2013-02-22 16:36:48

የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ መግለጫ ፡



የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የወቅቱ የቤተ ክርትያን ሁኔታ ትኩረት በመስጠት በየግዜው ለቫቲካን ጣልያን እና የውጭ ጋዜጠኞች ትኩስ ዜና በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል ። ቃል አቀባዩ ትናትና በየቫቲካን የመገናኛ ብዙኅን አዳራሽ ለጋዜጠኞች እንደገለጡት Conclave ማለት የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫ በተመለከተ የካርዲናሎች ጉባኤ ከ28 የካቲት በኃላ ተሰብስቦ የምርጫ ዕለት ይፋ እንድያደርግ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
በወቅቱ ስለ ቤተ ክርስትያን እና በቅርቡ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ስለሚለቁ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት መንፈስ የራቀ በቤተ ክርስትያን ባለስልጣኖች መካከል ፍጥጫ እና አለመረጋጋት አለ በማለት የሚጻፈው እና የሚነገረው ሁሉ ሐቅን የማያንጸባርቅ ፍረ አልባ መሆኑ ለሚሰጡ ግምቶች ሁሉ ምላስ መስጠት አዳጋች መሆኑ ቃል አቀባዩ ለጋዜጠኞች ገለጠዋል።
በነዲክት 16ኛ ቫቲ ሊክስ ፍሰት ምስጢራዊ ዜና ትኩረት በሰጠ ጉዳይ ሶውስት ካርዲናሎች ጠርተው ለማነጋገር አቅደዋል የሚባለው ጉዳይም መሠረት እንዲሌለው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ ገልጠዋል።Motu proprio ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በግል የመነጨ ሐሳብ ለንባብ የሚበቃ ሰነድ ዝግጁ መሆኑ እና ይዘታው አስቀድሞ ለመናገር የማይቻል ሆኖ Conclave አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ሕገ ቤተ ክርስትያን ትኩረት እንደሚሰጥ ቃል አቀባዩ አውስተዋል።
የቅድስት መንበር ቃል አቅባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በነዲክት 16ኛ መንበረ ሐዋርያ ከመተዋቸው በፊት በጥቂት ቀናት የሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ምግባሮች አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ፡ ቫቲካን ውስጥ በመካሄድ ላይ ያለው እና ነገ ቅዳሜ የምጠቃለለው መንፈሳዊ አስተንትኖ እንደሚሳተፉ የመንፈሳዊ አስተንትኖ ፍጻሜ ቃል እንደሚያሰሙ አመልክተዋል።
ኃላም በነዲክት 16ኛ የጣልያን ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ ፊታችን እሁድ እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከሚገኙ በ150 ሺ ከሚገመቱ ምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት እንደሚደግሙ ፊታችን ሮቡዕ ረፋድ ላይ ለምእመናን የመጨረሻ ትምህርተ ክርስቶስ እንደሚሰጡ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።በዚሁ የበነዲክት 16ኛ ለመጨረሻ ግዜ የሚሰጡት ትምህርተ ክርስቶስ በ30 ሺ የሚገመቱ ምእመናን እንደሚገኙ ቃል አቀባዩ በተጨማሪ ገልጠዋል።የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳፕሳት በነዲክት ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና የመጨረሻ ቀን እንደ ጎርጎርዮስ አቀቁጣጠር ሐሙስ 28 ቀን እንደሚሆንም ቃል አቀባዩ በማያይዝ አስገንዝበዋል። በነዲክት 16ኛ በዚሁ መንበረ ሐዋርያ የሚለቁበት የመጨረሻ ቀን ረፋድ ላይ ሮም ውስጥ ከሚገኙ ካርዲናሎች እንደሚሰናበቱ እና ከቀትር በኃላ በሮም ሰዓት አቆጣጠር አምስት ሰዓት ላይ ቅድስት መንበር ለቀው በሆሊኮፕተር ከቫቲካን ወደ ካስተል ጋንዶልፎ ቤተ ርእሰ ሊቃነ ጵጵስና እንደሚያቀኑ የቫቲካን ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎማርዲ አብራርተውል። ከቫቲካን ካስተልጋንዶልፎ 15 ደቂቃ እንደሚፈጅ እና የሮም እና የካስተል ጋንዶልፎ ሀገረ ስብከት ቁምስናዎች ደወል እንደሚደውሉ እና በነዲክት 16ና ካስተልጋንዶልፎ እንደደረሱ በአደባባዩ ለሚጠብቅዋቸው ምእምናት እና ምእመናን ሰላምታ ሰጥተው ሐዋርያዊ ቡራኬ እንደሚሰጡ መርሀ ግብሩ ያምለክታል ።ፊታችን ሐሙስ የካቲት 28 ቀን በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከስምንት ሰዓት ጀምሮ ቅድስት መንበር አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እስከ ሚመረጡ ድረስ መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ vacante ሌጣ ትቆያለች ።








All the contents on this site are copyrighted ©.