2013-03-06 16:09:05

ብፁዓን ካርዲናሎች ለቀድሞ ር ሊ ጳ መልእክት መላካቸው ተገለጸ ፡


እነሆ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ሰደ ቫካንተ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አልባ ከቀረች ነገ አንድ ሳምንት ሊሆን ነው ። በነዲክት 16ኛ ባላፈው ሳምንት አጋማሽ ሐሙስ 28 ቀን በገዛ ፈቃዳቸው እና ፍላጎታቸው መንበረ ሐዋርያ መልቀቃቸው የሚታወስ ነው ። የቤተ ክርስትያኒቱ ብፁዓን ካርዲናሎች ከመላ ዓለም ተሰባስበው አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ አብዛኛዎቹ ሮም የገቡ ሲሆን ጥቂት እንዲገቡ እየተጠበቁ ይገኛሉ ።በአሁኑ ግዜ ትናትና እና ዛሬ ብፁዓን ካርዲናሎች ቫቲካን ውስጥ በአዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ ተሰብሰበው ጸሎት እና አስተንትኖ በማካሄድ ላይ እና ኮንክላቭ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመረጡበት ግዜ ለመለየት እየወያዩ እንደሚገኙ የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ለመገኛኛ ብዙኀን አስታውቀዋል። የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በየቫቲካን ክፍል ማኅተም ለተገኙ በርካታ ጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ፡ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብጹዓን አበው ቫቲካን ውስጥ ኮንክላቨ አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ቀኑ ለመለየት እና የቤተ ክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ቫቲካን ውስጥ አጠቃላይ ስብሰባ እያካሄዱ ይገኛሉ ። በማያያዝም ብጹዓን ካርዲናሎቹ መንበረ ሐዋርያ ለለቀቁ የቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መልልእክት ማስተላለፋቸው አስገንዝበዋል።
ብፁዓን ካርዲናሎቹ ለበነዲክት 16ኛ ያስተላለፉት መልእኽት ይዘታ በስምንት ዓመታት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ላሳዩት ብርሃናዊ አመራር እና ለቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና ለዓለም መልካምነት ለነሱ ያሳዩት ሰናይ አርአያ የምስጋና መልእክት መኖሩ ቃል አቀባዩ አክለው ገልጠዋል። በነዲክት 16ኛ ለብፁዓን ካርዲናሎች እና ለቅድስት ቤተ ክርስትያን እንዲጸልዩ መልእክቱ መማጸኑ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ለጋዜጠኞች ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል። ብጹዓን ካርዲናሎቹ ለበነዲክት 16ኛ የላኩት የጋራ መልእኽት በየካርዲናሎች ጉባኤ ሊቀመንበር የብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ ፊርማ የሰፈረበት እንደሆነ ቃል አቀባዩ ማስገንዘባቸው ታውቆዋል። ቫቲካን ውስጥ የተሰበሰቡት ካርዲናሎች 148 መሆናቸው እና ከነሱ 110 የመምረጥ መብት ያላቸው እንደሆኑ እና ሌሎች አምስት ሮም እንዲገቡ እየተጠበቁ መሆናቸው ቃል አቀባዩ በተጨማሪ ማብራርያ መስጠታቸው ተመልክተዋል።
በየቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ገለጣ መሠረት ፡ ኮንክላቭ ማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመረጡበት የካርዲናሎች ጉባኤ ቀን እንዳልተቆረጠ እና ብጹዓን ካርዲናሎቹ ዕለቱ እንዳልለዩት እና መቸ እንደሚሆን እና መቸ እንደሚጀመር በውል አይታወቅም ።ይሁን እና ብፁዓን ካርዲናሎች ኮንክላቭ የአዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ከመሰናዶ ባሻገር የቅድስት መንበር እና የተለያዩ ተቅዋሞችዋ እንቃስቃሴ እነዚህ ከረኪበ ጳሳት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ተንተርሰው ተሐድሶ ቤተ ክርስትያን የቤተ ክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ እና አዲስ ስብከተ ቅዱስ ወንጌል ትኩረት የሰጡ ዓበይት ነጥቦች እየተመለከቱ እንደሆነ ከተሰበሰቡበት አዲስ የሲኖዶስ አዳራሽ ይወጣ ዜና አስገንዝበዋል።በሌላ ዘገባ የቫቲካን ቤተ መዘክር ዝግ መሆኑ እና ካፐላ ሲስቲና ለኮንክላቨ እየተዘጋጀ መሆኑ ተመልክተዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ ምክንያት ከ65 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ 24 የተለያዩ ቋንቋዎች ዘገቢዎች አምስት ሺ ጋዜጠኛች በቫቲካን አከባቢ አድፍጠው በመጠባባቅ ላይ ይገኛሉ ።








All the contents on this site are copyrighted ©.