2013-02-20 15:36:47

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የእውነት ሥራ ተካፋይ


RealAudioMP3 “የፍቅር ቤተ ክርስቲያን የእውነት ቤተ ክርስቲያን ነች” ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው እንደ ተመረጡ የጴጥሮሳዊ ስልጣናቸው ማእከል የወንጌል እውነት መመስከር የሚል በማድረግ ይኽ የመረጡት ቅዉም ሃሳብ ገና ካህን ጳጳስ ከዛም ለካርዲናል ማእርግ ሲሰየሙም የጵጵስና ተልእኮአቸው መለዮ ከሦስትሰኛይቱ የዮሓንስ መልእክት ቁጥር ስምንት “የእውነት ሥራ ተካፋዮች” የሚል በማድረግ ያገለገሉ መሆናቸው ሲገለጥ። ስፍር ቁጥር የሌላቸው የተለያዩ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ተሰብከዋል፣ የተለያዩ የአስተሳሰብ እንቅስቃሴዎች ታይተዋል፣ ሆኖም የክርስቲያን መለኪያ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነትንና ሃሰትን ለመለየት የሚያበቃ የሰጠን መመዘኛ ነው። እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ገና የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ራትዚንገር ይኸንን የሚያጎላ ወቅታዊው አምባገነናዊው ተዛማጅ ባህል ለቤተ ክርስቲያን ተጋርጦ መሆኑ ባሰሙት ስብክት በማበከር፣ እኚህ ከር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊው ቀጥለው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ የተመረጡት፦ “የእውነት ሥራ ተካፋይ፣ የእውነት መስካሪ” በሚል ሃሳብ በመመራት ያገለገሉና ይኽንን ሐዋርያዊ መርህ በተመስጦና በአስተንትኖ ጸላይ ሕይወት የሚያከናውኑ ታላቅ የቲዮሎጊያ ሊቅ ናቸው።
እ.ኤ.አ. ታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ለቅርብ ተባባሪዎቻቸው የቅድስት መንበር ለአበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች ባሰሙት ስልጣናዊ አስተምህሮ፦ “የእውነት ገዢዎች ሳንሆን በእውነት የተገዛን፣ እርሱም እውነት የሆነው ክርስቶስ በእጃችን ይዞ እርሷን ለመፈለግ በምናደርገው የተመስጦና የተማራኪነት ጉዞ በመምራት በጽናት ይደግፈናል። በእጆቹ መመራት ነጻ የሚያደርግ ሲሆን፣ በሌላው ረገድ ደግሞ እርግጠኞች ያደርገናል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ስለዚህ እውነት አንድ አካል እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በቀዳሚቷ Deus caritas est-እግዚአብሔር ፍቅር ነው” በተሰየመው አዋዲ መልእክታቸው ዘንድ “በክርስትና ጅማሬ ሥነ ምግባራዊ ውሳኔ ወይንም አንድ ትልቅ አስተሳስብ ሳይሆን ከአንድ አካል ጋር መገናኘት” የሚል መሆኑ ያረጋግጣሉ። እ.ኤ.አ. ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ባቀረቡት የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ የሚሳተፍ ሁሉ መከራ ስቃይ ስደት ተቃውሞ ሁሉ መጋፈጥ ይኖርበታል። ምክንያቱ የዚህ ዓለም ስልጣናትን ሁሉ አልገዛም እምቢ የሚል ነውና” እንዳሉ ያስታውሰሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እውነት ከፍቅር ሳይነጥሉ እውነትና ፍቅር ተያይዘው የሚሄዱ መሆናቸው በማስገንዘብም፣ አለ እውነት ፍቅር ስሜት ብቻ ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ ፍቅር ባዶ ይሆናል። እውነት የሚያገል ባህል ፍቅርን ለአደጋ ያጋልጣል። ስለዚህ እምነት ወደ እውነት የሚመራ ነውና በእምነት ወደ እውነት በእውነት ላይ ወደ ተገነባው ፍቅር እንደሚመራን የካቶሊክ ሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተና አባላትንም ጭምር እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ተቀብለው ባሰሙት ሥልጣናዊ ትምህርት፦ “እውነትን በስምምነት ቅቡል በሚሆን ኮሳሳ በቀላሉ ለመቆጣጠር በሚቻል ሃሳብ ሲተካ ክርስትና ግን በፍልስፍናዊ ሥነ ምግባርም ይሁን እውነትን ለማሳወቅ በቅድመ ሁኔታ የተቀመሩ መፍትሔዎች የሚደረድር ሳይሆን ታማኝና የተለያዩ በሁሉም ዘርፍ መፍትሔ ሊሆን የሚችል በሥነ ምርምር የተደገፈ በግብረ ገብ የተመራ ተስፋ የሚጠቁም ተጨባጭና ትክክለኛ መፍትሔ የሰው ልጅ አእምሮ የሚሻውን ያቀርብልናል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
እ.ኤ.አ. ሰነ 5 ቀን 2006 “ዓ.ም. በእምነትና በምርምር መካከል ያለው ተወያይ ግኑኝነት፣ በቅንነትን በተገቢና በጽናትና ጥብቅ በሆነ መንገድ ከተመራ በማንኛውም ዓይነት የሚሰበከው እግዚአብሔር ሳይሆን ገዛ እራሱ የእውነተኛ ስብእና በሙላት በሚገልጥልን በጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ አማካኝነት በሚገልጠው እግዚአብሔር ላይ ለሚጸናው እምነት ውጤታማና አሳማኝ ግንዛቤ እንዲኖረን ይደግፈናል” ሲሉ ለሮማ ሰበካ እምነትና ምርምር በተሰየመው ርእስ ሥር አካሂዶት ለነበረው ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.