2013-02-04 14:22:15

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ በእምነትና በሚሠዋ ፍቅር ዓለም ይታደሳል


RealAudioMP3 ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምን የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ “ዓለም የሚታደሰው በእምነትና በሚሠዋ ፍቅር ነው” በሚል ርእስ ሥር በመቀጠል፦ “ትብብር አለ ሙሉ መንፈስ ወይንም ባለ እንጀራውን ሳይመለከት እግዚአብሔርን ብቻ የሚመለከት ትብብር እምነትና ፍቅርን አመዛዝኖ መኖር የተሳነው ነው። ስለዚህ እምነት እና ፍቅር የማይነጣጠሉ ብቻ ሳይሆን ለጌታ ያለን ፍቅር መመዘኛው ለባለንጀራችን ያለን ፍቅር” መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ለ 2013 ዓ.ም. አቢይ ጾም ምክንያት ባስተላለፉት ኩላዊ መልእክት ዘንድ በስፋት የተብራራ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ያመለክታሉ።
እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን ታስቦ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን፣ እንዲሁም ለ 2013 ዓ.ም. ዓቢይ ጾም ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከወዲሁ ያስተላለፉት መልእክት ጥልቅ ጥናትና አስተንትኖ የሚያሻው መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ጠቅሰው፣ “በዚህ የእምነት ዓመት በእምነትና በፍቅር መካከል ያለው ጥብቅ ትስስርና ተምሳይ በጥልቀት እንድኖር የሚያሳስብ ከመሆኑም ባሻገር አለ እምነት ፍቅር፣ ፍቅር አለ እምነት ባዶ ሰብአዊ ተግባር ወይንም ግብረ ገባዊ ግዴታ ብቻ ሆኖ ነው የሚቀረው፣ እምነትና ፍቅር”አይነጣጠሉም ብለዋል።
“ውበት፣ የመንፈሳዊነት ማራኪነት ልብን የሚነካ የቤተ ክርስቲያን ታማኝነት የአስደናቂውና ደማቁ ፍቅር ነጸብራቅ ለሚሠዋ ፍቅር ኃይል ነው። ይኽ ፍቅር በእምነት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ በማተኮር ከእግዚአብሔር የምንማረውና በቅዱስ ቁርባን በመሳተፍ የምንኖረው ነው። የቅዱሳን አብነት ብንመለከት ይኸንን እውነት ነው የሚያረጋግጥልን። ቅዱሳኖች ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር አለ ምንም ውስንነት በሙላት ገዛ እራሳቸውን በእጁ ላይ በመተው የኖሩት ፍቅር በታማኝነት ባለእንጀራን በመውደድ የገለጡትና በተለይ ደግሞ ለተናቁትና ለተናንሾች በመግለጥ የመሰከሩት መሆኑ” አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አብራርተዋል።
“በልኡላዊው ነጻው የፍቅር ሕግ መሠረት ቅዱስ አጎስጢኖስ እንደሚለውም አፍቅርና የፈለግከውን አድርግ በማለት የተነተነው ገዛ እራሱን ለመንፈስ ቅዱስ መርህነት በመተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኖረው ፍቅር እንዲሁም ቅዱስ ቪንቸስንት ዘ ፓውሊ ፍቅር ከሁሉም በላይ የሆነ ሕግና ሁሉም ሕጎች ፍቅር የሚያንጸባርቁ ፍቅር መሠረት የሚያደርጉ መሆን እንዳለባቸው ይገልጥልናል” ካሉ በኋላ ይኸንን ፍቅር የሚኖር የሌላው ችግር ሊረዳ ብቻ ሳይሆን ተከፋይ በመሆን ተገቢ ድጋፍ ለማቅረብ ይችላል፣ እምነትና ፍቅር የማይነጣጠሉ ናቸው ይኸንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው ያስተምሩናል በማለት ያቀረቡትን ርእሰ ዓንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.