2013-02-27 14:49:38

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ አስመርቶ ያስጀመረው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር መሠረት ትላንትና “የክርስቲያን እግዚአብሔር ለምን አንድ ሦስትም ነው? የሚለው ጥያቄ መርህ በማድረግ የቅድስት ሥላሴ አካላት ሦስት መካከል ያለው የሱታፌ ሚሥጢር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቅዱስ መጽሓፍ ባህል መሠረት አቢይና ጥልቅ አስተንትኖ ያቀርባል” ብለው፣ በኦሪት ዘ ዳግም ምዕ. 6 ቁ. 4“እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” የሚለውን፣ በተአምኖተ እምነት ዘንድ ያለው በአንድ እግዝአብሔር እምናለሁ” በማለት ከምንናዘዘው እምነት ጋር አያይዘውም ክርስቲያን በአንድ እግዚአብሔር የሚያምን መሆኑ ኢሳያስ ምዕ. 45 ቁ. 22“እናንተ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና ከእኔ በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ተመለሱ ትድኑማላችሁ” በሚለው ጥቅስ መሠረት አብራርተዋል።
ክርስትና ልክ እንደ ምስልምናውና እንደ የአይሁድ ሃይማኖት በአንድ እግዚአብሔር የሚያምን ሃይማኖት ነው። ሆኖም የክርስትናው አንዳዊ አምላክ ከምስልምናውና ከአይሁድ ሃይማኖት ከሆነው ከአንዳዊ አምላክ ጋር አንድ-ዓይነት አይደለም፣ የተለየ ነው። ምክንያቱም የክርስትናው አንዳዊ አምላክ ሦስትነትም ነው በማለት ብቸኛው የእግዚአብሔር ባህርይ ሦስትነት አካል ነው። የተለያዩ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ስም በሚሰጠው ሚሥጢረ ጥምቀት ክርስቲያን ይኮናል፣ ሦስት እግዚአብሔሮች ሳይሆኑ አንድ አግዚአብሔር መሆኑ የካቶሊክ መዝገበ ሃይማኖት ከቁ. 249 እስከ ቁ. 256 ያለውን ጠቅሰው በማስረዳት፣ ስለ ምን አንድ ሦስትነት እግዚአብሔር? ለምን በቀላሉ ለመረዳት እንዲቻለን አንድ አካል አይሆንም፣ ለምን በሦስት አንድ ተብሎ ይገለጣል? የሚሉትን ጥያቄዎችን በማቅረብ፣ የካቶሊክ መዝገበ ሃይማኖት ቁ. 254“በእርግጥ አንድ መለኮታዊ አካል ከሌላው ይለያል። ‘እግዚአብሔር አንድ’ ነው፣ ግን ‘ብቸኛ’ አይደለም፣ ‘አንዱ አካል ከሌላው ብግልጽ ይለያልና አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለመለኮታዊ ሕላዌ የተስጡ ተራ ስሞች አይደሉም’፣ አብ ወልድ አይደለም፣ ወልድም አብ አይደለም መንፈስ ቅዱስ አብም ወልድም አይደለም፣ ‘አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ነው’ መለኮታዊ አንድነት ሦስትነት ነው።” በሚለው ትምህርት ሥር በመመለስ፣ ክርስቲያን ላንድ ለማይጨበጥ መለኮት ሳይሆን፣ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ለሁሉም በአንድነትም ሦስት ለሆነው አንዱ አካል ከሌላው በግልጽ ለተለየው አካል የሚጸልይ ነው። በዚህ ዘለዓለማዊነት ሱታፌ ሙሉ ፍቅር ሙሉ ደስታ ከአንድነት እግዚአብሔር ሦስትነት ወደ ሆነው ዘንድ ለመግባት ባለው ተስፋ አማካኝነት ጸሎቱን ያቀርባል በማለት ያቀረቡት አፍስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.