2013-03-01 13:47:30

ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይሎች


RealAudioMP3 ቀደም ተብሎ እንደተገለጠው ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኅይሎች ትላትና ልክ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ መንበር ክፍት በመሆኑ አዲስ ር.ሊ.ጳ. እሲኪሾሙ ድረስ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚሰጡት የጸጥታና የደህንነት ጥበቃ መቋረጡ ሲገለጥ፣ ይኽም የዚህ የጸጥታ ኃይል ዓላማ ምን መሆኑ የሚያርጋግጥ ሂደት ሲሆን፣ የዚህ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይሎች አዛዥ ዳኔለ ሩዶልፍ እንሪግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ለእኛ ካቶሊኮችና በጠቅላላ ለሁሉም ማኅበረ ክርስትያን ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ ካለ መታከት እውነትን የመፈለግ ጥሪ አብነት ናቸው፣ ስልጣናዊ ስብከቶቻቸው ያስደመጡዋቸው ንግግሮች፣ በእውነቱ እውነትን የእግዚአብሔርን ቃል ለመከተል የማያወላውል ጥሪ ልዩ አብነት በመሆን የመሪ መሆናቸው ያረጋግጥልና” ካሉ በኋላ፦ የዚህ የጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል አባላት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጸጥታና ደህንነት ዋስትና ለመስጠት የሚያገለግል ነው። ቅዱስነታቸው የትህትና አርአያ ናቸው፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን በእድሜ መግፋት መክንያት እንደሚለቁ መወሰናቸው ይፋ እንዳደረጉ በእውነት የጸጥታ ኃይሎች ልክ መንፈሳውያን ነጋድያን እንደተሰማቸው ስሜት የኖረ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አገልጋይ፣ ቅዱስነታቸው በሁሉም የጸጥታ ኃይል አባላት ጸሎት የሚታወሱ ናቸው” ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.