2013-02-22 14:13:08

ብፁዕ አቡነ አንቶኒያዚ አድስ የቱኒሲ ሊቀ ጳጳሳት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በእስራኤል በጋሊለያ የራማላህ ቆሞስ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 1948 ዓ.ም. በኢጣሊያ ትረቪዞ አውራጃ በሚገኘው የቪቶሪዮ ቨነቶ ሰበካ የተወለዱት የኢየሩሳሌም ፓትሪያርክ ውሉደ ክህነት አባል ብፁዕ አቡነ ኢላሪዮ አንቶኒያዚ የቱኒሲ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ እንደሰየሙዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ብፁዕ አቡነ አንቶኒያዚ የኦደርሶ የቅዱስ ፒዮስ አስረኛ ልኡካን ተቋም በመግባት የአንደኛ ደረጃ በሐዋርያዊ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የፓትሪያርክ በይት ጃላ በሚገኘው የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት እ.ኤ.አ. ከ 1962 በንኡስ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት እ.ኤ.አ 1965 ዓ.ም. በአቢይ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በመግባት የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ትምህራቸውን አጠናቀው እ.ኤ.አ. ሰነ 24 ቀን 1972 ዓ.ም. ማእርገ ክህነት ተቀብለው እ.ኤ.አ ከ 1972 እስከ 1975 ዓ.ም. በዘርቃ በሚገኘው ቅድስ ፒዮ ቁምስና ምክትል ቆሞስ እ.ኤ.አ. ከ 1975 እስከ 1976 ዓ.ም. ህሶሊዱም የፉሄይስ ቆሞስ እ.ኤ.አ. ከ 1976 እስከ 1980 ዓ.ም. የማርቃ ምክትል ቆሞስ፣ እ.ኤ.አ. ከ 1980 እስከ 1992 ዓ.ም. በስማካይህ ቆሞስ እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ.ም. ሮማ በመምጣት በተርሲያኑም መንበረ ጥበብ በመንፈሳዊነት ቲዮሎጊያ ሊቅነት አስመስክረው እ.ኢ.አ. በ 1995 ዓ.ም. ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እስከ 2005 ዓ.ም. በራማላህ ጋሊለያ እስራኤል ቆሞስ ከዛም እ.ኤ.አ. ከ 2005 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. በረነህ ቆሞስ ቀጥለውም በራመህ ቆምስ በመሆን ያገለገሉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለዚህ አዲስ ኃላፊነት ሲጠሩኝ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በእኔ ላይ ያላት እምነት የሚገልጥ በመሆኑ ትልቅ ኃላፊነት ነው። በሳቸው እንዲሁ በምእመናን ጸሎት ሁሉ ተደግፌ የሚፈጽመው ሐዋርያዊ አገልግሎት ነውና በተአዝዞ ተቀብየዋለሁ በተሰጠኝ አዲስ ሐዋርያዊ ኃላፊነት አማካኝነው በቱኒዚያ ሰላም ለማስፋፋትና በሰላም ባህል ሕዝብ ለማነጽ በሚደረገው ጥረት ሁሉ ተቀዳሚ ሚና ለመጫወት ቤተ ክርስትያን ስለ ሰላም ፍቅር ምህረትና ይቅር ባይነትን ለምታስተምረው ትምህርት ምስክር እንዲሆኑ በዚህ ተልእኮ እግዚአብሔር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ቅድስት ድልንግል ማርያም እንደምትደግፋቸው ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልስል አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.