2013-02-11 15:27:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሠማዕትነት ከመቀበል የሚያፈገፍግ፣ ክርስቲያን ነኝ ለማለት አይችልም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓርብ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሮማ ሰበካ አቢይ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤተ ጠባቂ ቅድስት ድንግል ማርያም ዘትትአምን ዓመታዊ በዓል ምክንያት በዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት ሓዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ እዛው ከሚገኙት ከ 190 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች አለቆችና አበ ነፍሳት ጋር በመገናኘት መሪ ቃል ሰጥተው የዕራት ማዕድ ተቋድሰው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ወደ አገረ ቫቲካን ከተመለሱ በኋላ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ስምንት ሰዓት ተኩል በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ከዘርአ ክህነት ተማሪዎችና አለቆች ካህናት ጋር ጸሎት ዘሰርክ መርተው ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን በቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ አንድ ከቁጥር አንድ እስከ ሶስት ያለው ክፍለ ምዕራፍ አስደግፈውም በሰጡት መለኮታዊ ንባብ እንዳመለከቱት፦ “በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ” በሚለው ቃል ላይ በማተኮር ዘንድሮ የዘርአ ክህነቱ ጠባቂ ቅዱስት ድንግል ማርያም ዘትትአምን ክብረ በዓል እየተከበረ ያለው የእምነተ ዓመት ለየት የሚያደረገው መሆኑ በማስታወስም፣ በአሁኑ ወቅት ብዙ ወጣቶች በክህነት ሕይወት ጌታንና ቤተ ክርስቲያኑን እንዲሁም ሕዝበ እግዚአብሔርን ለማገልገል ለክህነት ሕይወት ሲዘጋጁ ማየቱ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፣ ካሉ በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት መሲሕ ጋር የተገናኘ ጥልቅና ሙሉ የእምነት ስሜት የተሞላው የመጀመሪያ የር.ሊ.ጳ. ዓዋዲ መልእክት በማለት ሰይመው፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ምንም’ኳ ሰው እንደመሆኑ መጠን በድካም ቢገኝም ለክርስቶስ ታማኝ በመሆን ሕይወቱን ስለ እርሱ የሰዋ መሆኑ አብራርተው፣ መልእክቱን እዚህ በሮማ በእምነት ወንድሞቹ በሆኑትና በመላይቱ ቤተ ክርስቲያን ተደግፎ የጻፈው ኩላዊ መልእክት ነው እንዳሉ ኦንዳርዛ ገለጡት።
“ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መልእክቱ በነጠላ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ሰው እንደመሆኑ መጠን የሚናገር በግል ሰብአዊ ኃላፊነት እንጂ በግላዊ ሊቅነት ላይ ተንተርሶ የጻፈው መልእክት አይደለም፣ ከቤተ ክርስቲያን ጋር በሱታፌ የሚናገረ ነው” ካሉ በኋላ፦ “ስቁል ኢየሱስን የማይከተል ክርስቲያን ነኝ ለማለት አይችልም። ስለዚህ ሠማእትነት በማግለል ክርስትናን ለመቀበል የሚቻል አይደለም” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
የክርስቶስን ገጽ ለይቶ ለማወቅ እርሱን ለመከተል እግዚአብሔር የመረጣቸው የፈለጋቸው ካቶሊክ ለመሆን መጠራታችን ጸጋ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ይኸንን ጸጋ ስለ ሰጠን ደስተኞች መሆን አለብን። የእግዚአብሔር እውነትና የፍቅሩ ኃሴት በሙላት ማወቅ ፍጹም ውበት ነው። የተመረጡ የሚለው ቃል ባንድ መልኩ ቅድሚያ የሚያሰጥ በሌላው ረገድ ደግሞ ትህትናን የሚያሰማ ነው። ስለዚህ የክርስትናው ጥሪ ስግብግብነት እኔነት ለሚለው አዝማሚያና ቁሳዊነት እምቢ የሚል ነው። አስመሳይነትን የሚቃወም በመሆኑ ለስደት ተጋልጦ ይገኛል” ካሉ በኋላ፦ “ጌታ በዚህ በምንከተለው መንገድ እንዲደግፈን የሰጠንን ተልእኮ በመቀበል የምንኖረው ሕይወት ምክንያት የሚያጋጥመን መከራ ስደትና ውሁዳን የሚያደረገን ቢሆንም ቅሉ፣ የመልካምነት ኃይል በዓለም በመሆን ስለ ሌሎችና ለሌሎች ይኸንን ኃሴት ለማካፈል ተጠርተናል” እንዳሉ ኦንዳርዞ ገለጡ።
“ክርስትና አብቅቶለታል የሚሉ የኃሰትና የጨለምተኝነት መንፈስ የሚነዙት ቤተ ክርስቲያን በሰው ልጅ ኃጢአትና ለእምነት እምቢ በማለትና እምነትን በሙላት ካለ መኖር በሚመነጨው ኃጢአት አማካኝነት የምትሞት ብትመስልም ለዘለዓለም የሚኖረው ተክለ እግዚአብሔር ስለ ሆነች ይኸንን ዘለዓለማዊነት በገዛ እራሷ ይዛ የምትኖር ነች” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.