2013-02-12 11:31:06

ሁሉንም የሚለውጥ እግዚአብሔር ስለሆነ ክርስቶስን ተስፋ አለመቍረጥ ለሁሉ መስበክ አለብን፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደበባይ የተለመደውን የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ባቀረቡበት ነበር፣ ቅዱስነታቸው ይህንን ሲያሳስቡ፤ “ክርስቶስን ለሁሉም ሰዎች መስበክ የገዛ ራስን ደካማነት ካለመፍራት ይሁን ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሕረት ነው ሁሉን የሚቀይርና የሚያሳድስ” ብለዋል፣ እንዲሁም በዛሬው ዕለት በቅድስት ድንግል ማርያም ዘሉርድ በዓል የሚዘከረውን 16ኛ ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀን እና በኤስያ የሚከበረውን የጨረቃ ርእሰ ዓመት በማስታወስም መልካም ፍልጎታቸውና ሰላምታቸውን ለሁሉንም አቅርበዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ግጻዌ ትናንትና የተነበበውን ወንጌል የመጀመርያዎቹ ሐዋርያት ጥሪ የሚያመለክት ሆኖ ጌታ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ዮሐንስና “ከአሁን ወዲህ የሰው ልጆች አጥማጆች ትሆናላችሁ” ብሎ እንዲከተሉት በጠየቃቸው ግዜ ሁሉን ትተው እንደተከተሉት የሚያመለክት ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ይህንን በመጥቀስ “ሐዋርያት ወንጌልን እስከ አጽናፈ ዓለም ለሁሉም ሰዎች ለመስበክ ተስፋ አይቆርጡም” ሲሉ እያንዳንዳችን ይህንን ክርስቶስን ለሁሉ የመስበክ ሐዋርያነት በሚገባ እንድንወጣ ጥሪ አቅርበዋል፣ በወንጌሉ እንደተመለክተው ጴጥሮስ ሌሊቱን ሙሉ ሰርተውና ለፍተው ምንም ማጥመድ እንዳልቻሉ ሲገልጥ ጌታ ኢየሱስም ይህንን የቅዱስ ጴጥሮስ ተስፋ መቍረጥ ለማበረታታት የሰው አጥማጆች እንዲሆኑ ከመጥራታቸው በፊት ወጥመዳቸውን በቀኝ በኩል እንዲያወርዱ ያዛቸዋል ብዙ ዓሣም ያጠምዳሉ፣ ቅዱስ ጴጥሮስም በዚህ ተአምር ይደነቃል፣ የዚህ ቃለ ወንጌል ዋና መል እክት ሲገልጹ ቅዱስነታቸው “ጌታ ሲጠራና ለሐዋርያነት ሲያዘጋጅ የተጠሩ ሰዎች ብልኃትና ችሎታ ሳይሆን ያላቸውን እምነት ነው የሚመዝነው” ሲሉ የክህነት እና የውሉደ ክህነት ጥሪ የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን ገልጠዋል፣
“የሰው ልጅ የጥሪው ዋና አይደለም፤ ነገር ግን ለመለኮታዊ ጥሪ የሚሰጥ መልስ ነው፣ እግዚአብሔር የጠራ እንደሆነ ሰብ አዊ ደካማነት ሊያስፈራው አይገባም፣ በድህነታችን በሚሠራው የእግዚአብሔር ኃይል ውስጥ እምነት ማኖር አለብን፤ በሚለውጠውና በሚያሳድሰው ምሕረቱ ችሎታ መተማመን ያስፈልጋል” ይህ ምሕረት መልካሙንና መጥፎውን ሁሉ ለመቀበል የተጠራችን ለዚሁ ለምትኖር ቤተክርስትያን መላውን ተልእኮ ይሸኛታል፣ ከሙታን ከተነሳን በኋላ ግን መልካሞቹን ብቻ ትይዛለች፣ በማለት ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.