2013-02-04 14:17:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በችግር ላይ ለሚገኙት ስደተኞች እናቶችን መርዳት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በዚህ በ 2013 ዓ.ም. በተገባው የካቲት ወር በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፦ “ለስደተኞች ቤተሰቦች በተለይ ደግሞ በችግር ላይ ለሚገኙት ስደተኞች እናቶች ድጋፍና ትብብርና ለተሻሻለ ሕይወት መልካም መስተንግዶ” እንዲረጋገጥ የሚጠራ ትብብርና ድጋፍ የጸሎት ሃሳብ እንዲሆን ማሳሰባቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው የሰጡት የጸሎት ሃሳብ ውሳኔ በማስመልከት በኢጣሊያ ቺስል በመባል ለሚጠራው የሠራተኞች ፈደራላዊ ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ኢጣሊያዊት የፐሩ ተወላጅ ሊልያና ዖክሚን ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “በዚህ በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚና የገንዘብ ሃብት ቀውስ እጅግ ያጠቃው ቤተሰብ ነው። በተለይ ደግሞ ስደተኞች በከፍተኛ ደረጃም ስደተኞች እናቶችን ነው የሚያጠቃው። ስለዚህ ስደተኛው በመጣበት አገር ለሚገኙት ቤተሰቦች መርጃ ያውለው የነበረ ድጋፍ እንዲቋርጥ ያስገደደ ሁኔታ ነው ተከስቶ ያለው። ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት ቅዱስ አባታችን ስለ እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል እንዲጸለይ ሲያሳስቡ አለ ምክንያት አይደለም” ብለዋል።
“ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚና የገንዘብ ሃብት ቀውስ ባሻገር እጅግ አሳሳቢ የሆነው የሥነ ምግባርና ግብረ ገብ ቀውስ ነው። ስለዚህ ሥነ ምግባርና ግብረ ገብ አቅቦ በመኖሩ ረገድ ስደተኛው የኅብረተሰብ ክፍል ትልቅ አብነት ነው። ካለ ምንም ማማረጥና ማጉረምረም ቆርጦ ከመሥራት ወደ ኋላ አይልም” ካሉ በኋላ አክለውም፦ ስደተኛው በተስተናገደበት አገር ኑሮውን ለመግፋትና በትውልድ አገሩ የቀሩት ቤተሰቦችን የመርዳት ኃላፊነት የሚሰማው ተካፍሎ መኖር የሚል ነው” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.