2013-02-06 14:52:14

በቅድስት መንበርና በኢጣሊያ መካከል የጋራ ትብብር ለማኅበራዊ እርባና መረጋገጥ


RealAudioMP3 በቅድስት መንበርና በኢጣሊያ መካከል የተደረሰው የላተራነንሰ የስምምነት ውል ዝክረ 84ኛው ዓመት ምክንያት በቅድስት መንበር የኢጣሊያ ልኡከ መንግሥት ለቅዱስ አባታችን ክብር የውሁድ ሙዚቃ ጥዑም ትርኢት የዕጣ ፋንታ ኃይል የተሰኘው የጁዜፐ ቨርዲና የበቶቨን ቁጥር ሦስት የሁድ ጥዑም ሙዚቃ ድርሰት በፊዮረንቲና የውሁድ ሙዚቃ ቡድን አማካኝነት ከትላትና በስትያን በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድተኛ የጉባኤ አዳራሽ የኢጣልያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተገኙበት ለትርኢት መቅረቡ በዓሉን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራሶ አስታወቁ።
የሙዚቃ ትርኢቱ ከመቅረቡ ቀደም ተብሎ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና የአገረ ኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ መካከል በተካሄደው ግኑኝነት የታየው የመቀራረብ መንፈስ ጥልቅና ወዳጅነት በሁለቱ አካላት መካከል የወንድማማችነት መንፈስ ጎልቶ መታየቱ ጋዜጠኛ ቸራሶ ጠቅሰው፣ ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ፦ “ቅዱስነታቸው ለኢጣሊያና ሕዝቧ ያሳዩትና የሚያሳዩት ቅርበትና አሳቢነት የሚደነቅ ነው። አሁንም ይኽ እሳቢነታቸው ለኢጣሊያ ህዝብ እንዳይለየውና ከምን ግዜም በበለጠ አሁን እጅግ ያስፈልገዋል” እንዳሉ ገልጠዋል።
በአገረ ኢጣሊያና በአገረ ቫቲካን መካከል ለጋራ ወዳጅነት በጋራ የፈጸሙት ጉዞ የላተራነንሰ የስምምነት ውል ጠቅሰው፣ የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ ባቀና እውነተኛ መንፈስ ላይ የጸና ከመሆኑም ባሻገር በመተማመን ላይ የተመሠረተ መሆኑ ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ባሰሙት ንግግር ገልጠው፦ “ቅዱስነትዎ ከሚሰጡት ምዕዳንና አስተምህሮ እንዲሁም መልእክት ለመተማመንና ለማስተንተን የሚበጀው ለማጤን የነቃ ትኵረት እንደሚሰጥበት ላረጋግጥልዎት እወዳለሁ” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራሶ ገልጠው፣ የውሁድ ሙዚቃ ትርኢት እንዳበቃም ቅዱስ አባታችን በበኩላቸውም ባሰሙት ንግግር፦ “የቨርዲ የዕጣ ፋንታ ኃይል የተሰኘው የውሁድ ሙዚቃ ድርስት ቅኝት ነገረ ሃይማኖት የሚዳስስ፣ ከእግዚአብሔር ከእምነት ከቤተ ክርስትያን ጋር የሚነጻጸር፣ የሙዚቃ ደራሲው የገዛ እራሱ ሰብአዊ ጭንቀትና ሃይማኖታዊ ፍለጋ የሚያንጸባርቅ ነው። ይኽ ደግሞ የሰው ልጅ ሰብአዊ መሆኑ ዘንድ ያለው እግዚአብሔርን የመናፈቁና የመሻቱ ያ ለሕይወት ብርሃን የሚሰጠው በጨለማ ተስፋ የሚያመለክተው የእግዚአብሔር ምሕረትና የፍቅሩ ጥማት የሚያስተጋባ ነው። በዚህ ረገድ እምነት ሰመመን ሳይሆን ተጨባጭ ተስፋ ያቀርብልናል” ካሉ በኋላ የተደመጠው የበቶቨን የኃዘን ግስጋሴ የሙዚቃ ቅኝት ጠቅሰው፦ ይኽ የሙዚቃ ድርሰት በሰው ልጅ ዘንድ በኑባሬ ያለው የዘለዓለማዊ ሕይወት ጥማትና ከነገር ሻገር ያለው መጠባበቅን የሚመሰክር ነው” እንዳሉ ቸራሶ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.