2013-02-18 15:26:12

ብፁዕ ካርዲናል ዉኤርል፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ እግዚአብሔር በሚጋርደው ዓለም ዳግም ወንጌልን ያነቃቁ


RealAudioMP3 ተዛማጅ ባህል በተስፋፋበት ዓለም ዳግም እግዚአብሔር ማቅረብና ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ለመገናኘት እንደሚቻል መምራት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተቀዳሚ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ኃላፊነት በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና በዓለም የጎላበት የተልእኮ ተግባር መሆኑ የዋሽንግተን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዶናልድ ዉኤርል ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ የዛሬ አምስት ዓመት በፊት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት አስታውሰው በዚያኑ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት የካቶሊክ ምእመናን ብቻ ሳይሆን፣ የመላ የአገሪቱ ሕዝብ የማረኩ እየተስፋፋ ላለው ማመን አለ ማመን ያው ነው። እሴቶች ብሎ ነገር የለም የሚለው ተዛማጅ ባህል ለመጋፈጥና ለማሸነፍ የሚያበቃው አዲስ ጰራቅሊጦስ እንዳነቃቁ ብፁዕነታቸው በማስታወስ ለዚህ ዓለማ የሚያበቃው አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ፈር በማስያዝም ለዚህ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያለመ ያቋቋሙት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጠቅሰው፣ ያለንበት ወቅት በቤተ ክርስቲያን ሕይወት አዲስ ሁነት ነው ብለዋል።
ለገዛ እራሳችን በመላ ቤተ ክርስቲያን ላለንበት ዘመን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም በማነቃቃት ሁሉ በቃሉ እንዲማረክ ሁሉ እምነቱን በቃልና በተግባራ ለመኖር የሚያበቃው መንገድ ያሳዩ የጠቆሙ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ናቸው በማለት ቅዱስ አባታችንን ገልጠው፣ ይኽ በተዛማጅ ባህል የተጠቃው ዓለም ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ዳግም እንዲገናኝ በሕይወቱ ቦታ እንዲሰጠው ለማድረግ የሚደግፈውና የሚመራው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማነቃቃት፣ የመሩ ናቸው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለምን ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣናቸው በነጻነት በገዛ ፈቃዳቸው ለማስረከብ እንደወሰኑ ለብፁዓን ካርዲናሎች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ለወቅታዊው ዓለም የበቃ ር.ሊ.ጳ. ማለትም በቅድሚያ ወቅቱ ዓለም የሚያቀርበው ጥያቄ ሂደትና ሁለ ዘርፈ ምንጣቄውን በመለየት አብሮ የሚራመድ ማለትም ማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ፍጥነት ጋር ለመራመድ የሚችል፣ በእድሜ ያልገፋ መሆን እንዳለበት የሚያሳስብ ነው። ከወቅቱ ዓለም ጋር ለመራመድ የሚችል መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን ከሰጡት መግለጫ ለመገንዘብ እንችላለን በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.