2013-02-22 14:10:07

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለማርያም ለእመ አምላክ ጽሞናና ትህትና ያላቸው ፍቅር


RealAudioMP3 “ማርያምን እንከተል እርሷንም እንምሰል፣ እርሷን ከተከተልና ከመሰልን መላ ሕይወታችን እንደ የማርያም የምስጋና ጸሎት እግዚአብሔርን የሚያወድስ ይሆናል” ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለማርያም ያላቸው ፍቅር ካሉት ጥልቅና ያላቸው ማርያማዊ መንፈሳዊነት ከሚገልጡ ቃላቶቻቸው አማካኘንት ለመረዳቱ አያዳግትም። ልክ እንደ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማርያማዊ መንፈስ የተካኑ ለማርያም ያላቸው ውሉዳዊ ፍቅር ገና ከሕፃንነታቸው በባቪየራ በሚገኘው በአልቲዩቲንግ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ጋር የነበራቸው ትስስር ምስክር ነው።
እ.ኤ.አ. ታህሳስ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ባሰሙት የእለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “የእግዚአብሔር ክብር የሚገለጠው በድልና በአንድ የንጉሥ ሥልጣን ዘንድ በአንድ አቢይ የናጠጠ ቤተ መንግሥት ወይንም በታወቀች ከተማ ሳይሆን በአንዲት ድንግል ማሕጸን በማደር በአንድ ሕጻን ድኽነት አማካኝነት ነው የሚገለጠው። የእግዚአብሔር ከሃሌ ኩሉነት በሕይወታችን በኃይል የሚገለጠው በጽሞና ነው” በማለት በሰጡት አስተምህሮ የማርያም ማንነት ለይተው እንዳስገነዘቡ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
እ.ኤ.አ ግንቦት 31 ቀን 2009 ዓ.ም. የማርያም ወር መዝጊያ ምክንያት ባሰሙት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፦ “”የማርያም እናትነት ኩላዊነት ባህርይ ያለው፣ ኩላዊት እናት ይኽም ሁሉም ከእግዚአብሔር በክርስቶስ እምነት የሚፈጠሩትን የሚወለዱትን የሚያቅፍ ነው። ለዚህም ነው ማርያም ለሁሉም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በጊዜና በሥፍራ በመጓዝ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም በድል አድራጊነት መምጣት ‘ጌታ ኢየሱስ ና’ በሚለው ጸሎት ለትውልድ ምልክትና የቤተ ክርስትያን አርአያ የሆነችው” እንዳሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገባቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ስብከት፦ “ውዶቼ ንጽሕት ቅዱስት ድንግል ማርያም እናታችን መሆንዋ ምንኛ አቢይ ጸጋ ነው። በዕለታዊ ኑሮአችን በእያንዳንዷ ቀን ኮሳሳነታችን በክፋት መንፈስ ስንፈተንም ወደ እርሷ ስንማጠን ልባችን ብርሃንና መጽናናትን ይታደላል” እንዳሉ ያስታውሳል።
ቅሱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የእምነት ዓመት እንዲሁም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ ጅማሬ 50ኛው ዓመት ምክንያት የሚከናወነው መንፈሳዊ እንዲሁም የአውደ ጥናት መርሃ ግብሮችን ሁሉ ለማርያም አማላጅነት ለማማጠን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመፈጸም ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “እግዚአብሔር በሚኖርበት ቤት ሁሉ ቤተኞች ነን፣ ክርስቶስ በሚኖርበት ቤት ሁሉ ወድማማቾችና እህታማቾች እንጂ ስደተኞች አይደለንም። ማርያም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት የቤቷን በር በመክፈት ወደ ልጅዋ ፈቃድ ለመግባት እንድንችል ትመራናለች’ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.