2013-03-01 18:55:20

ር ሊ ጳ በነዲክት ቅድስት መንበርን ለቀቁ ፡


በነዲክት 16ኛ ትናትና የካቲት 28 ቀን እንደ ጎርጎዮስ ዘመን አቆጣጠር ከቀትር በኃላ በሮም ሰዓት አቆጣጠር አምስት ሰዓት ላይ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ለቀዋል ። ፍጻሜውን መገናኛ ብዙኀን ዓለም ዓቢይ ትኩረት በመስጠት ዘግበዋል።
ይሁን እና መንበረ ሐዋርያ ከመልቀቃቸው ከቀትር በፊት ሮም ውስጥ ለተገኙ 144 ካርዲናሎች በክልመቲና ሐዋርያዊ አዳራሽ ተገናኝተው ንግግር ሲያደርጉ
ውድ በክርስቶስ ወንድሞቼ ለስምንት ዓመታት ያህል በርእሰ ሊቃነ ጵጵስናየ ግዜ የናንተ እገዛ እና ምክር በጣም አግዞኛል ከልብ አመሰግናችሁለሁኝ ፡ በቅርብ ግዜ ለሚመረጡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እጸልያለሁኝ ከአሁን ጀምሬ እንደማክበራቸው እና እንደምታዘዛቸው ቃል እገባልሁኝ ነበር ያሉት ።
በማያያዝ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በጤረጰዛ ዙርያ የታነጸች አይደለችም ያነጻት ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እና ህያው የሚያደርጋት ራሱ ነው በማለት አክለው ለካርዲናሎቹ ገልጠውላቸዋል ።
በኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሞቼ ውድ ካርዲናሎች በአካል ብንለያይም በጸሎት አብረን እንጓዛለን አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ በምንዘጋጅበት በአሁኑ ወቅት በጸሎት እና በአስተንትኖ የምንጠመድበት ግዜ ነው እና በምርጫው ግዜ መንፈስ ቅዱስ ያግዛችሁ ያብራላችሁ ብለዋል በነዲክት 16ኛ ። ካርዲናሎቹን በየተራ እና አንድ በአንድ አነገጋረዋል።
የክርዲናሎች ጉባኤ ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ በቡላቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፡ የወደዱ እና የተከበሩ የመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ወኪል በነዲክት 16ኛ እኛ ነን እስዎን ማመስገን ያለብን የኤማሁስ ሐዋርያት ተመኩሮ ተከትለን ሐዋርያቱ እና ክሱ ጋ ስንጓዝ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ጋ ልባችን ጠጥሮ ሳይቀር አልቀረን ምኽንያቱ እሱ ያያናግረን ዝም ማለታችን ምን ይሆን እያሉ ርስ በርሳቸርው እንደተነጋገሩ በማለት በቅድስት መንበር የቅድስት መንበር የካርዲናሎች ጉባኤ ሊ ቀመንበር ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ ።
በማያያዝም አዎ ቅድስነትዎ ለስምንት ዓመታት ያህል ከስዎ ጋ ስንጓዝ ልባችን ደርቆ ከሆነ ይቅርታ በመጠየቅ ላደረጉት ሁሉ ከልባችን እናመሰግንዎታለን ብለዋል።
በነዲክት 16ኛ የካርዲናሎች ጉባኤ ሊቀመንበር ብጹዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖን አመስግነው ፡ ከትናትና ወድያ ሮቡዕ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ የመጨረሻ ትምህርተ ክርስቶስ በሰጡበት ግዜ ልሰናበትውቸው 150 ሺ ምእመናን በአደባባዩ በመገኘታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው እና ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ህያው መሆንዋ እንደሚያመላክት ገልጠዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን በመከተል በአጸሎት እና አስተንትኖ በመጠመድ ለሰው ዘር ሁሉ እና ለቤተ ክርስትያን ማገልገል እንችላለን ቃል በነዲክት 16ና ።ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በነዲት 16ኛ ትናትና ከቀትር በኃላ በሮም ሰዓት አቆጣጠር አምስት ሰዓት ላይ መንበረ ሐዋርያ ጰጥሮስ ለቀው ከቫቲካን 33 ኪሎሜትር ርቆ ወደ ሚገኘው ቤተ ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና ካስተል ጋንዶልፎ ተዘዋውረዋል ።
በነዲክት 16ኛ ከቫቲካን ተነስተው ካስተል ጋንዶልፎ እስከ ሚገቡ ራድዮ ቫቲካን የቫቲካን ተለቪጅን ማእከል እና የጣልያን ተለቪጂን አገልግሎት በቀጥታ አስተላልፈዋል።በነዲክት 16ኛ ካስተልጋንዶልፎ አደባባይ ለተጠባበቅዋቸው በርካታ ምእመናን በሐዋርያዊ መስኮት ብቅ ብለው አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እምብርት ቅድስት መንበር ከትናትና ምሽት በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከስምንት ሰዓት ጀምራ አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እስከ ሚመረጡ ድረስ senza Papa ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አልባ ሁናለች ።
በነዲክት 16ኛ ከተጠቀስው ሰዓት በኃላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አይደሉም ሆኖም ግን ቤተ ክርስትያንን በጸሎት ይሸኛሉ ።ቅዱሳን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብእግዚአብሔር ስም የቤተ ክርስትያን መርከብ መሪዎች እና አዲስ እስከ ሚመረጡ ድረስ በጸሎት እና አስተንትኖ እና በትዕግስት መጠበቅ እንደሆነ ይታወቃል።
በመላ ዓለም የሚገኙ የቤተ ክርስትያኒቱ ካርዲናሎች አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ሮም መግባት መጀመራቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.