2013-03-01 13:54:44

ከቻይና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ለቅዱስነታቸው የተላለፈ መልእክት


RealAudioMP3 ቅዱስነታቸው የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ለመልቀቅ ከወሰኑ በኋላ የዚህ ሐዋርያዊ ተልእኮ ፍጻሜ ምክንያት በማድረግም በቻይና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነት ምእመናን ለቅዱስነታቸው መልእክት እንዳስተላለፉ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው ለቻይና ሕዝብ ለመላ በቻይና ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና አባላቶቿ ዘወትር ቅርብ በመሆን ቻይናንም በመባረክ የቻይና ካቶሊካውያን ምእመናንና ውሉደ ክህነት እንዲሁም የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት የተሸከሙትን መስቀል ቀለል ለማረግና በአገሪቱ የጋራ ውይይት ለማነጽ የሰጡት ድጋፍና ያሳዩት ቅርበት በመልእክቱ በመጥቀስ፣ ለቅዱስነታቸው ከልብ የመነጨ ውሉዳዊ ምስጋና እንደተላለፈም ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አመለከተ።
በቻይና ለተካሄደው የ 2008 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ውድድር ለቻይና አዲስ ዓመት ባለፈው በዓለ ልደት ምክንያት ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልእክት የጠቀሰው በቻይና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መልእክት በማያያዝ በቻይና ቋንቋ ታትሞ የተደረሰው የቅዳሴ መጽሓፍ ለቻይና ውሉደ ክህነት ያስተላለፉት ጥልቅ መልእክት፣ በቅዱስ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳዊ የውሁድ ልብ ምክር ቤት አማካኝነት በተለያየ ወቅት በቻይና ተከስቶ በነረው የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በርእደ መሬት አደጋ ለተጠቃው ለቻይና ሕዝብ የለገሱት ድጋፍ በማስታወስ ምስጋናን በማቅረብ፣ በመጨረሻውም ኵላዊ የሰው ልጅ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲረጋገጥ እሴቶች እንዲኖሩ የእምነት ክብር እንዲታቀብ ብሎም አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለማነቃቃት ካለ መታከት የሰጡት ሕንጸትና አስተምህሮ ያስታወሰው በቻይና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መልእክት ለቅዱስነታቸው በመተባበሩ ጥሪያቸው ድካም ያሳዩ እንደሆነም በይፋ ይቅርታን በመጠየቅ በጸሎት ቅርበትና አድነት እንደሚኖራት ማረጋገጡንም የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.