነጭ ነው፣” ሲሊ ከአንድ ዓመት በኋላ በግንቦት 23 ቀን 2010 በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሰብከው ነበር፣
ይህ እሳት ኢየሱስ ለቤተ ክርስትያኑ ሕይወት የሰጠበትና እርሱን በመከተለም ሐዋርያት ያቀጣጠሉት መሆኑ ሲገልጡ ደግሞ፤
“ከሁሉም አስቀድሞ ከመጀመርያው ግዝያት ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስትያንን የሁሉ ሕዝቦች ቤተ ክርስትያን አድርጎ ፈጠራት፤ እርሷ መላውን ዓለም ታቅፋለች፤ የወገን የኑሮ ደረጃና አገራዊ ድንብሮችን በመጣስ እግዚብሔር አንድና ሶስት መሆኑን በሚያምንና በምሥጢረ ስላሴ በጸና መተማመን ትገለጣለች፣ ከመቆምዋ ጀምራ ቤተ ክርስትያን አንድ ካቶሊካዊት እና ሓዋርያዊት ናት፣ እውነተኛው ባህርይዋም ይህ ነው በዚህ ብቻም ነው መታወቅ ያለባት፣ እርሷ ቅድስት ናት ይህም በአባሎችዋ ቅድስና ሳይሆን እግዚአብሔር በመንፈሱ በሚፈጥራት በሚያነጻትና በሚቀድሳት ኃይል ነው ሲሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓም ሰብከው ነበር፣








All the contents on this site are copyrighted ©.