2013-03-04 14:37:50

ኅዳሴ በሊኅቅ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ ቲዮሎጊያ


RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ራትዚንገር የዛሬ 8 ዓመት በፊት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሁም እንደተሸሙ ሁሉም የመገናኛ ብዙኃን የቲዮሎጊያ ሊቅ ር.ሊ.ጳ. በሚል መጠሪያ በመግለጥ የእሳቸው ጥልቅ የቲዮሎጊያ ሊቅነትን የተመራማሪ የአጥኚ ሊቅነታቸው ላይ በማተኮር ለረዥም ዓመታት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በመሆን ያገለገሉትም አለ ምክንያት እንዳልነበር ሲተነትኑ ታይተዋል። አሁን የእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የተኖረ ፈቃቸው አማካኝነት ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን ያስረከቡ ሲሆን ቲዮሎጊያዊ ስልጣናዊ ትምህርታቸው በተመለከተ በጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበር ጥበብ የመሠረታዊ ቲዮሎጊያ መምህር የቲዮሎጊያ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ፒኖ ሎሪዚዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ርሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ‘እምነትና ምርምር’ በተሰየመው ዓዋዲ መልእክታቸው አምካኝነት ያስተላለፉት ሥልጣናዊ መሠረታዊ የቲዮሎጊያ ትምህርት ጥልቅ ነው። ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለማስተንተን ለማሰላሰል ለመመራመር ይኽም ካለ ምንም አእምሮአዊ ውስንነት የተሰጠንን የማሰብ ባህርይ እንድንጠቀምበት ያዝገነዝቡናል። ስለዚህ ለዓቢይ ምሥጢር ክፍት በመሆን አእምሮን በመጠቀም፣ ለሰው ልጅ ምሥጢር የሆነው የእግዚአብሔር ምሥጢርና የዓለም ምሥጢር አእምሮና ቀልብ ክፍት ማድረግ ትክክለኛውና እውነተኛውን የአእምሮ ጥሪ መተግበር ማለት ነው” ካሉ በኋላ፦ “ቃል እሳቤ የግልጸት ክፍል የሆነውን ባህርይ እሜን በማለት እምነትን በመኖር ይኽ እምነት አእምሮ የማያገል መሆኑ በመረዳትም፣ እምነትና ምርምር ያልታከለበት አሜን በሳል እምነትና የታሰበ እምነት ሊሆን አይችልም። ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተስፋ ነው የዳነው በተሰኘው ዓዋዲ መልእክታቸው አእምንሮ እምነትን ያነጻል ይኽም ከጣኦታዊ አምልኮ ከጥንቆላና ከከንቱነት እና ከምትሃት ነጻ ያወጣናል” በማለት የሰጡት ጥልቅ አስተምህር ፕሮፈሰር ሎሪዚዮ አስታውሰው፦ “ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ገና የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ እያሉ ከዛም ር.ሊ.ጳ. ሆነው ቲዮሎጊያዊ ሥነ ምርምር ክፍት የሆነ፣ ሥነ ምርምር የሚያነቃቃ መንገድ በመጠቆም የአእምሮ አመክንዮአዊ ተወያይነት ዝንባሌ ያነቃቁ ፈጽሞ እንዳይዳከም ያስተማሩ፣ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይትና የምሁራን አካላት ውይይት በዚህ መንፈስ እንዲመራ ያሳሰበ ያነቃቃና ያስተማረ ቲዮሎጊያ ያቀረቡ ናቸው” በማለት የሰጡትን ቃል አምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.