2013-02-08 14:59:17

ሴነጋል፦ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ልኡካን ጉባኤ


RealAudioMP3 የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በካሪታስ የሚጠራው የተራድኦ ማኅበር በሴነጋል የሚገኙት የ56 ቅርንጫፎቹ ወኪሎች ባለፉት ቀናት በዚጉይንቾር ባካሄዱት ጠቅላይ ጉባኤ “የፍቅር ተግባር አንዱ የቤተ ክርስቲያን ባህርይና የተልእኮዋ መሠረታዊ አድማስ ነው” የሚለው ሃሳብ እንዳሰመሩበት ሲገለጥ፣ ይኽ “አንተ እምነት ያለህ እምነትህን በተግባር አሳየኝ” በሚል ርእስ ተመርቶ የተካሄደው 49ኛው ጠቅላይ ጉባኤ የፍቅር ሥራ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ማእከል መሆኑና ይኽ ደግሞ በቅድስት ሥላሴ ፍቅር ላይ የተመሠረተና በዚህ ፍቅር ላይ ታምኖ የሚፈጸም አገልግሎትና በቅድስት ሥላሴ ፍቅር ሱታፌ ማለት መሆኑ በማስታወስ፣ ተወካዮቹ በሴነጋል የሚታየው ድኽነት ለመቅረፍና በችግር ላይ የሚገኙትን ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት የሚሰጠው አገልግሎት ላይ እንዳስተነተነ በሴነጋል የካሪታስ ቅርጫፍ ድረ ገጽ አስታውቀዋል።
በሴነጋል የሚገኙት ልኡካነ ወንጌል ካህናት እና ዓለማውያን ምእመናን በፍቅር ተግባርና መንፈስ ታንጸው በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት መሠረት ለጌታ ያላቸው ፍቅር ለወንድሞች በሚገልጡት ተግባር እንዲኖሩ ጉባኤው በማሳሰብ፣ የሚሰጠው ትብብርና ድጋፍ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሠረት ያወጁት የፍቅር አገልግሎት ውሳኔ መሠረት እንዲታደስ አደራ እንዳለም የሴነጋል የካሪታስ ቅርጫፍ ድረ ግጽ ያመለክታል።
ጉባኤው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ የተራድኦ ማኅበራትን የሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ የወጠነው ደንብ መሠረት በሴነጋል የሚገኘው የካሪታስ ቅርጫፍ አገልግሎት እንዲያቀርብና የሚሰጠው አገልግሎት በሕጉ የተመራ እንዲሆን ተካፍሎ የመኖር ባህል እንዴት መጎልበት እንዳለበትም በመወያየት መፈጸሙ ድረ ገጹ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.