2013-02-20 15:43:05

የአፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ለሰብአዊ እድገት አገልግሎት


ቤተ ክርስቲያን በወቅታዊው የአፍሪቃ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ ችላ የምትል ተገላ የምትኖር አለ መሆንዋ የመላ አፍሪካና ማዳጋስካር የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ጉባኤ በጋና ርእሰ ከተማ “ተገቢና ትክክለኛ አመራር የጋራ ጥቅምና ዴሞክራሲያዊ ለውጥ” በሚል ርእስ ሥር የተደረሰ ሐዋርያዊ መልእክት የዚህ የመላ የአፍሪቃና የማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ሊቀ መንበር የዳር ኤስ ሳላም ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፖልይካርፕ ፐንጎ በይፋ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ይህ የመላ አፍሪካና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የአፍሪካና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ላካሄዱት ሁለተኛው ሲኖዶስ መሠረት በማድረግ የደረሱት የአፍሪቃ ቃል አማሕላ የተሰየመው ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በማስደገፍ ማኅበራዊ ጥቅም፣ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ መልካም መስተዳድር ማነቃቃት የአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ አስፈላጊ ጉዳይ ነው” የሚል ሃሳብ የሰፈረበት ብፁዕ ካርዲናል ፐንጎ ያቀረቡት ሐዋርያዊ መልእክት፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ መልካምና ተገቢ መስተዳድር ዴሞክራሲና ማኅበራዊ ጥቅም ለመሻትና ብሎም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሕንጸት በማቅረብ ይኸንን ዓላማ የምታነቃቃ መሆንዋ በመግለጥ፣ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የዴሞክራሲ ሥርዓት ለውጥ በስፋት በተረጋገጠት በ 1990 ዓመታት እንዳቀረበችው የሕንጸት ድጋፍ በመቀጠል በአሁኑ ወቅት በሚከሰቱት ለውጦች ሁሉ ቅርብ በመሆን ለበለጠ ለውጥና መሻሻል ሕንጸት በመስጠት ሐዋርያዊ ተልእኮዋን እንደምታከናውንም ሐዋርያዊ መልእክቱን በይፋ ባቀረቡበት ወቅት እንዳመለከቱ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.