2013-02-26 09:58:01

ሱባኤ


RealAudioMP3 በተገባው ዓቢይ ጾም ምክንያት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተመረጡት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በሰባኪነት የመሩት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የአንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካላት ብፁዓን ካርዲናላሎች በማሳተፍ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደው ሱባኤ መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን በሱባኤው ማጠቃለያ ባሰሙት ሥልጣናዊ ቃል፦ “የእግዚአብሔር እጅ መንካትና ፍቅሩንም ማጣጣም በእውነቱ ያ ፍጹም ውበት ዝቅ ብሎ በሰው ልጅ ሁነት በሙላት መሳተፉ የሚገልጥ ፍቅር መኖር ማለት ነው” በማለት ያ ፍጹም ፍቅር የጠፋውን የሰውን ልጅ ለመፈለገ ገዛ እራሱ የጠፋው ሰው በመሆን የኖረው ሙሉ ፍቅር ለይተው ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ባለፉት ዓመታት በቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው የቅርብ ተባባሪ በመሆን አብሮአቸው በሐዋርያዊ ተልእኮ ለተጠመዱት ብፁዓን ካርዲናሎችን ማመስገናቸው ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
“የክፋት መንፈስ የእግዚአብሔርን ፍጹም ውበት ለማጉደፍ በሥውር አድብቶ ከመንቀሳቀስ ወደ ኋላ አይልም፣ ‘ጨለማ ቆሻሻ ጭቃነት በእምነት ብቻ ነው የሚወገደው፣ ምክንያቱም እምነት በጨለማና በድንግርግር መንገድ የእግዚአብሔር እጆችን ፍቅርንና እውነትን እንድናገኝ የሚያበቃን ብሶል ነውና። የክፋት መንፈስ በስቃይ በምግባረ ብልሽት አማካኝነት እግዚአብሔርን ለመጻረር እውነቱና ውበቱን እንዳይታወቅ ለማድረግ በቀጣይነት ተፈጥሮን ለማጉደፍ ይሻል” ካሉ በኋላ የሱባኤው መሪ ቃል እርሱም፦ “የእምነት ጥበብና የጸሎት ጥበብ” የሚል መሆኑ በማስታወስ፣ “የመካከለኛው ክፍለ ዘመን የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ‘Logos-ሎጎስ’ ቃል በሚል ብቻ ሳይሆን ጥበብ የሚል ትርጉም አዘል መሆኑ በመግለጥ፣ ቃል (ሎጎስ) የሥነ አኃዝ አመክንዮ ብቻ ሳይሆን ልብ ያለው እንዲሁም ፍቅር ማለት መሆኑ ጥልቅ ፍቹን ይገልጣሉ። እውነት ውበት ነው፣ እውነትና ውበት ተያይዘው የሚሄዱ የማይነጣጠሉ እርሱም ውበት የእውነት ማህተም ነው” ብለዋል።
ክርስቶስ የእግዚአብሔር ፍቅር ውበትና እውነት እርሱም ሥጋ ለብሶ የወረደ ቃል መሆኑና ለዚህ ለወረደው ቃል-ሥጋ ዓለም እሾክ ይዞ እንደጠበቀውና። በጨለማ የተከደነው ውበት በኃሰት የጎደፈ እውነት፣ ይኽ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ የሚያመለክት መሆኑና በስቃዩ ዘንድ የፈጣሪያችንና የመድህናችንን ውበትን እንደምንመለከት፦ “ምንም ቢሆንም በጨለማው ሌሊት በጽሞና የእግዚአብሔርን ቃል እናዳምጣለን። ማመን ሌላ ትርጉም ያለው ሳይሆን በጨለማው ዓለም የእግዚአብሔርን እጆች መንካትና በጽሞና ቃሉን ማዳመጥ ፍቅሩንም መመለከት ማለት ነው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘውም፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሥልጣናዊ ቃል ከመለገሳቸው ቀደም በማድረግ የሱባኤው ሰባኬ ለባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ለብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ከልብ አመስገነው፣ መዝሙረ ዳዊት መሠረት በማረግ በሙላት እምነት ምን ማለት መሆኑ የሰጡት የአስተንትኖ እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑ ገልጠው፣ የእሳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ፍጻሜ ሌላ አዲስ ጅማሬ የሚያመለክት መሆኑ ሲያብራሩ፦ “ውዶቼ ብፁዓን ካርዲናሎች፣ በዚህ የሱባኤ ሳምንት ብቻ ሳይሆን ላለፉት ስምንት ዓመት ከእግዚአብሔር በተቀበልኩት የቅዱስ ጴጥሮስ ተካታይነት ከባዱ ሐዋርያዊ ሥልጣን ከጎኔ በመሆን በእምነትና በፍቅር ለሰጣችሁት ትብብርና ላሳያችሁት ቅርበት ድጋፍና ፍቅር ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ያሳያችሁት ውጫዊ ሱታፌ ልቆ የሚሄድ ፍቅር መቼም ቢሆን በልቤ አቅቤ የምይዘው ነው። ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ እንዳሉትም፣ መንፈሳዊ ቅርበት የተሞላው ነው። በዚህ እርግጠኝነት ወደ ፊት በማለት እግዚአብሔር በጨለማ ላይ ድል የሚነሳው እውነት ውበትና ፍቅር ዘወትር ድል አድራጊዎች መሆናቸው የማያወላውል እምነት አለኝ አለን” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.