2013-02-18 15:21:02

የዓብይ ጾም ሱባኤ በአገረ ቫቲካን


RealAudioMP3 የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በሰባኪነት የሚመሩት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የቅድስት ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ ብፁዓን ካርዲናላት ብፁዓን ጳጳሳት የሚሳተፉበት እ.ኤ.አ. እፊታችን የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው የዓቢይ ጾም ሱባኤ ትላንትና በሐዋርያዊ መንበር በሚገኘው እመ መድኃኔ ዓለም ቤተ ጸሎት በይፋ መጀመሩ ለማወቅ ሲቻል፣ ብፁዕነታቸው ባቀረቡት በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ስብከት፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደ ሙሴ ለሕዝበ እግዚአብሔር ይማጠናሉ” በማለት ቀዳሜ የስብከቱ አስተንትኖ የዓቢይ ጾም ቀዳሜ እሁድ ሁለተኛ ጸሎተ ዘሠርክ በማስቀጠል ቅዱስ መጽሐፍ አስደግፈው የቅዱስ አባታችን ኅልውና በመጻኢ የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ምን እንደሚመስል ሲያብራሩ፣ ኅልውናው አስተንተናኝ ጸላይ እርሱም የሙሴ ምስል የሚያንጸባርቅና የሚኖር ሙሴ ከአማሌቃውያን ጋር ሲዋጋ ለሕዝበ እግዚአብሔር ለመጸለይ ወደ ተራራ መውጣቱን የሚያስታውስ ይኸንን ሁነት የሚኖር ኅልውና መሆኑ ሲያብራሩ፦ “ይኽ የሙሴ ምስል ቀዳሚው ዓላማ የማማለድ የማማጠን ተግባር ነው። እኛ በተራራው ሥር አቧራና አማሌቅ ባሉበት እንቀራለን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፉት ስምነት ዓመት በዚህ ተራራ ሥር ከእኛ ጋር በመሆን እንዲሁም ወደ ተራራው በመውጣትም ስለ እኛ ተመጽነዋል ጸልየዋል። ከአሁን በኋላ ግን በተራራው ጫፍ ላይ በመሆን ስለ እኛ ይማጠናሉ” በማለት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መጻኢ በቤተ ክርስቲያን ህላዌ ምን እንደሚመስል ከተነተኑ በኋላ፣ ወደ የሱባኤው ማእከላዊ ነጥብ በመዝለቅ፦ “ሱባኤ ነፍሳችን ከምድራዊ ሁነት ከኃጢአት ከከንቱነት ከአሉ ባልታና በተለይ ደግሞ ውስጣዊ ጆሮአችንን ከሚስቡ ነገሮች ሁሉ የምንለይበት ወቅት ነው” ብለዋል።
ጸሎት በመዝሙረ ዳዊት ሥር፦ “ጸሎት፣ እስትንፋስ ነው። ለሕይወታችን እስትንፋስ እንዳለው አስፈላጊነት ጸሎትም እንዲሁ ነው። መጸለይ ማሰብ ማለት ነው። ይኽም ልክ እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር የሚለንን ሁሉ በልባችን የምናቅብበት እግዚአብሔርን ለማወቅ የምንገለገልበት መሣሪያ ነው። መጸለይ ከእግዚአብሔር ጋር መታገል ማለት ነው። በጭለማ ልብ በሚደነድንበት ወቅት ጭኾታችን ምሬታችንን ወደ እግዚአብሔር ከፍ የምናደርግበት መሆኑና መጸለይ ማፍቀርም ማለት ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የማንቅፍበት በእርሱ እቅፍ ሥር የምንሆንበት መሣሪያ ነው። ጸሎት የሁለት ፍቅረኛሞች ዓይን ልብ በጽሞና የሚገናኙበት ሁነት ነው” ካሉ በኋላ አክለውም ፈላስፋ ፓስካልን ጠቅሰው፦ “በፍቅር ወይንም በማፍቅረ ዘንድ ጽሞና ከቃል በላይ ጥልቅ ተናጋሪ ነው። ሁለት እውነተኞች ፍቅረኞች ተራው ዓለም የሚለው ልሙድ የሆነው የማፍቅርና የመፈቀር አነጋገርና አገላለጥ ማዶ በልጦ በመሄድ ዓይን ለዓይን በጽሞና የሚተያዩበት ልብ ለልብ የሚገናኙበት ተግባር ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.