2013-02-22 14:04:32

ሱባኤ በአገረ ቫቲካን
ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ ቸልተኝነትና አልቦ ጥልቅነት የዘመኑ ባህል እውነተኛ ክፋቶች


RealAudioMP3 በዚህ በተገባው ዓቢይ ጾም ምክንያት እንደ ተለመደው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የሮማዊት ቅድስት ካቶሊካዊት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስትያን አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች በማሳተፍ የሚካሄደው እ.ኤ.አ. የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠቃለለው መንፈሳዊ ሱባኤ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፣ የዚህ መንፈሳዊ ሱባኤ ሰባኪ እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተሰየሙት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ትላትና፦ እርቅ ንስሃ አልቦ እግዚአብሔርነትና ባዶነት በተሰኙት ነጥቦች ላይ ባተኮረ አስተንትኖ በመቀጠል፣ ሰብአዊ ውሱንነት ይዞት የሚጓዘውን የአካልና የሞራል ስቃይ ወደ እግዚአብሔር ማቅረብና ኃጢአት የግልና ከሰብአዊ ነጻነት የሚመነጭ መሆኑ በማበከር፣ ኃጢአት ገዛ እራስ በገዛ ፈቃድ ከእግዚአብሔር ማራቅ ማለት መሆኑ ሲያብራሩ፦ “ኃጢአት በቅድሚያ አንድ ተጨባጭና በተለይ ደግሞ ቲዮሎጊያ ጉዳይ ነው። ሥነ አዕምሮአዊ ገጽታ ያለው ነው። በተለይ ግን ቲዮሎጊያዊ ጉዳይ በመሆኑ ሃጢአተኛ ስል እግዚአብሔር ያለው ግንዛቤ ምክንያትም ፈጽሞ የንስሃ ምሥጢር መቼም ቢሆን በሥነ አዕምሮአዊ ትንተና የሚተካ አይደለም” ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረውም የሙጥኝ ብለን ከምንይዘው ነገር ሁሉ ተላቀን ድካምና አቀበት ያለው ቢሆንም ቅሉ የምንከተለው የገዛ እራስ መንገድ ትተን እንድንለወጥ የተጠራን ነን። ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ይኸንን ሃሳብ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ የጻፋት ሁለተኛይቱ መልእክት ላይ በማተኮር በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ግኑኝነት በሕገ ነክ ቃላት መሠረት እንደሚያበክረውም ሲገለጡ፦ “ካታላሶ ወይንም ካታላገ የሚል ቃል ቅዱስ ጳውሎስ የተጠቀመበት ግሪካዊ ቃል በመካከላቸው መግባባት የተሳናቸው ተጻራሪ አካላት ማስታረቅ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ ይኽ ቃልና የቃሉ ተግባርም በሁሉም አገሮች ሕገ መንግሥት ዘንድ ማእከላዊ ሥፍራ የተሰጠው ስለዚህ መለያየትና ፍች የሚመለከተው ዳኛ መግባባት ለተሳናቸው ፍች ብቻ አማራጭ መንገድ አድርገው በዳኛ ፊት ለፍች ውሳኔ የሚቀርቡትን በቅድሚያ ለማስታረቅ የሚቻል መሆኑ ለማስታረቅ ይሞክራል፣ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ቃል ኪዳናዊ ትስስር በኃጢአታችን አማካኝነት ለፍች አደጋ ይጋለጣል” ላለ መፋታት የሚደረገው ጥረት አድካሚና ምኅረትና ይቅርታ የሚጠይቅ ነው። አዲስ ሰው የሚያደርገን በመሆኑም ጉዞው ቀላል አንዳልሆነ ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ ሲያስረዱ፦ “በኅብረተሰብ ዘንድ በአዲስ መንፈስ ተነቃቅቶ አዲስ ጅማሬ ለማረጋገጡ እድል ቦታ የማይሰጥ አዝማሚያ ይታያል። በሕግ ሂደት የበደለ የፈጠረው መለያየት ለማስወገድ ቀድሞ የነበረው ትሥሥር እንዲመለስ የማድረግ ጥረት ይታያል። ሆኖም ግን የበደለው ቢታረቅም በዳይ መሆኑ የሚለየው ማኅተም እንዳለ ሆኖ ይቀራል። በቅዱስ መጽሓፍ ግን የበዳይ ማኅተም ብሎ ነገር የለም። በነቢይ ኢሳያስ ዘንድ ኃጢአትን ሁሉ በመተው ያንን ኃጢአት ፈጽሞ ዳግም የማይመለከት ኃጢአቱን እርግፍ አድርጎ የሚደመስስ የእግዚአብሔር ምስል እናገኛለን” ካሉ በኋላ ወደ ሁለተኛው የሱባኤው አስተንትኖ በመግባትም ብፁዕነታቸው ኢህላዌነትና ባዶነት ይኽም አለ እግዚአብሔር ማለት መሆኑ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 14ና ምዕራፍ 53 ላይ በማተኮር ኢኅላዌነት መናፈቅን የሚያስከትል ሲሆን ባዶነት የወቅታዊው ባህል አቢይ ነቀረሳ መሆኑ ሲያድረዱ፦ ቸልተኛነት፣ ኣልቦ ጥልቅነትና ከንቱነት። ባዶነት ምንም ነገር የማይናፍቀው የማይጠባበቅ መንፈስ የተካነው ነው። ስለዚህ እኛ (መንፈሳዊ መሪዎች) በሐዋርያዊ አገልግሎታችን ይኸንን ዓይነቱ ኢእግዚአብሔርነት (አለ-እግዚአብሔር) ባህል ፊት ለፊት እንገጥማለን” ከዚህ ጋር በማያያዝም ብዙውን ጊዜ እውነተኛ አማኝ የሚሰማው የእግዚአብሔር ዝምታ (ጽሞና) ላይ በማተኮር፦ “ለብ ባለው መንፈስ ተስፋ በመቁረጥ ዘንድ የተሰማንን የእግዚአብሔር ጽሞና (ዝምታ) ወይንም የኢእግዝአብሔርነት (አለ እግዚአብሔርነት) መንፈስ እናስታውስ። ይኽ ደግሞ እግዚአብሔር ከአድማስ ተገለዋል ማለት ሳይሆን የእርሱ ዝምታ ወይንም ጽሞና እኛ የሚሰማን መንፈስ ነው። ምክንያቱን ማዳመጡ ስለ ሚሳነን ነው። እኛ ብፁዓን አቡኖች ውሉደ ክህነትን እናስብ፣ ብዙ ካህናቶቻችን ይኸንን የአለ እግዚአብሔርነት መንፈስ ተጋርጦባቸው እናያለን። ምናልባትም ከእኛ የሚጠብቁት ትብብርና ድጋፍ ከማጣት የሚኖሩት ተመክሮ ሊሆን ይችላል። ይኽ ደግሞ ሁላችን የቅድት መንበር የበላይ አካላ ብፁዓን ካርዲናሎች ከመሆናችን በፊት በተለያዩ ሰበካዎች ያገለገልን ብፁዓን አቡናት በመሆናችን ይኸንን የውሉደ ክህነት ተመክሮ በቅርብ የምናውቀው ጉዳይ ነው” ዘማሪው ዳዊት በእግዚአብሔር ዝምታ ከተመክረ ባኋላ በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 22 ”እንተ ግን መለስክልኝ” ይላል፣ በዚህ አማካኝነትም ጸሎት ምስጋና በመሆን የባዶነት መንፈስ ሲሰማን በእርሱ ላይ መታመን ያለው እርካታና ብሎም ልመናችን አለ ምላሽ የማይቀር መሆኑ ያረጋግጥልናል።
“ወቅታዊው ኅብረተሰብ ብቸኝነት ስቃይ የተከናነበው፣ በብቸኝነት የሚኖር ብዙ ሕዝብ። ዓለማችን በብቸኝነት መንፈስ የተጠቃ የብዙ ሕዝብ ጋጋታ የሚታይበት ነው። በክርስትናው መንፈስ ስቃይ፣ የዚያ ገዛ እራሱን በትህትና ዝቅ በማድረግ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ወደ ሰው ልጅ በወረደው እግዚአብሔር በመተርጎም ይኽ ለብዙዎች እንቅፋት የሆነው የስቃይ ትርጉም ብቸኝነት ጽሞና ተገሎ መኖር የሚያስከትል የእግዚአብሔር ጽሞና ሞት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተኖረ ተጨባጭ ሁነት ነው። በእርሱ አማካኝነት ብቻ ነው የምንረዳው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.