2013-02-04 14:19:17

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በባቢሎን የከለዳውያን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያናዊ ውኅደት ፈቃድ ሰጡ


RealAudioMP3 እዚህ በአገረ ቫቲካን የተሰበሰበው የከለዳውያን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ በኢራቅ የከለዳዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የኪርኩክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊስ ራፋኤል አንደኛ ሳኮ በባቢሎን የከለዳዊ ሥርዓት የምትከተለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ እንዲሆኑ ባለፈው አርብ ከመረጣቸው በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሲኖዶሱን ውሳኔ በመቀበል የቤተ ክርስቲያናዊ ውህደት እውቅና የሚሰጥ ፈቃድ ማረጋገጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊስ ራፋኤለ አንደኛ ሳኮ በኢራቅ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በስደት የሚገኙት በጠቅላላ የከለዳዊ ሥርዓት የምተከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ እንድሆኑ የመረጣቸው የከለዳዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ምርጫ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳኮ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤተ ክርስቲያናዊ ውኅደት እውቅና እዲያገኝ ላቀረቡት ጥያቄ በመቀበል ፈቃድ በመስጠታቸው ሲኖዶሱ እጅግ ደስ መሰኘቱም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.