2013-02-12 11:28:36

ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በገዛ ፈቃዳቸው ከሥልጣናቸው እንደሚሰናብቱ ገልጠዋል፣


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ጠዋት ስለ ቅዱሳን ለመውያየት በጠሩት በኮንቺስተሮ የሚታወቀው የካርዲናሎች ጉባኤ ፍጻሜ ላይ በዚሁ የተያዝነው ወርኃ የካቲት መጨረሻ ቀን እ.አ.አ የካቲት 28 ቀን በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው እንደሚሰናበቱ በላቲን ቋንቃ ለካርዲናሎቹ አስታውቀዋል፣ RealAudioMP3
ቅዱስነታቸው ከሥልጣን የመገለላቸው ሁኔታ ሲገልጹ፤ ሕልናቸው በእግዚአብሐር ፊት በመደጋገም መመርማራቸው እና ከርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ለመገለል በጸሎት እና አስተንትና የተሸኘ ውሳኔ ውስኛለሁኝ ብለዋል። በማያያዝም በዕድሜ መግፋት ምክንያት መንበረ ቅዱስ ጰጥሮስን በሚገባ ለመምራት አካላዊ ኅይል ያንሰኛል መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ለመልቀቅ መሠረታዊ ምኽንያት የሆነኝም ይህ ነው ብለዋል። ይህንን እርምጃ የወሰዱትም ለቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መልካም ሁሉ በማሰብ እና በመፈለግ እንደሆነ አስታውቀዋል፣
ካለፉት ዓመታት አሁን ያለንበት ዘመን ፈጣን እና በየግዜው የሚከሰቱ ሁኔታዎች አስቸኳይ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ይህን ለመስራት ፈጣን እና ሙሉ ኀይል እንዲኖርህ የሚጠይቅ መሆኑም ቅድስነታቸው ተናግረዋል፣ በሙሉ ነፃነት መንበረ ሐዋርያ የቅዱስ ጰጥሮስ እና የሮም ከተማ ጳጳስ ከመሆን በገዛ ፈቃዴ የማይቀለበስ ውሳኔ ወስኛለሁ ብለዋል፣
አንድ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በገዛ ፈቃዳቸው መንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ሲለቁ በታሕሳስ 13 ቀን 1294 ዓም ር.ሊ.ጳ ቸለስቲኖ 5ኛ በኋላ የመጀመርያ መሆኑ ይታወቃል፣
ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ሰባት ዓመታት 10 ወር እና ዘጠኝ ቀናት በኋላ ይህ ፍጹም የማይገመት እና የማይታሰብ እርምጃ በመውስዳቸው በዓለም ዙርያ የመወያያ ርእስ ሁነዋል፣
ይሁን እና የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትርያን ሕገ ቆኖና ዓንቀጽ 322 ከመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ የሚሰናበቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚወስዱት እርምጃ በሙሉ ነጻነት መከናወን እንዳለበት እንደሚያምለክት ይታውቃል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.