2013-02-08 14:53:40

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ዘወትር በክርስቶስ ፍቅር ማደግ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የተለመደው ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አቅርበው እንዳጠናቀቁ እዛው ከተገኙት የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ የወንድማማችነት ማኅበረሰብ አባላትን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሣቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አስከትሎ፣ ይክ የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ የወንድማማችነት ማኅበረሰብ እ.ኤ.አ. በ 1985 ዓ.ም. የ movimento di Comunione e Liberazione-ሱታፌና አርነት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ መሪ መንፈሳዊነት መሠረት በማድረግ የመሠረቱት ብፁዕ አቡነ ማሲሞ ካሚሳካ መሆናቸው ገልጦ፣ ብፁዕ አቡነ ካሚሳካ ገና ማዕርገ ክህነት ከመቀበላቸው በፊት የዚያ ሱታፌና አርነት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ አባልና የእንቅስቃሴው መስተዳድር አባል እንደነበሩም አስታውሶ፣ በተካሄደው ግኑኝነት ብፁዕ አቡነ ካሚሳካ በሬጆ ኤሚሊያና ጓስታላ ጳጳስ እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከተሰየሙ በኋላ እሳቸውን በመተካት የዚህ የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ የወንድማማችነት ማኅበር አዲስ አለቃ እንዲሆኑ የተመረጡት ክቡር ካህን አባ ፓውሎ ሶቶፔትራ እንዲሁም የሱታፌና አርነት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ክቡር አባ ኹሊያን ካሮን የዚህ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ አባላት በተለያዩ አገሮች በወንጌል ተልእኮ የተሰማሩት 18 ካህናት ጭምር መሳተፋቸው አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከዚህ ሱታፌና አርነት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ መሥራች ነፍሰ ኄር ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ጁሳኒ ጋር መገናኘታቸው ቀርበውም የእኚህ ካህን እምነት ከእምነት የመነጨ ኃሴት ጽናት የላቀው ጥልቅ አስተሳሰባቸው የእምነት ፍሪያማነት የሚያረጋገጠው አስተምህሮአቸው የተገነዘቡ እንደሆኑም አስታውሰው፣ ጥብቅ ወዳጅነት መሥረተው በሳቸው አማካኝነት የሱታፌና አርነት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ በበለጠ መንፈሳዊነቱን ለማወቅ እንደቻሉም መግለጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው ቀጥለውም የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ መሥራች ለብፁዕ አቡነ ካሚሳካ ያላቸው አድናቆት ሲገለጡም፦ “በሥነ ጥበብ ሊቅነታቸው አርቆ የመመለከቱ የጊዜ ምልክቶችን የመተንተን የሕንጸት ብቃታቸው እውነተኛ የክህነት ሕይወታቸው የሚደነቅ ነው። የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ መንፈሳዊነት እርሱም ለክርስቶስ ካለ ፍቅርና ፍቅር ከሆነ ክርስቶስ የተነሳሳ አቢይ የእረኝነት አርአያ በመከተል እንደ እርሱ ታናናሾችን በመፈለግ በማፍቀር ለእምነት ጸጋ በቃልና በሕይወት በማነጽ ለቤተ ክርስቲያን እድገት መንቃት” የሚል መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማስታወስ፣ ቅዱስ ቦሮመዮ የዚህ የወንድማማችነት ማኅበር አባላት ካህናት በክህነት ሕይወታቸው እንዲበረቱ ተግተው እንዲያገለግሉ የሚሸኛቸው መሆኑ ካረጋገጡ በኋላ፣ ብፁዕ አቡነ ካሚሳካን በእውነት መሠረት ለማደግ በእያንዳንዳችን ያለው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርቶስ ወንድሞች የመሆናችንን መለያ እንዲበለጽግ ለሚደግፈው ታላቅ የሕንጸት ሊቅነታቸው አመስግነው አድናቆታቸው እንደገለጡም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም አዲሱ የዚህ የወድማማችነት ማኅበርሰብ አለቃ በመሆን የተመረጡት አባ ሶቶፔትራ ገና የዘርአ ክህነት ተማሪ እያሉ እንደሚያውቁዋቸውና ከሳቸው ማለትም ከቅዱስ አባታችን የቲዮሎጊያ አመለካከት ጋር ቅርበት ያላቸው መሆናቸውንም አስታውሰው ስለዚህ ከዚህ ማኅበረሰብ ጋር መንፈሳዊነትና ሙሁራዊ ቅርበት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ተመክሮ መሆኑ በማረጋገጥ እግዚአብሔር ይኸንን የቅዱስ ካሮሎ ቦሮመዮ የወድማማችነት ማኅበረሰብ ስለ ሰጠን እናመሰግን፣ ለክርስቶስ ያለን ፍቅር ለወንድሞች ባለን ፍቅር እንዲመሰከር እግዚአብሔር በዚህ መንፈሳዊነት እንዲሸኛቸውም ጸልየው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.