2013-02-06 14:59:11

የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 ዝክረ 20ኛው ዓመት እየተከበረ ያለው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ርእስ ሥር የቫቲካን ረዲዮ በኢየሱሳውያን ማኅበር አባል የሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ዳሪዩስዝ ኮዋልዝይክ የተመራ የሚያቀርበው ተከታታይ የሥርጭት መርሃ ግብር መሠረት ትላንትና ያቀረቡት 13ኛው አስተምህሮ፦ “ለብቻህ አይታመንም። እምነት በቤተ ክርስቲያን ነው። እምነት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የግል ጸጋና የጋራ መንፈሳዊ ገጠመኝ የሚል በጋራ የሚኖር ነው” በተሰኘው ቅዉም ሃሳብ ላይ በማተኮር፦ “እምነት የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ነጻ መልስ ነው። ስለዚህ ማንም በጫና ወይም በግድ መልስ እንዲሰጥ፣ መልስ የሚያስገድድ ጥያቄ አይደለም። ከታሪክ በጋራ እና በግል መልስ የተሰጠባቸው በጫና የቀረቡ ሃይማኖቶች እንዳሉ እንገነዘባለን። ሆኖም በግድና በጫና የቀረቡት ገና የሚቀርቡት ሃይማኖቶች እምነት ማለት አይደሉም። ‘እምነት ራሱን ከሚገልጠው እግዚአብሔር ለሚመጣ አነሳሽነት የሰብአዊ ፍጡር ነጻ ምላሽ የሆነ ግላዊ ድርጊት ነው። ነገር ግን እምነት ነጠላ ድርጊት አይደለም፣ ማንም ብቻውን መኖር እንደማይችል ሁሉ ማንም ብቻውን ማመን አይችልም። ሕይወት ራሳችሁ አልሰጣችሁም። አማኝ እምነትን ከሌሎች ተቀብሏልና ለሌሎች ማስተላለፍ አለበት። ለኢየሱስና ለባልጀራችን ያለን ፍቅር እምነታችንን ለሌሎች እንድናካፍል ያስገድደናል። በዚህ ዓይነት እያንዳንዱ አማኝ የረጅሙ የምዕመናን ሰንሰለት ቋጠሮ ነው። በሌሎች እምነት እስካልተገፋፋሁ ድረስ ላምን አልችልምና እኔም በእምነቴ ሌሎችን አምነው እንዲገፉበት እረዳለሁ፣ ቁ. 166” ጠቅሰው ካብራሩ በኋላ፦ “እምነትን ከሌሎች እንቀበላለን ለሌሎች እናስተላልፋለን። ብለዋል።
በሕፃንነታችን በቤተሰቦቻችን ጥያቄ መሠረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጸጋ ጥምቀት ትሰጠናለች በዚህ መሠረትም የቤተ ክርስትያን ማኅበርሰብ አባል እንሆናለን የወላጆች እዎን አምናለሁ የሚለው መልስ የቤተ ክርስቲያን እዎን እናምናለን ሆኖ በሕይወታችን ይመራናል። ብዙውን ጊዜ ኢየሱስን አዎን ቤተ ክርስቲያን ግን አልቀበልም። እምነት አለ ቤተ ክርስቲያን ሲባል እንሰማለ፣ ለቀደምት የእምነት አበው ቀዳሜ ቤተ ክርስቲያን የመሠረቱት በዚያች ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት እምነትን አስተላልፈውልናል። በግል የተላለፈ እምነት የለም” ካሉ በኋላ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 169፦ “ደኅንነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ነገር ግን የእምነትን ሕይወት የምንቀበለው እምነታቻን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ስለሆነ ‘ቤተ ክርስቲያን የአዲሱ ልደታ እናት እንደሆነች እናምናለን እንጂ እንደ ድኅነታችን ባለቤት (ምንጭ) አድርገን አንቆጥራትም’ እናታችን ስለሆነች የእምነት አስተማሪያችንም ነች” የሚለውን ጠቅሰው ያቀረቡትን 13ኛውን አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.