2013-03-04 16:23:32

የመጀመርያው የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ


ድኅረ በነዲክቶስ 16ኛ የመጀመርያው የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ዛሬ ጥዋት በካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ በቫቲካን ከተማ በጳውሎስ 6ኛ አደራሽ ዛሬ ጥዋት እንደ ተካሄደ እና ማምሻውም ደግሞ በሮም ሰዓት አቆጣጠር አምስት ሰዓት ከቀትር በኋላ ሁለተኛው እንደሚካሄድ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣ ከአንደኛው ጉባኤ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ የቅድስት መንበር የዜናና የኅትመት ክፍል አላፊና የቫቲካን ረድዮ ዋና አስተዳዳሪ ጥቀ ክቡር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ናቸው፣
እንደ አባ ፈደሮኪ ሎምባርዲ መግለጫ ይህ ጉባኤ ር.ሊ.ጳ ለመምረጥ ለሚካሄደው የዝግ ጉባኤ ማለትም ኮንክላቨ ማዘጋጃ ነው፣ በዚሁ ጉባኤ 142 ካርዲናሎች ተሳትፈዋል ከእነዚህም ውስጥ 103 ሊመርጡና ሊመረጡ የሚችሉ መሆናቸውም አመልክተው ሌሎች 12 ሊመርጡና ሊመረጡ የሚችሉ ካርዲናሎች ማምሻውን እንደሚደርሱ አስገንዝበዋል፣
ዛሬ ጥዋት የተካሄደው ጉባኤ ነዓ ኦ መንፈስ ቅዱስ በሚለው ጸሎት እንደተጀመረና ጉባኤውን የካርዲናሎች አፈ ጉባኤ እንደከፈቱትና ሁላችው ካርዲናሎችና በኅብረትና በተናጠል ቃላ መሃላ መፈጸማቸውን አመልክተዋል፣ በጉባኤው የተገኙ መንበረ ጴጥሮስ ክፍት ሆኖ በሚቀርበት ጊዜ ር.ሊ.ጳ እስከሚመረጡ ድረስ የመንበረ ሐዋርያው ቤት ተጠሪ ማለትም ካመርለንጎ ብፁዕ አቡነ ታርቺዝዮ በርቶነ የቤተ ጳጳሱ ሱባኤ ሰባኪ የነበሩ ጥቀ ክቡር አባ ራኒየሮ ካንታላመሳ በማታው ክፍለጊዜ ጉባኤ የመጀመርያውን አስተንትኖ እንዲመሩ ባቀረቡት ኃሳብ ሁላቸው አባቶች ተስማመተዋል፣ ከዚህ በመቀጠል የካርዲናሎቹ ጉባኤ ለልሂቀ ር.ሊ.ጳ ቅዱስነታቸው የምስጋና መልእክት እንዲጽፉላቸውም ተስማምተዋል፣
በዛሬው ጉባኤ ከተደረጉ ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ለመንበረ ሐዋርያ ተጠሪ የሚርዱ ሶስት ካርዲናሎች መርጠዋል፣ ለአቡናት ሥር ዓት ብፁዕ ካርዲናል ረ ለካህናት ሥር ዓት ብፁዕ ካርዲናል ሰፐ ለዲያቆና ሥር ዓት ብፁዕ ካርዲናል ሮደ ተመርጠዋል፣ እነኚሁ ሶስት ካርዲናሎች በሚካሄዱ ልዩ ጉባኤዎች የመንበረ ሐዋርያ ተጠሪውን ይረዳሉ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.