2013-02-08 14:56:31

ብፁዕ ካርዲናል ላዮሎ፦ የኢየሱስ ስቃይና ትንሣኤ


RealAudioMP3 “የኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ ስቃይና ትንሣኤ፣ በዮሐንስ ወንጌል መሠረት” በሚል ርእስ ሥር የአገረ ቫቲካን መስተዳድር ልኂቅ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካዲናል ጆቫኒ ሎዮላ የደረሱት በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው ከትላትና በስትያ ሮማ በሚገኘው በዓለም አቀፍ ጳውሎስ ስድስተኛ ቤተ መጻሕፍት በተካሄደው ዓውደ ጥናት ለንባብ መብቃቱ ዓወደ ጥናቱን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።
ከተካሄደው ዓውደ ጥናት ፍጻሜ በኋላ ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፣ የዮሐንስ ወንጌል የሚነካቸው ወቅታዊነታነት ያላቸው ቀጣይ ጥያቄዎች ብቻ ሳይሆን ወቅታዊነቱ የማይሟጠጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ስቃይና ትንሣሴ በተመለከት የሚሰጠው ንባብ ላይ ያተኮረ መጽሓፍ ነው። ኢየሱስ ተሰቃይቷል፣ እርሱም ስለ እኛ ሞቷል ሞትን አሸንፎም ተነሥተዋል፣ ይህ ዜና ብዙ ማስታወቂያ የማይነዘለት እውነተኛ ብቸኛ ዜና ነው፣ ማለትም ብሥራት ነው። በኢየሱስ ስቃይ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ምሉእ ፍቅር ይገለጣል፣ ማለትም ሁሉና ምሉእ የእግዚአብሔር ማንነት ይገለጣል፣ ስለዚህ ማንም ክርስቲያን ይኸንን በሕይወቱ ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ሕይወት ገዛ እራሱን የሚከውንበት እውነት መሆን አለበት” ብለዋል።
“የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ የንጹሕና የቅን ሰው ስቃይ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሕይወት መልስ በግብር ይሰጣል። የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ትንሣኤ ብቻ ሳይሆን ሞቱ ጭምር ለሕይወት መልስ ነው። እግዚአብሔር ሰው በመሆን ስለእኛ መስቀልን በመሸከም ስለእኛ ይሞታል፣ ይኽ ደግሞ እኔ ዕለታዊ መስቀሌን ተሸክሜ ለማደርገው ጉዞ ጥልቅ ትርጉም ይሆነኛል። ሙሉና ፍጹም መልስ መስቀልና ትንሣኤ ነው። መስቀልና ትንሣኤ የማይነጣጠሉ ተጨባጭ ሁነት ናቸው። ‘ክፍ በምልበት ጊዜ ሁሉንም ወደ እኔ እስባቸዋለሁ’ ብለዋል። የዮሓንስ ወንጌል ከመቅድሙ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው በኢየሱስ ስቃይና ትንሣኤ ላይ ያተኮረ ነው። ብርሃን በሞት ላይ ድል ይነሳል ጨለማ ለብርሃን ጆሮውን ከድነዋል፣ የእርሱ በሆኑት ዘንድ መጣ ነገር ግን አልተቀበሉትም ሲል የዮሐንስ ወንጌል የሚያስደምጠን ቃል ስለ ኢየሱስ ስቃይና ትንሣኤ ነው የሚናገረው” ካሉ በኋላ፣ የደረሱት መጽሐፍ ሁሉንም በበለጠ ለሚያውቁ ለሊቃውንትና ለምሁራን ለአበይት የቲዮሎጊያና የቅዱስ መጽሐፍ ሊቃውንት እንዳልሆነም በማብራራት፣ ወደ ክርስቶስ በበለጠ ለመቅረብ ለሚሻ ክርስቲያን ምእመን ሁሉ መሆኑና ማንም ወደ ክርስቶስ ለመቅረብ ለሚሻ ሁሉ ወደ ክርስቶስ የሚያደርገው ጎዞ ለመምራት ነው። ወንጌልን እንድናነብ የሚይደግፈን የሚገፋፋንም መጽሐፍ ነው። “ወንጌልን ስናነብ እንዲናገረንም ጭምር ነው። ወንጌልን ማንበባችን የሚናገረንን ወንጌል ማዳመጥ ይሆናል በማለት የደረሱት መጽሐፍ ይኸንን የሚያጎላ ነው” ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.