2013-02-14 13:04:48

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚለቁ የሚነግረው ዓለምን ያንቀጠቀጠው ዜና ከመከሰቱ ለመጀመርያ ጊዜ ለሕዝብ ቀርበው የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ከመጀመራቸው በፊት በብዙ ጉጉትና ስሜት ይጠብቃቸው የነበረው ሕዝብ ብጭብጨባ ሲቀበልዋቸው ስለሁኔታው ለመግለጥ ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ብለው ስለወሰኑት ጉዳይ ለመንገር በጀመሩበት ወቅት ጭብጨባው እንደገና በመንጐድጉዱ ጥልቅ ስሜት በሞላው ቃና ለድጋፋችሁ እጅግ አመስግናለሁ በማለት ዋና መል እክትን እንዲህ ሲሉ አስተላለፉ፣ ጌታ በ19 ሚያዝያ 2005 ዓም ያለበሰኝን ሥልጣን በገዛ ፍቃዴ ለመተው እንደወሰንኩኝ ለመግለጥ እወዳለሁ፣ ይህንን ያደረኩት ደግሞ በሙሉ ነጻነቴና ለቤተ ክርስትያን በጎ ነገር መሆኑን ለመግለጥ እውዳለሁኝ፡ ለረዥም ጊዜ ከጸለይሁና በእግዚአብሔር ፊት ኅልናየን ከመረመርኩ በኋላ ውሳኔው የሚያስከትለውን ከባድ ነገር በማውቅ ሆኖም ግን የቅዱስ ጴጥሮስ ኃላፊነት የሚያለብሰውን ሥልጣን እና የሚጠይቀውን ኃይል በሚገባ ለመወጣት አለመቻልን በመገንዘብ ነው፣ ቤተ ክርስትያኑ የኢየሱስ መሆንዋ በሚሰጠኝ ኃይል እና በሚያበራልኝ እርግጠኝነት ግፊት ይህንን ውሳኔ አደረግሁ፤ ይህንም የእርሱን መሪነትና እንክብካቤ ዘወትር እንደማይለያት ያረጋግጥልናል፣ ሁላችሁንን ከኔ ጋር በማበር ስላቀረባችሁት ስለ ፍቅራችሁንና ስለ ጸሎታችሁ ለማመስገን እወዳለሁ፣ በተያዝናቸው ቀናት ሁሉንን በአካል ለማድረግ አለመቻልየን ተረዳሁት፤ ሆኖም ግን የቤተ ክርስትያንዋ ጽሎትና ፍቅር እንዲሁም የእናንተው ጸሎት ምኑን ያህል እንደረዳኝ ተረጅቻለሁ፣ ስለ እኔም ይሁን ስለቤተ ክርስትያኒትዋ እንዲሁም እኔን ስለሚተካ ር.ሊ.ጳ ለመጸለይ እንድትቀጥሉ ይሁን፤ ጌታ ከእናንተ ጋራ ይሁን ሲሉ በዚሁ ቀናት ስለአውጁት ሁኔታ መብራርያ ሰጥተዋል፣
ከዛም በመቀጠል የሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርታቸውን እንዲህ ሲሉ አቅረበዋል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ዛሬ በአመድ ሮብ የዘመነ ጾም ሥርዓት እንጀምራለን፣ እነኚሁ 40 የጾም ቀኖች በዓለ ትንሣኤን በሚገባ ለመቀበል ያዘጋጁናል፣ ስለሆነም በመንፈሳዊ የሕይወታችን ጉዞ ይህ ጊዜ እጅግ ክቡርና አስፈላጊ ነው፣ 40 የሚለው ቍጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ግዜ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፣ በተለይ የሚያመለክቱት ሕዝበ እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር ለመሆን በምድረበዳ ያደረገውን የአርባ ዓመት ጉዞን ነው፤ ሆኖም ግን ለረጅም ጊዜ የጌታ ኪዳን ለማፍረስ ያሳለፉት የፈተና ጊዜ እስካሁን ያለ ነው ለማለት ይቻላል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኤልያስ ነቢይ በእግዚአብሔር ተራራ በሆነው የሆረብ ተራራ ለመድረስ አርባ ቀናት ፈጀበት፣ በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝባዊ ተል እኮውን ከመጀመሩ በፊት በምድረበዳ በዲያብሎስ እየተፈተነ ያሳለፋቸውን ቀናትም አርባ ነበሩ፣ በዛሬው አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እፊታችን እሁድ በወንጌል የምናነበውን የእግዚአብሔር ልጅ ምድራዊ ሕይወት የጀመረበት የአርባ ቀናት ጾም ልናስተነትን ነው፣
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሄደው ምድረበዳ የጸጥታ የድህነት የሰው ልጅ ምንም ዓይነት ቍሳዊ ድጋፍ የማያገኝበት በኑሮ ውስጥ ፈታኝ የሆኑ የሕይወት ጥያቄዎች የሚደቀኑበት ሆኖም ግን እግዚአብሔር ለማግኘት በቀላሉ የሚቻልበት ቦታ ነው፣ ነገር ግን ምድረበዳ የሞት ቦታ መሆኑንም መዘንጋት የለብንም፤ ምክንያቱም ውኃ ሕይወት ስለሆነ ውኃ ከሌለ ሕይወትም የለም፣ የብቸኝነት ቦታ በመሆኑም የሰው ልጅ እዛ ላይ ፈተና እጅግ ይከብደዋል፣ ኢየሱስ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል እዛም እግዚአብሔር አብ ያመለከተውን መንገድ ትቶ ዓለማዊውና ቀላሉን መንገድ ለመከተል ይፈተናል (ሉቃ 4፤1-13)፣ በዚህም እርሱ አሳዛኝ የሆነ ሁኔታችንን በመሸከም ፈተናዎቻችንን ሁሉ ይቀበላል፤ በዚህም ክፋቱን አሸንፎ ወደ እግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ የሕይወት ለውጥ ጐዳናን ይከፍትልናል፣
ኢየሱስ በምድረበዳ የተቀበላቸውን ፈተናዎች ቀረብ ብለን ስንመለከታቸው እያንዳንዳችን መመለስ ያለብን መሠረታዊ የግል የሕይወት ጥያቄ ያቀርብልናል፣ በመጀመርያው ፈተና ዲያብሎስን ኢየሱስን የሚያቀርብለት ፈተና ረኃብን ለማቆም ድንጋይን ዳቦ እንዲሆን የሚጠይቅ ነበር፣ ኢየሱስም ይህን ፈተና የሰው ልጅ በዳቦ ብቻ እንደማይኖርና በእግዚአብሔር ፍላጎት ረሃብ የሚሆነው ቃል ካላገኘ ሊድን እንደማይችል ይገልጽለታል፣ በሁለተኛው ፈተና ዲያብሎስ ለኢየሱስ የሚያቀርበው ነገር የሥልጣን ነው፤ በአንድ ታላቅ ተራራ ወስዶ የዓለምን ሥልጣን ያሳየዋል፣ ሆኖም ግን ኢየሱስ ይህ መንገድ የእግዚአብሔ መንገድ አለመሆኑንና የሰው ልጅ በዚህ እንደማይድን ነገር ግን የመስቀል የትሕትና እና የፍቅር መንገድ እንደሚያድነው ይገልጣል፣ በሶስተኛውም ፈተና ዲያብሎስ ኢየሱስን ከታላቁ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ሕንጻ ወደ ታች እንዲወረወርና እግዚአብሔር በመላእክቱ ስለሚጠብቀው ምንም እንደማይሆን በመግለጥ ነበር፣ ከእነዚሁ ሶስት ፈተናዎች ውስጥ ምን መል እክት እናገኛለን? እግዚአብሔር መሣርያ አለማድረግ ለገዛ ራሳችን ጥቅም እንዳናውል ማለትም ለገዛ ራሳችን ክብርና ድል መቀዳጀት እንዳይሆን ያሳስባል፣ ይህም ማለት ራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አለመኖር ማለት ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዳችን እግዚአብሔር በሕይወቴ ውስጥ የትኛውን ቦታ ይይዛል? ጌታ እርሱ ነው ወይንስ እኔ? የሚል ጥያቄ ማቅረብ አለብን፣ እግዚአብሔር በሥራችን የማድረግ ፈተናን ለማሸነፍ ለእግዚአብሔር የመጀመርያ ቦታን መስጠትና ሁሌ እንዳአዲስ ክርስትናዊ ሕይወትን መጀመር ዋነኛ ተግባራችን መሆን አለበት፣ ተለወጡ፤ ንስሐ ግቡ የሚለው የጾመ አርባ መልእክት የኢየሱስ ወንጌል የሕወታችን መሪ ይሁን ማለትም እግዚአብሔር እንዲለውጠን ሁሉን በእርሱ መተው የሕይወታችን ገንቢዎች እኛ ብቻችን መስሎ የሚታየንን ነገር መተውና ፍጡራን መሆናችንን ማወቅ እንዲሁም በእግዚአብሔርና በፍቅሩ እንደምንጠጋ ተረድተን በምሕረቱ ብቻ ሕይውታችን በእርሱ ልናገኛት እንደምንችል መረዳት ያስፈልጋል፣ ይህም የሕይወታችን ምርቻዎች በእግዚአብሄር ቃል ብርሃን እንድናደርጋቸው ያሳስበናል፣ በዛሬው ዘመናችን በክርስትያን እምነት የተመሰረተ ሕይወትና ባህል እንዳለ በመገመት መጓዝ አይገባም፤ በክርስትያን ቤተ ሰብ ውስጥ የተወለድንና በክርስትያናዊ ትምህርት ያደግንም ብንሆን፤ ነገር ግን በየዕለቱ ክርስትያን የመሆናችን ምርጫ ምሳደስ አለብን፣ ይህም ማለት ያለነው ዓለማዊነት ባሸነፈው ባህል እና የዘመናችን ሰዎች በሚያቀቡልን ክህደታዊ ፍርድ ፊት ለእግዚአብሔር ቅድሚያ መስጠት እንዳለብን ማወቅ ያስፈልጋል፣
የምንኖርበት ሕብረተሰብ ለተለያዩ ፈተናዎች ክርስቲያኑን ሲፈታተን ስንመለከት ይሕም ብዙዎችን በግልና በሕብረተሰቡ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች ናቸው። ክርስቲያናዊ ጋብቻ እንደሚጠይቀው በአንድ ትዳር ጸንቶ መቆም ቀላል አይደለም፣ በየዕለቱ በይቅርታና መንፈስ መኖርና ለጸሎትና ውስጣችንንም ለማዳመጥ ግዜን መውሰድ፣ ብዙኅኑ በተስማማበትና በሚቀበለው አመለካከት አልስማማም ወይም አልቀበልም ማለቱ ከባድ ነው። ምሳሌ፣ ያልተፈለገ ጽንስ ማስወረድ፣ በኃይለኛ በሽታ የሚማቅቁትን እንዳይሰቃዩ መግደልና፣ በዘር ከሚተላለፉ በሽታዎች የሚወለደውን ሕፃን ለማዳን ገና በጽንስ ላይ እያለ የሚደረጉ ሕክምናዎች ናቸው፣
እነዚህ ፈተናዎች በየዕለቱ ያለንን እምነት በጎን እንድናስቀምጥ ሲያደርጉ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንም ግንኙነት መልሱን የምንፈልገው በምንኖረው ሕይወት መልስ እርግጠኝነት እንዲሆን ነው፣ ምሳሌዎችን ብንፈልግ ለለውጥ የሚገፋፉን፤ ሕይወታቸው የተቀየረና የተለወጡ ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆስ መንገድ ላይ፤ ቅዱስ አጎስጢኖስን ስንመለከት አሁንም እኛ በምንኖርበት ሕብረተሰብ የእግዚብሔር ቅድስና ፍቅር ምህረቱና ስራው አሁንም በብዙዎች ሰዎች ሲሰራ እናያለን። እግዚአብሔር የሰውን ልብ ማንኳኳት እንደማይሰለችና እንደማይደክመው ነው። በሕብረተሰብና በባሕል አመለካከት ከተወሰደ ግን ጥንት በመባል የተዋጡ ቃላቶች ናቸው። እንደ የራሻው ኦርቶዶክስ ፓቨል- ፍሎረንስኪ ብንመለከት የእውቀት ትምህርቱ በሕይወት ሞያው ሳይንሳዊ ቢሆንም እውቀቱ በልጅነቱ ት/ቤት የተማረውን ት/ክርስቶስን ሲቃወም አንድ ደረጃ ላይ ሳይንሳዊው ፍሎረንስኪ ያለ እግዚአብሔር መኖር አይቻልም በማለት ሕይወቱን እስከመቀየርና መነኩሴም እንደሆነ እናውቃለን፣
ሌላው ኤቲ ሂለሱም ወጣት ትውልድዋ አይሁድ ሆላንዳዊ በአውስኪዝ የሞተች ታሪክዋን ስንመለከት በመጀመሪያ ከእግዚብሔር በጣም ርቃ ትኖር እንደነበር የምትረዳውም እኔነቷን ውስጥዋን በጥልቀት በመመልከት ስትጽፍ በኔ ውስጥ የጠለቀ ኩሬ አለ ይህ ኩሬም እግዚአብሔር ነው ብላ ገልጻለች። አንዳንዴ ወደ ኩሬው በቀላሉ እንደምትደርስ ሲሆን ብዙውን ግዜ ግን ድንጋይና አመድ ኩሬውን እንደላበሱ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ተቀብራል። ከተቀበረበት ማውጣት ያስፈልጋል ገጽ (97) ፅፋለች። ሕይወታ ሰላም የሌለውና የተረበሸ ነበር። እግዚብሔርን የተገናኘችው በ900 ክ/ዘመን በሾአ ግዜ ነው። ይህች ደካማና ደስተኛ ያልሆነች ወጣት ወደ እምነት በመግባት በውስጣዊ ሰላምና ሙሉ ፍቅር ያላት ሴት ስትለወጥ ሁሌ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቃ እንደምትኖር በማረጋገጥ ገለፀች፣
የዘመኑ አመለካከትና አስተሳሰቦች የደለልዋት እውነትን በመፈልግ እምነትን ያገኘችና የመሰከረች የአሜርካዋ ተወላጅ ዶሮቲ ደይ ነች። በሕይወት ታሪኳ ጽሑፍ በተወችው ምስክርነት ብዙውን ግዜ ለወደቀችበት ወጥመድና ፈተና በፖለቲካ ለመፍታት ትፈልግ እንደነበርና ይህም የማርክስን ሐሳብ በመቀበል እንደነበር ነው። ሰልፍ ከሚያደርጉት ጋር አብራ በመውጣት መታሰርን ትሻ እንደነበርና ሌላውንም እንደሳ እንድያስቡና እንዲከተሏት ትሻ እንደነበር ስትገልፅ ሁሉን ታደርግ የነበረው ከዝና ባሻገር ማንነቷን ለማወቅ ነበር። በእምነት መንገድ መራመድ ጥንታዊና አስቸጋሪም ነበር። የእግዚብሔር ጸጋ ግን ሁሌ ይሰራል። ቤተክርስቲያን አዘውትሮ መሄድና ተንበርክኮ መጸለይን ብዙውን ግዜ እንደትፈልግም ስትገልፅ ይህም በውስጧ የነበረው ስውር የጸሎት መንፈስ ይቃትት እንደነበር ነው። ምክንያቱም በውኑ እንደምትጸልይ ባይረዳትም ግን በቦታው በመሄድ በጸሎት መንፈስ ውስጥ ትገባ እንደነበር ነው። እግዚአብሔር ወደ ቤተክርስቲያን በእውቀትና በመረዳት ደረጃ አድርሶ ሕይወቷን ችግረኞችን በመርዳት አገልግላለች፣
አሁን በምንኖርበት ሕብረተሰብ ብዙዎች ከጌታ ርቀው የነበር ወደ ጌታ የተመለሱ ሲኖሩ አንዳንዱ የጠለቀ የትምህርተ ክርስቶስ ትምህርት ባለማግኘቱ ሲርቅ ከዛም ክርስቶስን በወንጌል በማግኘት ወደ እርሱ ተመልሰዋል። ዮሐንስ በራዕዩ ሲገልፅልን ምዕ 3 ቁ 20 እነሆ በደጅ ሆኜ አንኳኳለሁ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። እኔነታችን እግዚአብሔር እንዲጎበኘው መዘጋጀት አለበት፣ ለዚህም ነው ከግዚያዊና ብልጭልጭ ነገሮች ስጋችን መታሠርና መደለል እንደሌለበት ነው፣
በዚህ በጾመ አርባና የዕምነት ዓመት ክርስትናችንን እናድስ፣ ገለልተኞች ሆነን ከመኖር ለእግዚአብሔር ልባችንን እንክፈትለት የዕለቱን ኑሮዓችንን በሱ ዓይን እንመልከተው። በሌላ አመለካከት የኛን ስግብግብነት በመዝጋት በፍቅር ለእግዚአብሔርንና ለሌሎች መሠጠት ነው። ማለትም የሰው ስልጣንና የመስቀል ፍቅሩን ልዩነታቸው የሰው ስልጣን በቁሳዊ መልካም ሕይወት የሚታይ ሕይወት ሲሆን የመስቀል ፍቅሩ ደግሞ እግዚብሔር በስራውና ሁሌ በሕይወታችን ስናስቀድመው ነው። መለወጥ ማለት ስልጣንና ሹመትን ለማግኘት መታገል ሳይሆን ግን በየዕለቱ በትንንሽ ነገሮች እውነትንና የእግዚብሔርን እምነትና ፍቅርን መፈለግ የሕይወታችን ዋነኛ ነጥብ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.