2013-02-26 10:02:02

ቡፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የብህትውና ሕይወት ምርጫ አዲስ የተልእኮ ሐዋርያዊ አገልግሎት ምሥጢር ነው


RealAudioMP3 በተገባው ዓቢይ ጾም ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የአንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካላት ብፁዓን ካርዲናላትን ያሳተፈው እ.ኤ.አ. ከየካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደው ሱባኤ የመሩት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ በሱኤው ማጠቃለያ ለቅዱስ አባታችንና ለብፁዓን ካርዲናሎች ባሰሙት የምስጋና ቃል በቅድሚያ በኵላዊ እምነትና በመዝሙረ ዳዊት መሠረት በማድረግ የተካሄደው የአንድ ሳምንት ሱባኤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተመርቶ መጠናቀቁ በማስታወስ በመላ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪዎች የኵላዊት ቤት ክርስትያን አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች ስም ቅዱስ አባታችንን ለማመስገን ባሰሙት ቃል፦ “የሁሉም ብፁዓን ካርዲናሎች ስሜትና የሰጡኝን ሃሳብ መሠረት በማድረግ፣ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቅርብ ተባበሪ በመሆን በተሰጠን ሐዋርያዊ ኃላፊነት ብቁዎች ሳንሆን ተገኝተን እንደሆን ይቅርታን እንጠይቅዎታለን። ለሰጡት ሥልጣናዊ ቃል አስተምህሮ መሪነት ሁሉ እናመሰግናለን። በላቲን ቋንቋ Magistero ‘magis’ የሚለውን ተውሳከ ግሥ ያስከተለ መሆኑና እርሱም በላይ ሆኖ መምራት ማለት ሲሆን፣ Ministero ደግሞ ‘minus' የሚለው ተውሳከ ግስ በማስከተል አገልግሎት ማለት ያሰማል፣ ገዛ እራስን ዝቅ ማድረግ ማገልገል ማለት ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እነዚሁ ሁለት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን መግለጫ የሆኑትን ተልእኮ በመኖር በቃልና በሕይወት ለሰጡት አብነት በሁሉም ብፁዓን ካርዲናሎች ስም አመሰግኖዎታለሁ። በገዛ ፈቃድዎት የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ሥልጣንዎት ሲያስረክቡ፣ ሌላ በብሕትውና በጽሞና ተደብቆ በሚኖር ሕይወት በመኖር በቤተ ክርስትያን ለሚኖሩት ጥሪ አዲስ የአገልግሎት መግለጫ ነው” ካሉ በኋላ አዲሱ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ አገልግልጎት “Ministero ይኽም ‘minus' የሚለው ተውሳከ ግስ የሚያስከትለው ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚያስተጋባ ነው” በማለት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ በጥልቀት በማብራራት የመሩት ሱባኤ አስተንትኖ ሙሴ በሲና ተራራ ላይ መውጣት የሚያስታውስና ከዚህ ጋር በማያያዝም ነቢይ ኤሊያስ መሠረት በማድረግ ፦ ይኽ ነቢይ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር በማዛመድ ምሬት ያጣጣመ ሁሉን ነገር እርግፍ አድሮ ለመተው ሲል ወደ ተራራ በመውጣት…የእግዚአብሔር ግልጸት ሁሉን የሚያናውጥ ሆኖ እያለ ነገር ግን በሁሉም ሥፍራ እንደሌለ የኖረው የእምነት ገጠመኝ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተመክሮም ነው። በዓለም በታሪክ ዘንድ ነን፣ የእግዚአብሔር አቢይ ግልጸት የሚኖርበት እውነት ነው። ወደ ተራራ በመውጣት የሚኖረው የእግዚአብሔር ግልጸት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተመክሮ ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ አስታወቁ።
ቅድስትስ ድንግል ማርያም ኢየሱስ ከእርሷ በተለየ ጊዜ ለየት ባለ መልኩ እናት እንደሆነችና በዝምታ በጽሞና እምነትን በሚፈትን ጽሞና ዝምታን መርጣ አዲስ የእናትነት ጥሪ ተቀብላለች፣ ማርያም ዝም ስትል በሙላት በገዛ እራሷ ስለ እውነት ትናገራለች። ሁላችን የጽሞና ተካፋዮች እንድንሆን በመጋበዝ የጽሞና የተናገረቸው ቃል የመጨረሻው ቃል ነው” ካሉ በኋላ አያይዘውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሱታፌና ፍቅር የማኅበርሰብ መርህ እንዲሆን በተደጋጋሚ የሰጡት ምዕዳን አስታውሰው፣ የወድማማችነት ፍቅር በሁሉም መንፈሳውያን ማኅበራት ዘንድ በሱታፌና በፍቅር ሥራ እንዲኖር የሚል እንደሆነም በመግለጥ፣ ቅናት ምቀኝነት የሱታፌና የፍቅር ጸር ናቸው፦ሱታፌንና ፍቅርን የሚጻረር ሁሉ እናግል” በማለት የእግዚአብሔር ምኅረት ወሰን የለውም” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.