2013-02-06 14:56:11

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ ቤተ ክርስቲያን የወጣት ትውልድ ልባዊና አእምሮአዊ ትርታ ታዳምጥ


RealAudioMP3 የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዘንድሮ በወጣት ትውልድ ባህል ላይ በማተኮር ቤተ ክርስቲያን የወጣት ትውልድ ልባዊና አእምሮአዊ ትርታ ታዳምጥ ዘንድ ለማበረታታት በማቀድ ይኸው ስለዚሁ ጉዳይ በአገረ ቫቲካን የሚወያየው የምክር ቤቱ ይፋዊ ዓውደ ጥናት ዛሬ ተከፍተዋል።
ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “በዚሁ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ድረ ገጽ በኩል ብፁዕነታቸው ለወጣቱ ትውልድ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ያገኙት መልስ፣ ወጣት ትውልድ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የባህል ሊቃውንት ምሁራን ወጣቶች የሰጡት መልስ ጭምር በማሰባሰብ፣ ከእነርሱ ጋር ለመወያየትና በዚህ በሥነ አሃዝ በተራቀቀው የመገናኛ ብዙኃን ባህል ተጠቃሚና በቀጥታ የዚሁ ዘመን ወጣት ትውልድ ጋር ቀርቦ በመወያየት የእነርሱን ጥማት ቀርቦ ከእነርሱ አንደበት ማዳመጥ ለወጣት ትውልድ ወንጌል ለማበሰር መሠረት ነው” ብለዋል።
“የወጣት ትውልድ ባህል ቀርቦ ለማወቅ የወጣቱ ትውልድ ባህል ለመረዳት ቀላል አይደለም፣ ስለዚህ ባህሉ ከሚመለከተው አካል ጋር ቀርቦ የወጣቱ ባህል መረዳት ወደ ወጣት ትውልድ የሚደረገው ጉዞ ፈጣን ያደርገዋል፣ ከወጣቱ ጋር ካልተወያየህና የልቡንና የአእምሮውን ትርታ ካልተገነዘብክ ቀርበህ ለሚሻው ሁሉ መልስ ለመስጠት አይቻልም። በተለይ ደግሞ በሕንጸት ሙያ የተሰማሩት ካህናት ደናግል መንፈሳዊ መሪዎች የወጣቱ ባህል ቀርቦ የማወቅ ግዴታ አለባቸው” ካሉ በኋላ፦ ለወጣቱ ትውልድ ክቡራን ዋጋዎች የሚባሉትን ዋነኛ እሴቶች ግብረ ገብ ሥነ ምግባር መንፈሳዊነት የተሰኙትን ማሳወቅ፣ ስለዚህ ሃይማኖታዊ ነክ ጥያቄ ጠቅለል ያለ ማኅበራዊ ሥነ ምግባር ማለት አይደለ። ስለዚህ ክርስቶስን ለማሳወቅና እርሱ የሕይወት ሙላት መሆኑ ማስረዳት ያለመ ዓውደ ጥናት ነው” ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.