2013-02-04 17:33:49

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከም እመናንና ነጋድያን ጋር የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስና በጣልያን አገር የሕይወት ቀን ተብሎ በሚዘከረው የየካቲት ወር መጀመርያ እሁድ በሚመለከት “ያለውን የኑሮ ቀውስ እውነተኛ መልስ የሚሆነው ለሕይወት ጥበቃና ለቤተሰብ ጥንካሬ አበክሮ መሥራት ነው” ሲሉ የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ክብር እንዲጠበቅ አሳስበዋል፣
ትናንትና እሁድ በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ግጻዌ መሠረት የተነበበው የሉቃስ ወንጌል በመጥቀስም እንዲህ ብለዋል፣
“ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ የዛሬው ወንጌል ከሉቃስ ም ዕራፍ 4 የተወሰደ ሆኖ ያለፈው እሁድ ወንጌል ቀጣይ ክፍል ነው፣ ኢየሱስ በትውልድ አገሩ ሁሉም ስለእርሱና ስለቤተሰቡ በሚያውቁበት በናዝሬት ቤተ መቅደስ ስላስተማረው ይናገራል፣ ረዘም ላለ ጊዜ በሌሎች የይሁዳ አገሮች ሲያስተምር ኖሮ ወደ ትውልድ አገሩ ይመለሳል፣ በአይሁዱ ሥር ዓተ አምልኮ መሠረት ቅዳሜ ዕለት በቤተ መቅድስ ገብቶ ነቢይ ኢሳይያስ ስለመሲሁ የሚናገረውን ክፍል አንብቦ ትንቢቱ በእርሱ ላይ እንደተፈጸመ እና ኢሳይያስ ስለ እርሱ እንደሚናገር ይነግራቸዋል፣ ሆኖም ግን ይህ ጕዳይ ለናዝሬታውያን አልዋጥ ይላቸዋል፤ “ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ። ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር።” (ሉቃ 4፤22) ቅዱስ ማርቆስ ይህን አስመልክቶ “ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና። እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው? (ማር 6፤2)፣ በሌላ በኩል ግን የአገሩ ሰዎች ጥሩ አድርገው ያውቁት እንደነበር ሲገለጥ፤ “እርስ በርሳቸው ይህ ከእኛ አንድ አይደለምን ይህ ሁሉ ለማስመስል እንጂ ለሌላ አይደለም” (የኢየሱስ ሕጻንነት ገጽ 11) “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” (ሉቃ 4፤22) በሌላ አነጋገር የናዝሬቱ የአናጢ ልጅ ምን ሊኖረው ይችላል፧ እንደማለት ነው፣
ኢየሱስ ይህንን የአእምሮ መታወር በማወቅ “በአገሩ የሚከብር ነቢይ የለም” ሲል ጠብ የሚጭሩ የሚመስሉ ቃላትን በቤተ መቅደስ ለነበሩ ሰዎች እየተናገረ አንዳንድ ጊዜ ከእስራኤል ይልቅ በሌሎች ታላቅ እምነት እንዳለ ለማሳየትም በዘመነ ኦሪት በታላላቅ ነቢያት ማለትም ኤልያስና ኤልሳዕ በእስራኤላውያን ያልሆኑ ሰዎች የተፈጸሙ ተአምሮችን ይጠቅስላቸዋል፣ በዚያው ግዜ ሁላቸው በአንድነት ተቋወሙት፣ ከቤተ መቅደስ ገፍተው አወጡት ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤ እርሱ ግን በታላቅ ትዕግሥት ቍጣ በሞላው ሕዝብ መካከል አልፎ ይሄዳል፣ እዚህ ላይ ለምን ነው ኢየሱስ ይህንን መለያየት ጠብ የፈለገው የሚል ጥያቄ ብቅ ሊለን ይችላል፣ በመጀመርያ ሰዎቹ በእርሱ ተደንቀው ነበር ምናልባትም በአንድ ሐሳብ የሚስማሙ ይመስል ነበር ሆኖም ግን ኢየሱስ ሰዎች በእርሱ ሐሳብ ሊስማሙ እንዳልመጣ ያሳያል፣ በመጨረሻም ለጲላጦስ እንደገለጠለት “የእውነት ምስክር ለመሆን ነው የመጣው” (ዮሐ 18፤37)፣ እውነተኛ ነቢይ ከእግዚአብሔር በስተቀር ለማንም አይታዘዝም፤ ራሱን መሥዋዕት እስከ ማድረግ ድረስ እውነትን ያገለግላል፣ ኢየሱስ የፍቅር ነቢይ መሆነ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር የራሱ እውነት አለው፣ ፍቅርና እውነት ያንድ ነገር ሁለት ስሞች ናቸው ማለትም ሁለት የእግዚአብሔር ስሞች ናቸው፣ በዛሬው ሥር ዓተ አምልኮ እነኚሁ ቃላት በቅዱስ ጳውሎስ አነጋገር “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤” (1ቆሮ 13፡4-6) ይላል፣ በእግዚአብሔር ማመን ማለት የገዛ ራሳችን ቅድመ ሁኔታዊ ፍርድን መተው እና እውነተኛ የእግዚአብሔር ግጽታ ሰው በሆነ በናዝሬቱ ኢየሱስ የተገለጠልንን መቀበል ነው፣ ይህ ጐዳና ኢየሱስን ለማወቅና በሌሎችም እንድናገለግለው ያስችለናል፣
የእመቤታችን ድንግል ማርያም ዝንባሌም በዚህ ነው የበራው፣ ከእርሷ በስተቀር የኢየሱስ ሰብ አውነትን ያጣጣመ ማን ሊሆን ይችላል፧ ሆኖም ግን እንደ ሌሎቹ ባለአገሮችዋ ናዝራውያን ዕንቅፋት ሊሆናት አልቻለም፣ እርሷ ይህንን ምሥጢር በልብዋ ትይዘው ነበር፣ በእምነትዋ ጉዞ ከመጸነሱ እስከ የመስቀሉ ጨለማው ሌሊትና የትንሣኤው ሙሉ ብርሃን ሁሉን በበለጠና እንዳዲስ መቀበሉንም አወቀች፣ ይህንን ጉዞ በታማኝነትና በደስታ እንድንፈጽም ዘንድ እመቤታችን ድንግል ማርያም ትርዳን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.